"ከሁለቱ የጽድቅ እንቅፋቶች እናስተውል"!
፩.ጸድቄአለሁና
፪. አልጸድቅም
ጸላኤ ሠናያት ሰውን የሚጎዳበት ሁለት ወጥመዶች አሉት። አንዱ ጸድቂያለሁ ማሰኘት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አልጸድቅም ማሰኘት ነው። በሁለቱም ምክንያቶች ጽድቅ መሥራት አይቻልም። ጸድቄያለሁ የሚያሰኛቸው መናፍቃንን ነው። ለምን ሲባሉ ጌታን እወደዋለሁና ይላሉ። አምናለሁና ይላሉ።
ጌታን ስለምወደው ጸድቄያለሁና ጽድቅ አልሠራም የምትል ከሆነ የምትድን አይምሰልህ። ለምን ትለኝ እንደሆነ ጌታ ራሱ በመውደድ ብቻ አላዳነንምና። እወዳችሁአለሁና ዳኑ ብሎ በዙፋኑ ተቀምጦ ትእዛዝ ሰጥቶ አልቀረም።
ወዶ ምን አደረገ ትለኝ እንደሆነ፦
ምሉዕ ስፉሕ ጌታ በጠባብ ደረት በአጭር ተወሰነ። ሰማይን በደመና የሚሸፍነው በጨርቅ ተጠቀለለ።
ከነደ እሳትነቱ የተነሳ ኪሩቤል የሚንቀጠቀጡለት በብላቴናዋ በድንግል ማኅፀን ተወሰነ። ምድርና ሰማይን የሚያቀልጣቸው የክብር መብረቅ በክንደቿ ታቀፈችው። በፊቱ የእሳት ጎርፍ የሚንቆረቆርለትን በከንፈሮቿ ሳመችው። አገልጋዮቹን የእሳት ነበልባል የሚያደርገውን እንዳይበርደው እንስሶች አሟሟቁት። አዳራሹን በመብረቅ የሠራው በበረት ተኛ። ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን የተሠወረው ቅጠል ለበሰ። የስደተኞች ተስፋ ተሰደደ። የሰማይና የምድር አባት በየጥቂቱ አደገ። ምድርን በደሙ የሚያነጻት ማይን ያነጻት ዘንድ ተጠመቀ። የዓለማት ዓለም ማደሪያ አጥቶ ቀን በምኩራብ ሌሊት በተራራ ተንከራተተ። የመምህራን አምላክ ለማይሰማ ሕዝብ በሰው ቃል ዝቅ ብሎ አስተማረ። ለመምህራን በሞገስ መከበርን የሰጠ እየተሰደበ አስተማረ። መላእክት እያመሠገኑ ለማመስገን የሚሳሡለት የአይሁድን ጽርፈት ሰማ። ለተበደሉት የሚፈርድላቸው በፍርድ አደባባይ ቆመ። ከፍርድ የሚያድነው ተፈረደበት። እስረኞችን የሚፈታ ታሰረ። ሰውን ወደ ሰማይ በልዕልና ስቦ የሚያሳርገውን ጎተቱት። መንሥኤ
ሙታኑን ጣሉት። ቁስለኞችን የሚፈውሰውን ቸንክረው አቆሰሉት። ራሱን ሊያለብስ የመጣውን አራቆቱት። ርኩሳኑን በደሙ ያጠበውን ርኩስ ምራቅ ተፉበት።የኃጢአትን እሾህ የሚነቅለውን የእሾህ አክሊል ደፉበት። የሕይወትን ውኃ መራራ አጡጡት። ዲያብሎስን በመስቀሉ የቸነከረውንበጦር ወጉት። ሕይዎት እርሱን ሰቅለው ገደሉት። የምድር መሠረት የሰማይን ጽንዓት በምድር ውስጥ ተቀበረ። ትንሣኤና ሕይወት ነውና ሞትን በሞቱ ደምስሶ ተነሣ!
ወደጄ ሆይ ጌታን ስለምወደው ስለማምነው ጸድቄያለሁ የምትል ከሆነ እንዲህ ብሎ ሲጠይቅህ ምን ትመልስለታለህ? ልጄ ሆይ እኔ አንተን ወድጄ ተሰቀልኩልህ።አንተ እኔን ወደህ ምን ሆንህልኝ?በዚህ ጊዜ ስለምወድህ ትጋት ትቼ ሰነፍሁልህ ልትለው ነው? ሁሉን የሚችል አምላክ በቃሉ ብቻ ማዳን እየቻለ ነገር ግን ፍቅሩን በመከራ ገልጦ ካዳነ ሰው ለአምላኩ ቃል ብቻ እንዴት ይበቃዋል?
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወረቅ እንዲህ ሲለን እንስማ!
"ኢትበል እፈቅድ ባሕቲቱ=ወዳጄ እወዳለሁ ብቻ አትበል"ዋናተኛ ዋና እወዳለሁ በማለት ወንዝ ይሻገራልን?ሐናጺ መሆን የሚሻ ቤት መስራት በመፈለግ ብቻ ሙያውን ሳይለምድ ቤት መስራት ይችላልን? መርከበኛ መሆን የሚሻ መርከብ መቅዘፍን ሳይለምድ ሊቀ ሐመር መሆን ይችላልን?ጸሐፊስ መጻፍ በመፈለግ ብቻ ፊደል ሳያውቅ መጻፍ ይችላልን? መንጻት የሚፈልግስ ሳይታጠብ በመፈለግ ብቻ ይነጻልን? የተራበስ ስለ ምግብ በማሰብ ብቻ ይጠግባልን? ጽድቅንስ በመሥራት እንጅ በመውደድ ብቻ መዳን ይቻላልን?
ሁለተኛው ደግሞ አልጸድቅም ማለት ነው።
እንደዚህ የሚያሰኛቸው ደግሞ ምእመናንን ነው። መጀመሪያ ጥቂት ጥቂት እያለ ከጽድቅ ስራ ያወጣቸዋል። ከዚያ እግዚአብሔር መሐሪ ነው እያሰኘ ኃጢአት እንዲጨምሩ ያደርጋቸዋል። ከዚያ ወዲያ ፍጹም ኃጢአተኛ ሲሆኑ በኋላ እንዳይመለሱ መቼም አልጸድቅ ያስብላቸዋል።
የእመቤ ታችን ልጆች ንቁበት። ላልጸድቅ ሲያሰኛችሁ ክርስቶስ የውበት ባሕር ነው ብላችሁ መልሱለት። በአንዲት ውኃ ብዙ ሰዎች ቢታጠቡ ትደፈርሳለች። ክርስቶስ ግን የጎሰቆሉ ሁሉ ወደ እርሱ ገብትው ሲነጹ የእነርሱ ጉስቁልና እርሱን የማይለውጠው የምሕረት ባሕር ነውና እየገባን እንንጻ! በጭቃ የተለወሰውን ወርቅ ወልውለው አጥርተው ለአክሊልነት ያበቁታል። በእግር ከሚረገጥ ጭቃ በታች የነበረውን አጥርተው ከራስ በላይ ያውሉታል። ከምእመንነት በታች ወርዶ ጌታውን የካደውን ቅዱስ ጴጥሮስን በንስሐ ጠርቶ ርእሰ ሐዋርያት እንዳደረገው አትዘንጋ! እግዚአብሔር ቸር ነው ብሎ ኃጢአት መስራት ነው እንጅ ክፉ
እግዚአብሔር ቸር ነው እያሉ መመለስ ያድናል።
አሁንም ተስፋ ቆርጠን አንዘግይ! ለመመለስ ያብቃን!ደግሞ ማንንም የማትጸየፍ እናት አለችን። ምን ብንገዳገድ እርሷን እየተመረኮዝን እንነሳ!( በትረ ሃይማኖት ድንግል ማርያም)
ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረ_ኪዳን
@mekra_abaw✝️❤️🙏