#Press_conference
አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ክለባችን እሁድ በፕሪሚየር ሊጉ ከሌስተር ሲቲ ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ አስቀድመው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
ሩበን አሞሪም ስለ ሃሪ ማጓየር | 🗣''በሃሪ ማጓየር ጉዳይ ላይ ሀላፊነት መስወድ አልፈለግንም ስለሆነም ከትላንቱ ጨዋታ ውጭ አድርገነዋል።''
''ሃሪ ማጓየር አሁን በአሪፍ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከእሁዱ ጨዋታ አስቀድሞ ተጨማሪ ምርመራ የሚደርጉለት ይሆናል።''
ሩበን አሞሪም ስለ ማሰን ማውንት |🗣
ሜሰን ማውንት ሙሉ በሙሉ ከጉዳቱ ያገገመ ሲሆን ለእሁዱ ጨዋታ ወደ ቡድን ስብስብ ይመለሳል።''
''በተጨማሪም ጨዋታውን ከተጠባባቂ ወንበር ተነስቶ የማድረግ እድሉ ሰፍ ነው።''
"እሱ እና እያንዳንዱ ተጫዋች ያስፈልጉናል። ብዙ ደቂቃ መጫወት አይችልም ነገር ግን የአምስት ደቂቃ የሜሰን ማውንት ጨዋታ እንኳን ፍፁም ነው"
"ሜሰን ማውንትን በእውነት እወደዋለሁ። እሱን አይቼ ምን ያህል በጉዳት እንደተሰቃየ መገመት አይከብደኝም።''
''በትክክል ሁሉንም ነገር እንዴት እንደሚሰራ አውቃለሁ ትክክለኛውን ምግብ ይመገባል የሰውነት አካሉንም በሚገባ ይጠብቃል።''
''አንድ ተጫዋች እንደዚህ ሁሉንም ነገር በትክክል ሲሰራ እዚህ ክለብ ውስጥ ከሁሉም ሰው ድጋፍ ይኖረዋል።''
የአሞሪም ሀሳቦቹ በጨዋታዎች ላይ መታየት ስለመጀመራቸው |🗣
"ለጨዋታዎች ያለንን እቅድ በተሻለ ሁኔታ እየተገነዘብን ነው። ግብ ተቆጥሮብን አእምሯችንን አጥተን ሌላ ግብ ማስተናገድ አንፈልግም።''
አሞሪም ተጫዋቾችን ስለ መቀያየር |🗣''ድካምና ጉዳት ስላለ በተለያዩ ጨዋታዎች ተጫዋቾችን ማቀያየር ይኖርብናል።''
''ኮቢ ሜይኖ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወደ ሜዳ ይመለሳል የሚል ተስፋ አለኝ በተጨማሪም ማኑኤል ኡጋርቴም ለመመለስ ተቃርቧል።''
''ይህ ደግሞ የቡድን ጥልቀትን ይጨምርልናል።''
#ይቀጥላል...
@Man_United_Ethio_Fans @Man_United_Ethio_Fans