የትላንትናው የካሪንግተን ልምምድ የጀመረው ከበድ ባለ የሰውነት ማላቀቂያ እስፖርት ነበረ።
ቀጥሎም ፍጥነት ላየና የቦታ አረዳድ (positional awareness) ትምህርት ተሰጥቷቸዋል።
ተጫዋቾች በምን አይነት አቅጣጫ መሮጥ እንዳለባቸው እያንዳንዱ ትምህርት እንዲወስዱ የተደረገ ሲሆን፡ በማጥቃት ክፍሉ ላይ ደግሞ እድል የመፍጠር ሁኔታ (creativity) እና የሚያጠቁ ተጫዋቾች ጨዋታን እያነበቡ ቦታን መቀያየር (fluidity)ን ያካተተ ነበር። የማጥቃት ክፍል ላይ የሚገኙ ተጫዋቾች ከሚሰጣቸው ስልጠና ባሻገር እርስ በራሳቸው በመናበብ የግል ፈጠራቸውን እንዲያሳዩም ተፈቅዶላቸዋል።
የልምምድ ፕሮግራሙ እርስ በእርስ በመጋጠም ተጠናቋል። ግጥሚያውም ከሌላው ጊዜ ጠንከር ያለ ነበር።
@Manchester_Unitedfansz@Manchester_Unitedfansz