Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹 dan repost
ከአመታት በፊት እነዘመድኩን በቀለ ቲያንስን ባሟሟቁበት ወቅት በኔትዎርክ ማርኬቲንግ ተጭበርብሮ ብዙ ሰው መክሰሩን እናስታውሳለን። በወቅቱ የተወሰኑ ሰዎች ታስረው የተፈቱ ቢሆንም በየግዜው ዘዴያቸውን እየቀያየሩ ማጭበርበራቸውን ቀጥለዋል።
በቅርብ ግዜ ፊያስ እና crowd 1 ብዙ ሰው አጭበርብረው መሰወራቸው ሳይረሳ ሰሞኑን ደግሞ CMV የተባለው አጭበርባሪ መሰወሩ እየተነገረ ነው። አሁንም እንደETCare ያሉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ቢሮና ምርቶችን እያሳዩ ማጭበርበራቸውን ቀጥለዋል።
ሁሉም ህዝቡን ለማጭበርበር የሚጠቀሙበት ዘዴ በቀላል ገንዘብ በአጭር ግዜ ያለብዙ ድካም ገንዘብ መስራት እንደሚቻል በመቀስቀስ ነው። ከዛ እናንተ የማይጠቅማችሁን ስልጠና ወይም ምርት ከፍላችሁ እንድትወስዱ ካደረጉ በኋላ ሌላ ሰው ካመጣችሁና በስራችሁ ሌሎች መግዛት እስከቀጠሉ ትርፍ እንደምታገኙ ያወራሉ። ይሁንና በዚህ የሚጠቀሙት የመጀመሪያዎቹ አጭበርባሪዎች ብቻ ሲሆኑ ከስር ያሉት ከተበላበት በኃላ ስለሚደርሱ ብራቸውን ተበልተው ይቀራሉ።
ወገን አትታለል!
ያለልፋት ያለድካም ገንዘብ ታገኛለህ ና የሚል ካለ ሊበላህ ነው። ስራ እውቀትና ሙያ ኑሮህ ተቀጥረህ ወይ በራስህ እየሰራህ ሪዝቅህን የምታገኝበት ነው። አትሸወድ! ቢን ዓሊ