የ ማርከስ ራሽፎርድ ጉዞ |
ከማንችስተር ጉዳናዎች እስከ ትያትር ኦፍ ድሪምስ ከፍታን እና ዝቅታን ያየው አሁን ደግሞ በበሚንግሀም ሊደምቅ ስለተዘጋጀው የልጅነት ማጣቱን እና ድህነቱን በመገንዘብ አቀም የሌላቸውን ማህበረሰቦች በመደገፍ ተምሳሌት መሆን የሚችል ድንቅ ስብዕና ስላለው ማርከስ ራሽፎርድ አስቃኛችዋለው።
ትያትር ኦፍ ድሪምስ ከታዳጊነት አንስታ እስከ ማዕረግ ያበቃችሁ ልጇን ለበርሚንግሀም ከተማ መናገሻ ክለብ አስቶንቪላ አሳልፋ ሰጥታለች። ታላቁ የቀይ መንደር ጫና ከወጣትነት አንስቶ አንፀባራቂ ጊዜያትን አስከፊ አጋጣሚዎችን አሳልፎ በአለም የታወቀበትን መናገሻውን ለቆ ወደ ሌላ መንደር ከትሟል።
ኦልድትራፎርድ ያደረገላትን አትረሳም ማርከስ ራሽፎርድ በማንችስተር ዩናይትድ አብርቷል ቀያይ ሰይጣናቱ ውጤት በሚፈልጉበት ወቅት ደርሷል። አንድ ጊዜ ሸፍ አንድ ጊዜ ደግሞ ዝቅ ብሏል።
በክቡርነት ኢንግሊዝን የሞሸራት የልጅነት ማጣቱን እና ድህነቱን አስታውሶ አቀም የሌላቸውን ማህበረሰቦች በመደገፍ ተምሳሌት መሆን የሚችል ድንቅ ስብዕና ያለው ሰው ነው ማርከስ ራሽፎርድ።
ማርከስ ራሽፎርድ የተወለደው በኦክቶበር 31 እ ኤ የዘመን ቀመር በ 1997 በማንቸስተር ከተማ እንግሊዝ ውስጥ ነው። እንደማንኛውም የመንደሩ ልጆች እግርኳስን ከልጅነቱ ጀምሮ ተጫውቶ ያደገው።
በማንቸስተር ከተማ ውስጥ በሰራተኛ ቤተሰብ ውስጥ ያደገው ራሽፎርድ ለእግርኳስ ያለውን ፍቅር በመገንዘብ ታላላቅ ወንድሞቹ ወደ እግርኳሱ በይበልጥ አስገቡት። እናቱ ሜላኒ ማይናርድ ቤተሰቡን በመደገፍ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የተገኘውን ስራ ሰርታ ነው ልጆቿን ያሳደገችሁ። ማርከስ ራሽፎርድ ስለ እናቱ ሲያወራ ቃላትም የለውም። ለእግርኳሱ ያለውን እምቅ ፍቅር በመገንዘብ በማበረታታት ከጎኑ የቆመች እጅግ ድንቅ እናት ናት።
በየጎዳናዎቹ እግርኳስን በመጫወት ያደገው ማርከስ የማንቸስተር ዩናይትድ አካዳሚን በ 7 አመቱ በ 2004 አ ም ተቀላቀለ። በዩናይትድ የ ወጣት ቡድኖች ደረጃ በማለፍ በቴክኒክ ክህሎቱ፣ በስራ ባህሪው እና በብስለት አሰልጣኞችን ማስደመሙን ተያያዘው። ምንም እንኳን በቤተሰብ የፋይናንስ ፈተናዎች ቢገጥሙትም ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች የመሆን ህልሙ ላይ ትኩረት በማድረግ እግርኳስን ገፍቶበታል።
ማርከስ ራሽፎርድ ለመጀመሪያ ጊዜ በማንቸስተር ዩናይትድ ማልያ ጨዋታ ያደረገው ፌብሩዋሪ 25 ቀን እ ኤ አ 2016 ዓ ም በ UEFA Europa League ከዴንማርኩ ክለብ ኤፍሲ ሚዲትጄላንድ ጋር ነበር የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደረገው። ሁነቱም በመጨረሻው ደቂቃ ላይ አንቶኒ ማርሲያል ባጋጠመው ጉዳት ነበር ጨዋታ ያደረገው። ማንችስተር ዩናይትድ 5-1 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ሁለት ጎሎችን አስቆጥሮ ያገኘውን እድል በሚገባ ተጠቅሟል።
ከሶስት ቀናት በኋላ ፌብሩዋሪ 28 ቀን 2016 ዓ ም የመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታውን ከ አርሰናል ጋር አደረገ። በዚያም ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ 3-2 በሆነ ውጤት ጨዋታውን ሲያሸንፍ ሁለት ጎሎችን ከመረብ አዋህዷል። በ 18 አመቱ ከአካዳሚው ወደ ዋናው ቡድን በማደግ በማንቸስተር ዩናይትድ የማንፀባረቅ ጉዞውን ጀመረ።
ማርከስ ራሽፎርድ በዩናይትድ ኪንግደም የህጻናት የምግብ ድህነትን በመቅረፍ ላደረገው ልዩ ስብዕናአዊ ከማንቸስተር ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት በጁላይ 2021 ተሸልሟል። ማርከስ ራሽፎርድን በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ላሳየው የማያቋርጥ የበጎነት እንቅስቃሴ አጉልቶ አሳይቷል።
በ ዩናይትድ ኪንግደም መንግስት ትምህርት ቤት በ በዓላት ወቅት ለችግርተኞች ነፃ የትምህርት ቤት ምግብ በማቅረብ ይህም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ተጠቃሚ አድርጓል። ከዚህ ውጪ ምግብ በ ማከፋፈል እንደ FareShare ካሉ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋር በመተባበር ወጣቶችን በማነሳሳት *you are champion * የተሰኘ ምርጥ መጽሐፍ አዘጋጅቶ ለማህበረሰቡ አጋርቷል።
በእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን እ ኤ አ በ2018 እና 2022 የዓለም ዋንጫ፣ እንዲሁም በ2021 የአውሮፓ ዋንጫ ለሀገሩ ለእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ተጫውቷል። በEuro 2020 የ ፍፃሜ ጨዋታ ፔናልቲ በመሳቱ የዘረኝነት ጥቃትም ደርሶበታል።
ክብር ዶክተር ማርከስ ራሽፎርድ በብዙሀን ዘንድ መታየት ያለበት ነገር ማርከስ ራሽፎርድን ብቃቱ ወጥ እንዳይሆን ያደረገው የማንቸስተር ዩናይትድ የአሰልጣኝ ማባረር ነው። የእሱን ማንነት እየቀነሰው ጥራቱንም እያወረደው ሄደ በስተመጨረሻም ካሳደገችሁ ማንችስተር ወደ በርሚንግሀም ሄደ።
ትያትር ኦፍ ድሪምስ ከታዳጊነት አንስታ እስከ ማዕረግ ያበቃችሁ ልጇን ለበርሚንግሀም ከተማ መናገሻ ክለብ አስቶንቪሌ አሳልፋ ሰጥታለች። ታላቁ የቀይ መንደር ጫና ከወጣትነት አንስቶ አንፀባራቂ ጊዜያትን አስከፊ አጋጣሚዎችን አሳልፎ በአለም የታወቀበትን መናገሻውን ለቆ ወደ ሌላ መንደር ምናልባትም ላይመለስ ሄዷል።
✍
@ermias_ks@Manchester_unitedfansz@Manchester_unitedfansz