ዶናልድ ትረምፕ 47ኛ ፕሬዝደንት ሆነው ቃለ መሐላ ፈጸሙ
ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ ሰኞ 47ኛ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ሆነው ቃለ መሐላቸውን ፈጽመዋል። 45ኛው የአሜሪካ ፕሬዝደንት የነበሩት እና በጆ ባይደን የተሸነፉት ትረምፕ ከአራት ዓመታት በኋላ በ47 ኛ ፕሬዝደንትነት ወደ ኋይት ሐውስ ተመልሰዋል። ትረምፕ ቃለ መሐላቸውን የፈጸሙት በዋሽንግተን ሰዓት ዕኩለ ቀን ላይ ሲሆን ቃለ መሐላውን ያስፈጸሟቸው የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዋና ዳኛ ጆን ሮበርትስ ናቸው። ከሥነ ሥርዐቱ ቀደም ብሎ ተሰናባቹ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ተረካቢውን ፕሬዝደንት በኋይት ሐውስ ከተቀበሏቸው በኋላ አብረው በአንድ ኦቶሞቢል ቃለ መሐላው ወደሚከናወንበት ካፒቶል ሂል ተጉዘዋል። በዋሽንግተን የአየር ሁናቴው እጅግ በመቀዝቀዙ የበዓለ ሲመቱ ሥነ ሥርዓት በምክር ቤቱ ህንጻ ካፒቶል ሮተንዳ በተባለው ግዙፍ አዳራሽ ውስጥ በመከናወን ላይ ነው።
via የአሜሪካ ድምፅ (author: voadigital@voanews.com (ቪኦኤ ዜና))