ቪድዮ ፦ በአስደንጋጩ የአውሮፕላን አደጋ 124 ሰዎች ሞቱ።
በደቡብ ኮሪያ በማረፍ ላይ የነበረ አውሮፕላን ባጋጠመው አደጋ እስካሁን 124 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል።
ጄጁ የተባለው አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን ከባንግኮክ መጥቶ በደቡብ ኮሪያው ሙዋን አየር ማረፊያ ሲያርፍ ነበር መንገዱን ስቶ ከግድግዳ የተጋጨው።
የአውሮፕላን የፊተኛው ክፍል በእሣት ሲያያዝ ታይቷል።
ምንም እንኳ እስካሁን የአደጋው መንስዔ ባይታወቅም የእሣት አደጋ አገልግሎት " ምናልባት ከወፍ ተጋጭቶ አሊያም ባለው ከባድ የአየር ፀባይ ምክንያት ሊሆን ይችላል " ብሏል።
አውሮፕላኑ 181 ሰዎች አሳፍሮ ነው ከታይላንድ የተነሳው።
አብዛኛዎቹ ደቡብ ኮሪያዊያን መሆናቸውን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
እስካሁን አንድ ተሳፋሪና አንድ የበረራ ሠራተኛ በሕይወት ሲተርፉ ሌሎች ከአደጋው የተረፉ ሰዎችን የማዳን ሥራው መቀጠሉን ቢቢሲ እና ቲአርቲ ዘግበዋል።
ቪድዮ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ
@tikvahethiopia