Postlar filtri


ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️ dan repost
በስድስት ቀን ብቻ 10,691 ብር ሰርቻለሁ ብል ማን ያምናል ?
https://www.smartrobotuk.com/#/pages/reset/reset?inviteCode=38546664

ስራውን በፍጥነት መጀመር የምትፈልጉ ብልጥ ሰዎች ብቻ
በዚህ አድራሻችን በውስጥ ለማናገር @Melat_Admin


የመረጠችህን ምረጥ!

ብዙ ሴት ታውቃለህ፣ ከብዙዎቹ ጋርም የተለያየ ግንኙነት ይኖርሃል። ከነዚህ መሃል ግን አንዲት ሴት ፈልጋና ወዳህ ወደ ህይወትህ ትገባለች። ይህቺ ሴት በተለየ መንገድ ከጎንህ ትቆማለች፣ እሴትን ትጨምርብሃለች፣ ዋጋህን ከፍ ታደርጋለች፣ ከማንም በተለየ ትረዳሃለች ታግዝሃለች፣ በእርሷ ካንተ ጋር መሆን ነገሮች ሁሉ ምንያህል መቀየር እንደቻሉ ታስተውላለህ። ይህቺ ሴት ልቧን ትሰጥሃለች፣ ክብሯን፣ መዓረጓን፣ ማንነቷን፣ ሁለመናዋን አሳልፋ ትሰጥሃለች፣ ታምንብሃለች። ምንም በሌለህ ሰዓት አብራህ ነች፣ የምትፈልገው አንተን እንጂ አንተ ያፈራሀውን ንብረት ወይም የተሰጠህን ዝና አይደለም። ይህቺ ሴት እውነተኛዋ ሴት ነች፣ ይህቺ ሴት ያንተ ሴት ነች፣ ይህቺ ሴት መርጣህ መጥታለችና ብታቆያት ታተርፋለህ ከተለየሃት ግን ብዙ ነገር ታጣለህ። ከመረጠችህና ከመረጥካት ሴት የትኛዋ ህይወትህን ልታጣፍጥ እንደምትችል አስቀድመህ ተረዳ። ምናልባትም ያንተ ምርጫ የማትፈልግህ ሴት ላይ ወድቆ ሊሆን ይችላል። እርሱ ደግሞ ምንያህል ከባድ ሁኔታ ውስጥ እንደሚከትህ አንተ ታውቃለህ።

አዎ! ጀግናዬ..! ብልጥ ሁን፣ ወዳጅህን በጥበብ ምረጥ። ወዳጅ ሲባል የአጭር ጊዜ ወዳጅ አይደለም፣ ወዳጅ ሲባል ዛሬ አግኝተህ ነገ የምትተወው ወዳጅ አይደለም። እውነተኛዋን የህይወት ዘመን ወዳጅህን በጥንቃቄ ምረጥ። ብዙ ሰው ልታውቅ ትችላለህ ብዙ ሰው ሊቀርብህ ይፈልግ ይሆናል ነገር ግን ሁሉም ፈላጊህ የልብ ወዳጅህ አይደለም፣ ሁሉም ጠላትህም የህይወት ዘመን አሳዳጅህ አይደለም። ሰው መቼ እንደሚቀየር አታውቅምና የመረጠችህን ምረጥ፣ ከወደደችህ ተጠጋ፣ ከፈለገችህ ጋር አንድ ሁን። ጊዜያዊ ደስታህን ብቻ ለማርካት እዚም እዛም አትበል። ህይወትህ የተገደበ ነው፣ በጊዜው ቁብነገር ያስፈልገዋል። ያየሀው ቢያምርህ አንዱንም ሳታገኝ ልትቀር እንደምትችል እወቅ። ጉጉትህን ገድበው፣ ስሜትህን ሁሉ አትስማ፣ የመረጥካትን ስታሳድድ የመረጠችህን እንዳታጣ ተጠንቀቅ። ቁብነገረኛ መሆን በሚኖርብህ ጉዳይ ስትቀልድ ብትገኝ ህንወትም በተራዋ ስትቀልድብህ ትመለከታታለህ። የህይወት ዘመን አጋርህ የህይወት አቅጣጫህን የመቀየር ትልቅ አቅም እንዳላት አስተውል። ነገሮችን ዛሬ ላይ ማስተካከል እየቻልክ ለነገ ቁጪት ራስህን አታመቻች።

አዎ! ጀግኒት..! ብዙ ምርጫ ቢኖርሽም መሆን የምትችይው ግን ከአንድ ሰው ጋር ነው፤ ብዙ ሰው ብታውቂም ያንቺ ብቻ ሊሆን የሚችለው አንዱ ብቻ ነው። ደጋግሞ የሚያስብሽ፣ የተለየ ቦታ የሰጠሽ፣ በልቡ ላይ ያነገሰሽ ሰው እያለ የማያስታውስሽን፣ በንቀት አይን የሚመለከትሽን አይንሽን ለአፈር ያለሽን ሰው እየተለማመጥሽ ጊዜሽን አታባክኚ። ሰው ወዶ እንጂ ተገዶ በፍቅር ሊወድቅ አይችልም፣ መርጦ እንጂ ተመርጦ ደስታን ሊሰጠን አይችልም። ራስሽን አታሳዝኚ፣ ውስጥሽን አታውኪ፣ ልብሽን አታድክሚ። ዓለም እንጂ ህይወት ዘጠኝ አይደለችም። ያንቺ ሰው እያለ ሌላ ሰው ጋር አትሂጂ፣ እንደ ልዕልት የሚንከባከብሽ እያለ እንደ ባሪያ የሚያሰቃይሽ ጋር አትሂጂ። ህይወትሽ ሲዖልንም ሆነ ገነት ይሆን ዘንድ ወሳኟ አንቺ እንደሆንሽ አስተውይ። ለህይወትሽ የሚሆን ትክክለኛ ሰው ምረጪ፣ በምርጫሽም የመረጠሽን ምረጪ። ከገዛ ስሜትሽ ቀደም በይ፣ በአስተውሎት ተራመጂ፣ ወሳኝ ውሳኔዎችን በአንክሮ አሳልፊ።


በምክንያትህ ተመራ!

ህመሙን እለፈው፣ ስቃዩን ተሻገረው፣ ውድቀትህን ተጠቀም፣ በመገፋትህ እራስህን ስራው፣ በመከዳትህ ለእራስህ ታመን፣ በኋሊት ጉዞህ እራስህን መርምር፣ በውጤት አልባው ጥረትህ እራስህን ገንባ፣ በተለተለት የግል ጦርነትህ ብቁ ሆነህ ተገኝ። ሽንፈትህ ተስፋህን እንዳይገድለው፣ ስህተትህ ዋጋህን እንዳያሳንስ አስቀድመህ ለሽንፈትና ለስህተት ያለህን አመለካከት አስተካክል። ውድድሩ ውስጥ ስለገባህ ልትሸነፍ ትችላለህ፣ ስለሞከርክ ልትሳሳት ትችላለህ፣ በመጣርህ ብቻ ልትሰበር ትችላለህ አመለካከትህ ግን ይህን ሁሉ ድካምና ውጤት ሊያስታርቅልህ ይችላል። እራስህን ስለሰጠሀው ብዙ ነገር ፈጥኖ ፍሬ እንደሚያፈራ ልትጠብቅ ትችላለህ ነገር ግን አንዳንድ አካሔዶች ገና ከጅምራቸው ስህተት ነበሩና ምንም እንኳን አጥብቀህ ብትታገልላቸው፣ ዋጋ ብትከፍልላቸው፣ እራስህን አሳልፈህ ብትሰጥላቸው እንኳን ውጤት አይኖራቸውም።

አዎ! ጀግናዬ..! የጉዞ አቅጣጫህን፣ የትግልህን ምክንያት፣ የጥረትህን የኋላ መነሻ በሚገባ እወቀው። ለምን እየታገልክ ነው? ምን እንዲፈጠር እየጣርክ ነው? ለምንስ ይህን እልህ አስጨራሽ ጉዞ ጀመርክ? ስሜትህን ወደጎን በለው፣ የሚወራብህን ወሬ ከቁብ አትቁጠረው፣ በቀደመ ስህተትህ አትሸበር፣ ውድቀትን አትፍራ፣ በሌሎች ኪሳራ እራስህን አታስፈራራ። በምክንያትህ ተመራ፤ በጥበብ ተራመድ፣ በእውቀት ወደፊት ተጓዝ፣ በምርጫህ ፅና፣ በውሳኔህ ተማመን። ማንም በአመለካከትህ ላይ ስልጣን የለውም፣ ማንም በግል አቋምህ፣ በግል ውሳኔህ ላይ ጣልቃ የመግባት መብት የለውም፣ ማንም በምርጫህ ምክንያት ጫና ውስጥ ሊከትህ አይችልም። በመረጥከው፣ ባመንከውና በወደድከው ፅንፍ ከማንም በላይ እስከ ጥግ መጓዝን ብትፈልግ ማን ሊያስቆምህ ይችላል? ማንም! እምነትህ ወደፊት ይመራሃል፤ ደጋግመህ በአይነ ህሊናህ በምናብህ የምትመለከተው መዳረሻህ መንገዱን ሁሉ ያቀናልሃል።

አዎ! ወደፊት ስትጓዝ፣ በፅናት ስትራመድ፣ እራስህን ብቁ ለማድረግ ስትጥር የተዘጉ የሚመስሉ እድሎች ሁሉ እየተከፈቱ ይመጣሉ፣ በፊት በጨለማ የተሞሉት መንገዶችህ የብረሃን ጭላንጭል እየታየባቸው ይመጣል፣ ተስፋ የቆረጥክባቸው፣ "ዋጋ የላቸውም፣ አይጠቅሙም" ያልክባቸው የግልና የሃገርህ ጉዳዮች የምርም የለውጥና የእድገትህ ምክንያቶች ሲሆኑ ትመለከታለህ። ይህን የቻይኖች አባባል አስታስ፦ "አንድ ችግር ስትፈታ ብዙ መቶ ችግሮችን ታርቃለህ።" ችግር ሁሉም ቦታ አለ፣ ካንተም ይሁን ከሌላ አካል መፍትሔ የሚፈልግ ጉዳይ በየቦታው፣ በየደረጃው የትም አለ። አንተ ግን የእራስህን ሃላፊነት ብቻ ተወጣ፣ ወደፊት እየተራመድክ የእራስህን ችግር ብቻ ፍታ፣ እራስህን ለውጥ፣ እራስህን አሳድግ። የእድገት ጉዞህ በእራሱ የብዙዎችን ችግር እንድትፈታ ያደርግሃል፤ የለውጥ መንገድህ አይነተኛ ተመረጫ የመፍትሔ ሰው ያደርግሃል። በምክንያትህ ተመራ፣ በውጤትህም አሸብርቅ።


ጭንቀትህ የለም!

ሰውነት ማሰብ መገለጫው ነው፤ ማሰላሰል፣ ማመዛዘን መለያው ነው፤ ማስተዋል፣ መወሰንና በተግባር መግለፅ የማንነቱ መለኪያ ነው። በሰው አምሳል ምድር ላይ መመላለስ ብቻውን ሰው ሊያስብል ቢችልም እውነተኛውን ትክክለኛ ተፈላጊ ሰው ግን ሊያስብል አይችልም። ሰውነት ውስጡ ጥበብ አለ፣ ሰውነት በጉያው የአምላክን ድንቅ ሃይል ይዟል፣ ሰውነት በትንሹም በትልቁም የሚደነግጥና እንቅልፍ የሚያጣ፣ በተጨበጠውም ባልተጨበጠውም በጭንቀት የሚባክን አይነት አይደለም። የሰውነትን ምንነት ስትረዳ እራስህን በሚገባ ማክበር ትጀምራለህ፣ ማንነትህን ስታውቅ የምርም በጊዜያዊ ሀሳብና ጭንቀቶች መሸበርህን ታቆማለህ። ለማን ብለህ ነው ውሎህን በሚያውክ ሃሳብ ተጠምደህ የምትውለው? ማንን ደስ እንዲለው ነው ባልተጨበጠ ወሬ ምክንያት የውስጥ ሰላምሽን የምታጪው?

አዎ! ጀግናዬ..! ጭንቀትህ የለም! ስራህን በአግባቡ እንዳትሰራ ያደረገህ፣ ትምህርትን እንዳታጠና የከለከለህ፣ በሰዎች ፊት ሃሳብህን እንዳትገልፅ ያደረገህ፣ የእራስህን አዲስ ስራ እንዳትጀምር አስሮ የያዘህ፣ ከሱስህ እንዳትላቀቅ ፋታ የነሳህ የገዛ ጭንቀትና ስጋትህ ነፍስ የለውም፣ ምንም ሊያመጣብህ አይችልም። ያላንተ ይሁንታ ብቻውን ምንም ሊያደርግህ አይችልም፤ በውስጥህ የተፈጠረው አለመረጋጋት፣ ዘወትር የሚያውክህ አሉታዊ ስሜት፣ ሰላምህን የሚነሳህ የሰዎች ሃሳብና አስተያየት ካንተ ፍቃድ በቀር ምንም ሊያስከትልብህ አይችልም። አምነህ የተቀበልከው ስጋት መረጋጋት ይነሳሃል፤ እውነት የመሰለህ የሰዎች አስተያየት ውስጥህን ይረብሸዋል፤ ይሉኝታ ዘመንህን ሙሉ በጭንቀትና በፍረሃት አንድ ቦታ ላይ እንድታሳልፍ ያደርግሃል።

አዎ! ማንም ያስባል፣ ማንም በውስጡ ነገሮችን ያሰላስላል፣ ግፋ ሲልም ይጨነቃል፣ ይሸበራል። ከልክ በላይ ማሰብን ትርጉም ብነሰጠው በአጭር አማርኛ ጭንቀት ማለት እችላለን። ሃሳብ ሃሳብን ሲወልድ፣ በሂደትም በመላምቶችና መሰረት አልባ ትርክቶች ሲታገዝ መዳረሻውን እንቅልፍ ነሺ ጭንቀት ሆኖ እናገኘዋለን። አብዝተን እናስባለን ነገር ግን ምንም ተጨባጭ ነገር አናመጣም፤ እናወጣለን እናወርዳለን ነገር ግን ምንም አይነት እርምጃ አንወስድም። በገዛ ፍቃዳችን አዕምሮችን ላይ ሸክም እናበዛለን፣ ህሊናችንን በሌለ ነገር ደጋግመን እንፈትናለን። ጭንቀት አዲስህ አይደለምና ከዚህ በፊት ተጨንቀህ ምን እንዳመጣህ አስታውስ፤ አብዝተህ ስላሰብክ ምን እንዳተረፍክ ተረዳ። ስለጭንቀትህ መጨነቅ አቁምና እርምጃ መውሰድ ባለብህ ልክ እርምጃ ውሰድበት። ባልተጨበጠ ሃሳብ ውስጣዊ ሰላምህን እንዳታጣ ሃሳቦችህን ጠብቃቸው።


ረፍዶ አያውቅም!

ራሳችሁን ከልክ በላይ አታስጨንቁ፣ አዕምሯችሁን አትወጥሩት፣ "የኔ ጊዜ አልፏል፣ አብቅቷልኛል፣ ከዚህ ቦሃላ ምንም ባደርግ አይሳካልኝም፣ አቅሜን ጨርሼአለሁ፣ የቀደመ ተነሳሽነቴ ተመልሶ አይመጣም።" ብላችሁ ራሳችሁን አሳስራችሁ አታስቀምጡ። በህይወት እስካላችሁ ድረስ የፈለጋችሁትን የማድረግ ጊዜ እንዳላችሁ አስቡ፣ እየተንቀሳቀሳችሁ እስከሆነ ድረስ በመረጣችሁት መንገድ የመጓዝ አቅሙ እንዳላችሁ እመኑ። በገዛ ፍቃዳችሁ ነገሮችን አታወሳስቡ፣ ፈልጋችሁ ለዝንጉነት ቦታ አትስጡ። በቀን ውስጥ ሁሉም ሰው 24 ሰዓት አለው፣ ይህ 24 ሰዓት ግን ለሁሉም እኩል ውጤትን አያመጣም። የጊዜያቸው ውድነት የገባቸው ሰዎች ጊዜን በገንዘብ ይገዛሉ፣ የጊዜያቸው ውድነት ያልገባቸው ሰዎች ደግሞ እንዲሁ በቀላሉ ያባክኑታል። ትናንት በየትኛውም አልባሌ ነገር ውስጥ አሳልፉ፣ ጊዜያችሁ እንዴትም ይባክን፣ ፍላጎታችሁም ሳይሳካ ይቅር አሁንም ግን በቂ ጊዜ አላችሁ። ያለፈ ጊዜ ውስጥ ምንም ተመላሽ ጊዜ የለም፣ በትናንተ ላይ አንዳች የሚፈፀም ተግባር አይኖርም። ለሁሉም እኩል በተሰጠው ጊዜ ምክንያት ተስፋ አትቁረጡ።

አዎ! ረፍዶ አያውቅም፤ እንደ ጨለመ ቀርቶ አያውቅም፣ ጀምበሯ እንዳዘቀዘች፣ ብረሃኗን እንደነፈገች፣ ዓለምም ፊቷን እንዳዞረች አትቀርም። በአምላኩ ድንቅ አድራጊነት ለሚያምን ሰው ሁሌም የበረከት በሮች ክፍት ናቸው። ዕዴሜው ጨመረ፣ ሰውነቱ ዛለ፣ ተነሳሽነቱ ቀነሰ፣ አቅመቢስ ሆነ፣ ሱስ አደከመው የሚባሉ ነገሮች አይሰሩም። ልባችሁ ብረሃን፣ ውስጣችሁ ንቁ፣ በፈጣሪ ስራ የምታምኑ ከሆነ ባለፈ ታሪክ ምክንያት ወደፊታችሁን ጨለማ አድርጋችሁ አትመለከቱም። ማድረግ ያለባችሁን ነገር አሁን አድርጉት፣ መጀመር ያለባችሁን ጉዳይ አሁን ጀምሩ። ለዓመታት ቀጠሮ ማብዛታችሁ ዛሬ እንደ ረፈደባችሁ እንድታስቡ አድርጓችኋል፣ ትናንተ ላይ ቸልተኛ መሆናችሁ ዛሬ ደካማና ልፍስፍስ አድርጓችኋል፣ ባለፈ ጊዜ አላማቢስ መሆናችሁ ዛሬ እጅጉን የተመሰቃቀለ ህይወት እንድትኖሩ አድርጓችኋል። ነገር ግን አሁንም አልረፈደም፣ ወደ ትክክለኛው መንገድ ለመመለስ፣ ጥፋታችሁን ለማረም፣ ቀና ብሎ ለመራመድ፣ የህይወት አላማን አግኝቶ ለመኖር በፍፁም አልረፈደም። "ረፍዶብኛል፣ ጊዜው የእኔ አይደለም።" ብላችሁ ከምትጨነቁ "ጊዜው የእኔ ነው፣ አሁንም በራሴ ላይ ስልጣን አለኝ፣ እርሱንም የምፈልገውን በማድረግ አሳያለሁ።" ብላችሁ ተግባሩን ጀመሩት።

አዎ! ጀግናዬ..! ያለፈን እድል እያሰቡ መቆዘም እድሉን አይመልስም። አባባሉ እንደሚለው "በድሮ በሬ ያረሰ የለም።" ማረስ ከፈለክ አዲስ በሬ ጠምደህ እረስ፣ የምርም ወደፊት መጓዝ ከፈለክ ትናንትህን ሽረህ ዛሬህ ላይ ተደገፍ። ታሪክህ በብዙ አስከፊ ነገሮች ተበላሽቶ ይሆናል አዲስ የተለየ ታሪክ የመፃፍ አድልህ ግን በእጅህ ነው። ነገሮችን በራስህ ላይ ማዳፈን አቁም፣ የነካሀው ሁሉ እንደሚሰበር፣ ያሰብከው ሁሉ እንደማይሳካ ማመን አቁም። በትናንት ማንነትህ ራስህን ወቀስክ አልወቀስክ፣ ጥፋትህን አጎላህ አላጎላህ፣ በራስህ ተበሳጨህ አልተበሳችሁ  ካንተና ከፈጣሪ በቀር ማንም ስላንተ ሃሳብና ጭንቀት ግድ እንደሌለው አስታውስ። ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር፣ በቀላሉ የሚረበሽ ሰው አትሁን፣ ተስፋህን አርቀህ ስቀለው፣ ስሜትህን ለማንም አታሳይ፣ የግል ዓለምህን ከልለው። አንተ ራስህ ላይ ከጨከንክ ማንም ሊያዝንልህ አይችልም፣ አንተ ልብህን ካስጨነካት ማንም ሊያዳምጣት አይችልም። ውጥረትህን ቀንስ፣ ጭንቀትህን ግዛ፣ ብዙዎች ረፍዷል ብለው በተዘናጉበት ወቅት አንተ ካለፈው ጊዜ በላይ በዛሬውና በነገው ተማምነህ ያለህን ጊዜ በስስት ተጠቀም።


ያለማቋረጥ አጥቃ!

ባለህበት ቆመህ ማን የሚፈልግህ ይመስልሃል? አምና ካቻምና ስትሰራ የነበረውን እየሰራህ ማን የሚመርጥህ ይመስልሃል? ባለፈው ስራህን እደምትሰራው አሁንም ብትሰራ እድገት የምታገኝ ይመስልሃል? በአረጀ አመለካከት፣ ባፈጀ እይታ የምትለወጥ ይመስልሃል? በየጊዜው ካልተሻሻልክ እንዲሁ እንደቀላል ህይወት የእድገትን እድል የምትሰጥህ እንዳይመስልህ። ማንም በአጋጣሚ ህይወቱን የቀየረ፣ ኑሮውን ያሻሻለ፣ ደረጃውን የጨመረ፣ ከከፍታው የደረሰ ሰው የለም። እያንዳንዱ ነገር የብዙ እንቅልፍ አልባ ምሽቶች ውጤት ነው፤ እያንዳንዱ ከፍታ ክህሎትን ከማሻሻል ቦሃላ የመጣ ነው፤ እያንዳንዱ እርካታ ጨክኖ እራስን ከመግዛት ቦሃላ የተከሰተ ነው፤ የትኛውም ስኬት ለእራስ ከሚሰጥ ቦታና ፍቅር የሚመነጭ ነው።

አዎ! ክህሎትህን አሳድግ፤ እውቀትህን ጨምር፤ መረዳትህን አስፋ፤ ግንዛቤህን አጎልብት። አቋም ይኑርህ፣ እራስን የማስቀደም አቋም፣ ለእራስ የመታገል አቋም፣ እራስን ነፃ የማውጣት፣ እስከጥግ የመፋለም፣ ዋጋ የመክፈል፣ እራስን የመግዛት፣ ህመምን፣ ስቃይን፣ መከራን የመቻል አቋም፣ በእሾህ ጋሬዛ ውስጥ፣ በማያልቁ መሰናክሎች መሃል፣ እረፍት በማይሰጡ ትቺቶች ውስጥ፣ አበርታች፣ አጋዥ፣ ደጋፊ በሌለበት መንገድ መሃል በፅናት የመጓዝ አቋም ይኑርህ። 4030 ፑል አፕ በ17 ሰዓት ከ16 ደቂቃ በመስራት የአለምን የፑል አፕ ሪከርድ (world's pull up record) በእጁ ያስገባው፣ 5000KM መሮጥ የቻለውና የአለማችንን የምንጊዜውም ጠንካራው ሰው የተባለው ደቪድ ጎጊንስ (David Goggins) ስለ አዕምሯዊ ጥንካሬ ሲናገር እንዲህ ይላል፦ "አንድን ነገር ለማድረግ ከመረጥከው አጥቃው።"

አዎ! ያለማቋረጥ አጥቃ! ፋታ ሳትሰጥ ስራበት፣ ቀን ከሌሊት እራስህን ገንባበት፣ ያለምንም የአቋም መዋዠቅ እስከመጨረሻው ታገለው፤ እስክትነግስበት በፍፁም እንዳታቆም። እራስህን ከወደድከው ዋጋ ክፈልለት፤ ለእራስህ ክብር ካለህ ጨክንበት፤ የምርም ደስታህን የምትፈልግ ከሆነ፣ በእርግጥ እርፍት እንዲያደርግ የምትመኝ ከሆነ እያወክ ስቃይ ውስጥ ክተተው፣ ያለማቋረጥ አስተምረው፣ አሰራው፣ አሳድገው። ምንም ዋጋ ሳይከፍሉ ዋጋ ያለው ትርፋማ ህይወት መኖር አይቻልም፤ እየቀለዱና እያሾፉ ተመራጭ ተፈላጊ ሰው መሆን አይቻልም። ለመለወጥ ጊዜ አትውሰድ፤ ለእድገትህ ቀጠሮ አታብዛ፤ ከፍታህን አታዘግየው፤ ስኬትህን ወደኋላ አትግፋው። "የመጣው ቢመጣም ለእራሴ አላንስም፤ ምንም ማድረግ ቢጠበቅብኝ ማድረግ ያለብኝን አድርጌ ነፃነቴን እጎናፀፋለሁ" የሚል የማይናወፅ አቋም ይኑርህ።


ከራስህ አትሽሽ!

ራሳችንን በማንቀበልበት ጊዜ ሳናስበው ራሳችንን ጥለን ወደ ሌላኛውና የእኛ ወዳልሆነው ማንነት እንድንሄድ ይገፋፋናል፡፡ በዚህ አይነት ተጽእኖ ውስጥ እንድንወድቅ የሚያደርጉን ሁኔታዎች በዙሪያችን ሞልተዋል፡፡ እነዚህ “ጥሪዎች” መነሻቸው በውስጣችን የሚገኘው ተቀባይነት የማግኘትና ራስን የመቀበል ስነ-ልቦናዊ  ፍላጎት ነው፡፡

በውስጣችን ያለውን የመወደድና ተቀባይነት የማግኘት ፍላጎት ለማሟላት ብዙ ነገሮችን ለማድረግ ይቃጣናል፡፡ ሳናስበውም ራሳችንን ማለቂያ የሌለው ጉዞ ውስጥ ገብቶ እናገኘዋለን፡፡ ይህ እንዳይሆን በውስጣችን ያሉትን ስነ-ልቦናዊ ፍላጎቶች በማወቅ ትክክለኛ የመፍትሄ መንገድ መፈለግ አለብን እንጂ ራስን ባለመቀበል ስቃይ ውስጥ መማቀቅ የለብንም፡፡ የሚከተሉትን ከራሳችን እንድንሸሽ የሚያደርጉንን ስውር ስነ-ልቦናዊ ምክንያቶች እንመልከት፡፡

1. ተቀባይነት ፍለጋ
አንዳንድ ሰዎች ቤተሰባቸውን ለማስደሰት፣ ልባቸውን የሳበው ፍቅረኛ እንዲቀበላቸው፣ እንዲሁም በአንድ ቡድን ውስጥ ተቀባይነት ለማግኘት ራሳቸውን ለመለወጥ ሲጣጣሩ ይታያሉ፡፡ የዚህ አይነቱ ራስን የመለወጥ ሙከራ ግን መጨረሻው ድካምና “ራስን ማጣት” ነው፡፡ ብቸኛው መፍትሄ ራስን ተቀብሎና ሆኖ መኖር ነው፡፡

2.ዘመናዊነትን ፍለጋ
የዘመኑን ፋሽን፣ የዘመኑን ቁመናም ሆነ የዘመኑን የንግግር ዘይቤ ሁሉ ተከታትለንና አውቀንበት መኖር ብንችል መልካም ነበር፡፡ ሁኔታው ግን ያን ያህል ቀላል አይደለም፡፡ “ዘመናዊ ሰው መስዬ ካልታየሁ ተቀባይነት አላገኝም” ከሚለው ማለቂያ የሌለው የውስጥ ጥማት ከሚመነጭ ትግል መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው፡፡

3.ስኬታማ መስሎ የመታየት ጥማት
አንዳንድ ሰዎች በተለያዩ የኑሮ ዘርፎች ስኬታማ መስሎ ለመታየት የማያደርጉት ጥረት የለም፡፡ ስኬት ግን የታይታና የአንድ ጊዜ ክስተት ሳይሆን ሂደትና የኑሮ ዘይቤ ነው፡፡ የስኬት መነሻው መሆን ያለበት በመጀመሪያ ራስን ሆኖ መገኘት ነው፡፡ በመቀጠልም ባመኑበት ጎዳና ወደ መሰማራትና ራስን ወደ ማሻሻል ሊያድግ ይገባዋል፡፡


ለመውደቅ አትሞክርም!

ትሞክራለህ ትወድቃለህ፣ ድጋሜ ትሞክራለህ ድጋሜ ትወድቃለህ፣ አሁንም ትሞክራለህ አሁንም ትወድቃለህ፣ የውድቀትህ ድግግሞሽ ሙካራህን አያቆምም በምትኩ እራስህን ወደማወቅ፣ እራስህን ወደማግኘት ያቀርበሃል። የጉዞህ አካል ውድቀት፣ ስብራት፣ ህመም፣ ስቃይ ነው። ሃሳብህ መሻገር እንጂ ወድቆ መቅረት አይደለም፣ ውጥንህ ከፍ ማለት እንጂ ባሉበት መቅረት አይደለም፣ ፍላጎትህ መሻሻል እንጂ ዘወትር ተመሳሳይ ህይወት መኖር አይደለም። ስለዚህ የመረጥከውን ትጀምራለህ፣ ትሞክራለህ፣ ትወድቃለህ ደጋግመህም ትነሳለህ።

አዎ! ጀግናዬ..! ለመውደቅ አትሞክርም፤ ለማቆም አትጀምርም፤ ተንኮታኩቶ ለመቅረት አትጥርም። የጅማሬህ ውጥን መጨረሻ አለው፣ የሙከራህ ጥንስስ ግብ አለው። ውድቀትህ አንድ ቀን እንደሚያበቃ ታውቃለህ፣ በእያንዳንዱ ሙከራህ የምታካብተው ክህሎት፣ የምታሻሽለው ስጦታ አለ። ህልምህን እንዳትኖር የሚያግድህ ውድቀትህ አይደለም፣ ስብራትህ አይደለም፣ የመንገዱ ስቃይም አይደለም፤ የውድቀት ፍራቻህ፣ የመገፋት ስጋትህና የህመሙ ሽብር ነው። ሃሳብህ ትልቅ ከሆነ በትንሹም ቢሆን መውደቅህ፣ መቃጋጥህና በእራስህ ማዘንህ አይቀርም። ዋናው ግን እርሱ አይደለም፤ የሃሳብህ ትልቅነት የሚታወቀው ለስኬቱ ብለህ በምትከፍለው ዋጋ ነው፤ በምትጋፈጠው ተግዳሮት ልክ ነው።

አዎ! ትልቅ ህልም ይኑርህ፣ ግዙፍ ራዕይ አንግበህ ተነስ፣ ሁሉን አቀፍ እቅድ ይኑርህ፣ ነገር ግን እርሱን ለማሳካት እስከምን ድረስ ትጓዛለህ? እስኬት ትፋለማለህ? ለእርሱ ብለህ ስንቴ ለመሳሳት፣ ስንቴ ለመታረም፣ ስንቴ ለመውደቅ፣ ስንቴስ ለመነሳት ዝግጁ ነህ? ብዙዎች ብቁ ያልሆኑበትን ህልምህን መኖር ጀምረሃል፤ ጥቂቶች የሚሻገሩትንም ውድቀት ትሻገረዋለህ፤ ብዙዎች የሚፈሩትንም ትቺት፣ ዘለፋና ስህተትም በድፍረት ትጋፈጠዋለህ። ስለወደክ አታቆምም፤ ስተወቀስክ አትረታም፤ ስለተሳሳትክ አትሸነፍም። እስክታሸንፍ አታቆምም፤ ግብህን እስክትመታ፣ ህልምህን እስክታሳካ ሸብረክ አትልም። ከምንም የላቀ ግብ፣ ከምንም የሚበልጥ ራዕይ አለህ። ካንተም በላይ ብዙዎችን ቀያሪው ሃሳብህ አብሮህ አያረጅም፣ ይዘሀው አታልፍም፤ ትተጠቀምበትና ትጠቅምበት ዘንድ ግዴታ ነው።

አዎ! ሙከራህ፣ ጅማሬህ፣ ጥረትህ ለመውደቅ ብሎም ወድቆ ለመቅረት አይደለም። ከውድቀትህ ለመማር፣ ዳግም ለመነሳት፣ ስህተቶችንም ለማረም ነው። በምትፈራው ውድቀት አትሸበር፣ በስህተት ስጋት አትታሰር፤ ለእርማት፣ ለመሻሻል፣ ለማደግና ለመቀየር ሁሌም ዝግጁ ሁን።


ከባዱ ያከብድሃል!

ከባድ ሁኔታዎች ጠንካራ፣ ብርቱና አይበገሬ ሰዎችን ይፈጥራሉ። ብርቱና ጠንካራ ሰዎችም ቀላል ሁኔታን ይፈጥራሉ፤ ቀላል ሁኔታዎችም ልፍስፍስና ቀላል ሰዎችን ይፈጥራሉ፤ ልፍስፍስና ደካማ ሰዎችም ከባድ ጊዜያትን ይፈጥራሉ። ብስለትህ፣ ጥንካሬህ፣ ብርታትህ በቀላልና ከፈተና በፀዳ ሁኔታ ውስጥ ሊፈጠር አይችልም። እንቅፋት የሚገጥምህ ስለተንቀሳቀስክ ነው፤ የምትወድቀው፣ የምትነሳው እዛው የነበርክበት ስፍራ ስላልተቀመጥክ ነው። ቀና ማለትህ ብዙ ነገሮችን ያስመለክትሃል፤ ብዙ መሞከርህም የተለያዩ የሚሳኩና የማይሳኩ መንገዶችን ያሳይሐል።

አዎ! ጀግናዬ..! በፈታኙና በከባዱ ሁኔታ ውስጥ ተፈጥረህ፣ ተሰርተህ፣ በርትተህ፣ ጠንክረህ ወተሃልና ከባድ፣ አስጨናቂና አስቸጋሪ ሁኔታዎችን መውቀስ፣ መተቸት፣ ማማረር አይጠበቅብህም። ለውጥህ በከባድ ሁኔታ ውስጥ ነው፤ እድገትህ ነገሮች ስላልተሟሉልህ ነው። ኑሮ ስለተወደደብህ የተሻለ ለመስራት፣ የእራስህን ስራ ለመጀመር፣ የተሻለም ለማግኘት ትጥራለህ፤ የሚደርስብህን እያንዳንዱን በደል ተቋቁመህ በእራስህ ለመቆም በመሞከረህ ጥንካሬን ወደማግኘት ትመጣለህ። በብርታትህ ልክ ነገሮችንም ማቅለል ትጀምራለህ፣ የተሻሉ ሁኔታዎችን ትፈጥራለህ፣ ለሌሎች የመድረስ አቅምህን ታጎለብታለህ፤ እራስህን በማብቃት የወገንህ መመኪያ፣ የወዳጆችህ መጠለያ ትሆናለህ።

አዎ! ከባዱ ያከብድሃል፤ ቀላሉም ያቀልሃል። በህይወትህ ከችግርና ከፈተና በፀዳህ ቁጥር የተሻለና ብርቱ ሰው የመሆንህ እድል እየመነመነ ይመጣል። ለውጥ በሌለው፣ ምንም በማትጨምርበት፣ ሙቀት ቅዝቃዜ በሌለበት፣ ከፍታ ዝቅታ በማይታይበት፣ ደረጃው በማይቀንስ በማይጨምር መካከለኛ ( Mediocre ) የሆነ ህይወትን ትመራለህ። ለመቀየር ምክንያት ታጣለህ፣ ለማደግ የሚያስገድድህ ነገር አይኖርም፤ ለመቅረፍ የምትጣጣረው፣ በተሻለ ሁኔታ የሚያታግልህ፣ የሚያሰራህ፣ የሚያለፋህ፣ የሚያተጋህ ከባድ ሁኔታ አይኖርም። በፈተናዎችህ መሐል እራስህን አሳድግ፤ በአስጨናቂ ጊዜያት ውስጥ እራስህን አግኝ፤ በከባድ ሁኔታዎች መሐል ብርቱውን አንተ ፍጠር፤ ከተጎዳህበት አጋጣሚ በላይ ለመሆን እራስህን አጠንክረህ፣ አሻሽለህ፣ አጎልብተህ ተገኝ።


እንደ ቦታቸው ተረዳቸው!

ከጀርባህ ሆነው በሚያወሩ፣ በስኬትህ በሚቀኑ፣ በከፍታህ በሚበሳጩ፣ ተግባርህን በሚያቃልሉ ሰዎች በፍፁም አትናደድ። ምክንያቱም ስሜታቸው እንጂ ውስጣቸው መድረስ በሚፈልገው ስፍራ ሊናደድ አይችልምና። ምክንያቱም የንግግራቸው ይዘት በእራሱ ካንተ እንዳነሱ፣ ከኋላህ እንደቀሩ፣ ከአቅማቸውን እንደጎዱ አመልካች ነውና። ማንም ሰው ያለምክንያት ከጀርባ ሆኖ የሌላውን ሰው ስም ለማጥፋት አይሞክርም፤ በሌላው ውድቀት ለመደሰት አያኮበኩብም፤ በሌላው ችግርና ፈተና የእራሱን ህይወት ለማሻሻል አይሯሯጥም። በእራሱ የሚተማመን፣ በሳልና ብልህ ሰው የወንድሙ ደስታ ደስታው ነው፤ የጓደኛው ስኬት ስኬቱ ነው፤ የወገኑ ሰላም፣ የህዝቡ እረፍት ሰላሙ፣ እረፍቱ ነው። ማንም ክፉ የሚያስብ፣ ከኋላ ቢዶልት፣ ደባ ቢያደባ ከጀርባ ሆኖ የሚያሸንፈው ትግል አይኖርም። ስም በማጥፋት፣ ገፅታን በማጠልሸት፣ ጫናዎችን በማብዛት የእርሱ ስም የሚገነባ፣ ገፅታው የሚስተካከል ቢመስለውም ቅሉ ግን የተዛባው እይታው ለከፋ ውድቀት ይዳርገዋል።

አዎ! ጀግናዬ..! እንደ ቦታቸው ተረዳቸው! ወዳጅህ መስለው የጠላት ስራ የሚሰሩብህ፣ በልብ ጓደኝነት ሰበብ ከጀርባ የሚያደቡብህ፣ አጀንዳቸው ሁሉ ያንተ እድገትና ለውጥ በሆነባቸው ሰዎች አትበሳጭ፣ አትዘን፣ አትናደድ። ክፉዎች ሁሌም ስፍራቸው ከኋላ ነው፤ ተንኮለኞች ዘወትር ምልልሳቸው በዝቅታ ነውና እንደ ቦታቸው ተረዳቸው። የምቀኝነት እሳቤ የውድቀት መንገድ ነው፤ የንፉግነት ማንነት የትንሽነት ልክ ነው። መልካምነት ልብን ይጠይቃል፤ ሰው መሆን ይፈልጋል። ለእራስ እንዲሆን የሚመኙትን በሰው ሲመለከቱ ከኋላ ከመንሾካሾክና በድብቅ ክፋትን ከመዶለት ይልቅ በግልፅ የደስታው ተካፋይ መሆን የመልካምነት መለኪያ ነው። ልበ ቀና ደግ ሰው ሃሳቡ በእራሱ በጎነትን ያድለዋል።

አዎ! በወዳጅህ ደስታ ተደሰት፣ ከስኬቱ የምስራች ተቋደሰው፣ የከፍታውን ብስራት አካፍልለት። ትልቅነት በቅንነት፣ ብስለትም በአጋዦነት የሚገለፅ ነው። አርቆ የሚያስብ፣ ህልመኛና ባለራዕይ ሰው ትልቅ ስፍራ በደረሱ፣ ስኬትን በተቆናጠጡ፣ ከከፍታው በደረሱ ሰዎች አይቀናም፤ አይናደድም፤ አይበሳጭም። መንገዳቸውን መማሪያ፣ ስኬታቸውንም እንደ መነቃቂያ ይወስደዋል። ሁሉም ታስቦ የሚደረግ ነገር የእራሱ በቂ ምክንያት አለው። ሰዎች ያለምክንያት በለውጥህ አይበሳጩም፣ በእድገትህ አይናደዱም፣ በደስታህ አይቃጠሉም። አስከፊው ከፋት የስሜት ጭካኔ፣ የስሜት ደባ፣ የስሜት ጥላቻ ነው። ተንኮልን ከውስጡ የሚያወጣ፣ ጥሎ ለማለፍ ሁሌም የሚሯሯጥ፣ ሰው ሲያልፍለት አይኑ የሚቀላ ሰው አደገኛ ነውና ተጠንቀቀው። ግብህ ላይ ካተኮርክ፣ ልዩነት መፍጠር ከጀመርክ፣ ብዙዎች የሚመኙትን ነገር እጅህ ወደማስገባት ከተጠጋህ የኋላ ጫናና ክፋቶች ይበዛሉና ለእራሰህ ታመን፣ በጅማሬህ ቀጥል፣ ጫናዎችን ተጋፈጥ፣ ጥላቻውንም ጥልህ እለፍ።


ማን ይናገርልህ?

ማንም የማያውቀው ነገር ግን አንተ የምታውቀው የግል ክህሎት፣ የግል ችሎታ አለህ፣ አውጥተህ ለመጠቀም ጊዜ ትጠብቃለህ። ስለራስህ እንድታወራ መድረክ ቢዘጋጅልህም ትህትናን በመሰለው የበታችነት ስሜት ስለእራስህ ለማውራት ታፍራለህ፤ ትፈራለህ። እራስን ማድነቅ፣ ስለራስ ብርታትና ጥንካሬ ማውራት፣ የእራስን መልካም ጎን ዘወትር በአውንታዊነት ማንሳት ግብዝነት ወይም እራስ ወዳድነት ይመስልሃል። አንዳንዴ ሰው እንዲያወራልህ የምትጠብቅበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል፤ ሰው የሚያወራልህ ግን ስላደረክለት ወይም ካንተ ስላገኘው ነገር እንጂ ስላንተ ማንነት ሊያወራልህ አይችልም። ስለሆነ ሰው አውርተህ አትጠግብም ይሆናል፤ ስለመልካምነቱ፣ ስለቅንነቱ፣ ስለጥንካሬው፣ ስለጨዋታ አዋቂነቱ፣ ስለመረዳት አቅሙ። ስለራስህስ አውርተህ የማትጠግብበት፣ መስክረህ የማትረካበት ሁኔታ ቢፈጠርስ ሊሰማህ የሚችለውን ስሜት፣ ልታገኘው የምትችለውን በእራስ መተማመን አስበው።

አዎ! ጀግናዬ...! ነውር አሳፋሪ የሚባሉት የእራስ አገላለፅ ዘይቤዎች ልኬት አላቸው። ማንም የሌላውን መብት ሳይጋፋ፣ የሌላውን ስሜት ሳይነካ ስለእራሱ መናገር ቢችል ነውር ሊባል አይችልም፤ እራስን መግለፅ በእራሱ ጥበብ ነውና። ሰው ስለእራሱ ማውራት አለበት፣ ለለእራሱ መመስከር ይኖርበታል፣ ለእራሱ ሊሟገት ይገባል። ካልሆነ ግን ማንም ስለእርሱ የሚያውቀውን ትንሽ ነገር እንኳን ሊመሰክርለት አይችልም። አንተ ስለራስህ ካልተናገርክ፣ ለእራስህ ካልወገንክ፣ ስለእራስህ ካላወራህ ማን ያውራልህ? ማን ይናገርልህ? ማን ይወግንልህ? ማንስ ይደግፍህ? ለእራስህ ኩራት መሆን ካልቻልክ ማንም ኩራት የሚሆንህ ሰው የለም። በትህትናህ ሰዎችን ልታገለግል ትችል ይሆናል እራስህን ግን አሳልፈህ አትሰጣቸውም፤ ስላንተ የማያውቁትን ለማሳወቅ አትሸማቀቅም፤ ስለራስህ ለመናገር አታፍርም።

አዎ! የምታወራው ስለሌላ ሰው ሳይሆን ስለራስህ ነውና አትሸማቀቅ፤ የምትመሰክረው ስለምታውቀው ማንነት ነውና ሃፍረት አይያዝህ፤ የምታስረዳው እራስህን ነውና በእራስ መተማመን አይለይህ። ስለ ብዙ ነገር ብዙ አውርተናል፤ ስለማይመለከተን ብዙ ተንትነናል፤ ስላማናውቀው ብዙ አሽቃብጠናል፤ ስለምናውቀው እራሳችን በልበ ሙሉነት ብናወራ ነውርነት ሊኖረው አይችልም። ከስምህ በላይ ስለእራስህ የምትናገረው ነገር ያስፈልግሃል፤ ከስራህ በዘለለ የሚመሰክርልህ ሁነኛ ጠበቃ ያስፈልግሃል። እራሱን መግለፅ የማይችል፣ ስለማንነት ለመተንተን የሚሸማቀቅ፣ እሱነቱን በጉልህ ለማስረዳት የሚያፍር ሰው እራስን ስለማወቅና እራስን ስለመግለፅ ሁነኛ ጥቅሞች በቅጡ ያልተረዳ ሰው ነው። ስለእራስህ ስላወራህ የሚከስህ ሰው የለም፤ እራስህን መግለፅ ስለቻልክ፣ ለእራስህ ያለህን ፍቅር፣ ለእራስህ በምትሰጠው አክብሮትና ቦታ ምክንያት ለፍርድ የሚያቆምህ የለም። በነፃነት ስለእራስህ አውራ፤ እራስህን አነቃቃው፤ አበረታታው፤ አወድሰው። አንተ አንተ ለመሆንህ የማንንም ማረጋገጫ አልጠበክምና ስለአንተ እንዲያወራልህም ማንንም አትጠብቅ።


እቀጥላለሁ!

ከራስ ጋር ንግግር፦ "ላሸንፈው የማልችለውን፣ ከፊቱ እንኳን መቆም የሚከብደኝን፣ በፍፁም የማልችለውን ሰው እስካገኘው ድረስ መስራቴን እቀጥላለሁ፣ መጓዜን እቀጥላለሁ፣ መድከም መታገሌን እቀጥላለሁ። ሁሌም ጉዞ ላይ ነኝ፣ ሁሌም መንገድ ላይ ነኝ፣ ሁሌም እየታተረኩ ነው። ፍላጎቴ አንድና አንድ ብቻ ነው። እርሱም አይበገሬውን ጠንካራ ሰው መፍጠር። እስካሁን ያንን ሰው ስለመሆኔ እርግጠኛ አይደለውምና አሁንም ጥረት ላይ ነኝ፣ በረፍት አልባው መንገድ እየተጓዝኩ ነው። እርግጥ ነው ድካም አለው፣ እውነት ነው ይሰለቻል፣ ይታክታል ነገር ግን ሌላ ምርጫ የለውም፣ ነገር ግን ከዚህ ውጪ ቀላል መንገድ የለውም። ከማየው ሰው ጋር ሁሉ እየተወዳደርኩ ራሴን ዝቅ ማድረግ አልፈልግም፣ የሰማውትን ሁሉ እያመንኩ መከተል አልፈልግም። ማንም ሰው ያለውን የፈለገውን ሰው የመሆን ምርጫ ተጠቅሜ ራሴን እሆናለሁ የተሻለውን ግሩም ማንነትም እፈጥራለሁ። ለራሴ የመታመን ምርጫ ሳይሆን ግዴታ አለብኝ፣ ራሴን የማክበር ምርጫ ሳይሆን ግዴታ አለብኝ።

አዎ! እቀጥላለሁ! ደክሞኛል ግን አላቆምም እቀጥላለሁ፣ ደብሮኛል ነገር ግን አላቆምም እቀጥላለሁ፣ የማየው የምሰማው ነገር ደስ አይልም ቢሆንም አሁንም ጉዞዬ ላይ ነኝ። ወደፊት ስጓዝ ምን እንደሚገጥመኝ አላውቅም የመጣብኝን ለመቀበል ግን ዝግጁ ነኝ፣ በህይወት እስካለሁ ድረስ ከፈጣሪ ጋር መቀየር ማደግ እንዳለብኝ አምናለሁ ስለዚህ በፈተናዎች መሃልም ቢሆን ጎልቶ መውጣት የሚችል ብርቱ ማንነት መገንባት እንዳለብኝ አውቃለሁ። ያለሁት ቀላል ወይም አጭር መንገድ ላይ አይደለም፣ የጀመርኩት በአጭሩ የሚቋጭ፣ በትንሽ ጥረትም የሚሳካ እቅድ አይደለም። መሆን ያለብኝን ሰው የምሆነው ራሴን ሰጥቼው ነው፣ መድረስ የምፈልገው ስፍራ የምደርሰው መክፈል ያለብኝ ዋጋ ከፍዬ ነው። ብዙ ወዳጅ አለኝ ከራሴ የሚበልጥ ወዳጅ ግን የለኝም፣ ብዙ የሚያስብልኝ ሰው አለ ከራሴ በላይ የሚያስብልኝ ሰው ግን የለም እንዲኖርም አልፈልግም። ለራሴ መሆን ሳልችል ዓለም በእኔ ላይ ብታብር ምንም አይገርመኝም። ምርጥ ነገር እንደሚገባኝ አስባለሁና ምርጥ ሆኖ መገኘቱ የእኔ ስራ ነው። ራስን በመሆን ውስጥ ቀላል የሚባል እርምጃ የለምና ሁሌም ራሴን እያበረታው እጓዛለሁ፣ የምመኘውን ብርቱ ሰውም እፈጥረዋለሁ።"

አዎ! ጀግናዬ..! ሰው እንዲመክርህ አትጠብቅ። ማንም ሳይሰማ ማንም ሳያይ ራስህን በሚገባ ምከረው። ከፍ ማለት እንዳለብህ ካመንክ ከፍ የሚያደርግህ ሰው ሳይሆን አንተ ነህ፣ መቀየር ከፈለክ የሚቀይርህ ሰው ሳይሆን አንተ ራስህ ነህ። የትኛውም ራስን የማብቃት፣ በአስተሳሰብ፣ በስሜትና በገንዘብ ብቁ ሆኖ ለመገኘት የመጣር መንገድ አልጋ በአልጋ አይደለም። ታጣለህ ታገኛለህ፣ ይሳካልሃል አይሳካልህም፣ ትወድቃለህ ትነሳለህ፣ ታተርፋለህ ትከስራለህ። ተመሳሳይ ገቢ ሲኖርህ ተመሳሳይ ህይወት እንደምትኖረው ሁሉ ገቢህም የተለያየ ሲሆን ህይወትህም በብዙ መንገድ የተለያየ ሊሆን ይችላል። ሁሉም ነገር ሊሰለችህ ይችላል ነገር ግን እንድታቆም ሊያደርግህ አይገባም፣ ብዙ ሰው ላይረዳህ ይችላል ነገር ግን ወደኋላ ሊመልስህ አይገባም። ምንም አደረክ ምንም ገጠመህ ምርጫህ አንድ ነው። የተሻለ ሰው መሆንና መሆን ብቻ ነው። የመረጥከውን ሰው ለመሆን ከማንም ጋር አትደራደር፣ የፈለከው ስፍራ ለመገኘት የማንንም ይሁኝታ አትጠብቅ። ሁሌም ራስህን መስራትህን ቀጥል፣ የምትመኘውን ማንነትም መገንባትህን ግፋበት።


ሰው ብዙ ይላል!

ስላንተ ምንም ሊባል ይችላል፣ ማንም ምንም ሊል ይችላል። የሰዎች ስም ማውጣትና ስላንተ ተግባር ደጋግሞ ማውራት የሚያሳስብህ ከሆነ አንድም የሚያወሩብህን ሰዎች ተከታትለህ አፋቸውን አዘጋ አሊያም አንተ የምታደርገውን አቁም። እነዚህ ሁለቱም እርምጃዎች ትርፍ እንደሌላቸው ደግሞ ጠንቅቀህ ታውቃለህ። ስንቱን አፉን ታዘጋለህ? እስከመቼስ ለሚያወሩብህና የማይሆን ስም ለሚለጥፉብህ ሰዎች ብለህ እራስህን ትገድባለህ? አንድ ነገር አስታውስ ማንም ሰው ያላንተ ፍቃድ አናትህ ላይ መውጣት አይችልም፤ ማንም ሰው ያላንተ ይሁንታ ከግብህ ሊያቆምህ፣ አላማህን ሊያስትህ አይችልም። ያንተ ተሽሎ መገኘት፣ ያንተ እራስህን መሆን፣ ያንተ በእራስህ ቀለም መድመቅ፣ መፍካት፣ መዋብ ሊያስቀናው፣ ሊያበሳጨው፣ ሊያናድደው ይችላል፤ እርሱ ግን ያንተ ችግር ያንተ ጉዳይ አይደለም። ሰው የፈለገውን ማየት ይችላል፤ በመረጠው መንገድ መጓዝ ይችላል፤ ያሰኘውን መናገር ይችላል። ችሎታውን ለክፉና መጥፎ ነገር ከተጠቀመውም ነፃ ፍቃዱ ነውና ምንም ማድረግ አይቻልም።

አዎ! ጀግናዬ..! ሰው ብዙ ይላል! በተለይ ደግሞ የሚቀናብህ፣ ያንተን ቦታ አብዝቶ የሚመኝ ነገር ግን አንተ የምታደርገውን ለማድረግ፣ ያለህበት ስፍራ ለመገኘት ያልቻለ ሰው ስላንተ ከማውራት አያርፍም። ብዙ አስተያየት መስጫ ሰጥኖችን ተመልከት ስድብ፣ ነቀፋ፣ ጥላቻ፣ ትቺት ይበዛባቸዋል። በሚያስገርም ሁኔታ የነዚህ ስድብና ነቀፋ አስተያየት ሰጪዎች በህይወታቸው ምንም ጠብ የሚል ነገር ማድረግ ያልቻሉ፣ ማንነታቸውን ያልተረዱ፣ በውስጣቸው ያለው እምቅ ሃይል ያልገባቸው ምስኪን ሰዎች ናቸው። የሚሰሩ ሰዎች ላይ የጥላቻ ቃል በመወርወር፣ መንገዳቸው ላይ እንቅፋት በማስቀመጥ፣ እየተከተሉ በስድብ በማከናነብ የእነርሱ ህይወት የሚቀየር ይመስላቸዋል፤ ማንም ከእነርሱ በልጦና ተሽሎ እንዲገኝ አይፈልጉም። እነርሱም መሔድና ረጅም ርቀት መጓዝ እየቻሉ የሚሔደውን ጎትተው ለማስቀረት ይጥራሉ።

አዎ! ማለት የሚፈልግ ያሰኘውን ይላል፤ የሚናገርም ይናገራል። ነገር ግን አለም የተቀየረችው በሚናገሩት ሳይሆን በሚያደርጉት ሰዎች ነው። የሚዘልፍ፣ የሚተች፣ የሚያጠለሽ፣ የሚሳደብ ሰው ሁሉ የሚችለውን ብቻ ማድረግ ቢችል አለም በብዙ እጥፍ ባደገችና በተመነደገች ነበር። ማንም እቅድህን አያውቅም፣ ቀጣይ እርምጃህ አይገባውም። ስታደርገው ብቻ ማወቅ የሚገባው ከለ በተግባር አሳየው። ከተግባርህ ምላስህን አታስቀድም። ስንቱ ሊጠልፍህ በመንገድ እንደሚጠብቅህ አስተውል። ያለምክንያት፣ ያለምንም ትርፍ፣ አንድ አይነት ሆኖ የወረደን ህይወት ለመኖር ብቻ ሰው ለሰው አይተኛም። አንተም ለእራስህ ብለህ አትተኛና። ብዙ የሚቃወሙህ ቢኖሩም ጥቂት የሚደግፉህ፣ በሒደትም የሚበዙ፣ የሚያበረቱህ ሰዎች አሉና በእራስህ ተስፋ እንዳትቆርጥ። የተባለው ይባል አንተም የምታደርገውን አድርግ፤ የሚገባህ ስፍራ ተገኝ፤ በሚመጥንህ ፍጥነት ተጓዝ፤ ግብህን ምታ፤ ህልምህን ያዝ።


አታቆመውም!

ያልተመቸህ ነገር ይኖራል የህይወትን ፍሰት ግን ማዘግየት አይችለም። ህይወትም ስላልተመቸህ ነገር የምትሰማበት ጊዜ የላትም። ለሰበብ አስባቡ፣ ምክንያት ለመደርደሩ፣ አጀንዳ ለማብዛቱ ያባከንከው ጊዜ የሚመለስ ከመሰለህ እንዳትሳሳት የሰራህበት፣ ያልሰራህበት፤ ያመሰገንክበት ያማረርክበት፤ የወደክበት የተነሳህበት ጊዜ በፍፁም የሚመለስ አይደለም። ዛሬ ዛሬ ነው፤ አሁንም አሁን ብቻ ነው። ህይወትም በዛሬና በአሁን ውስጥ ብቻ ነች። ምንም ነገር ሊያሳስብህና ሊያስጨንቅህ ይችላል፣ ከአሁን ቅፅበት ውጪ ከሆነ ግን የማስጨነቅና ሰላምህን የመንሳት ስልጣን የለውም። ሁሉም እንደምታስበው ቢሆንልህ የት ነበርክ? ፍራቻህ ቢጠፋ፣ ጭንቀትህ ቢወገድ፣ ስጋት ቢርቅህ፣ የምትፈልገው ሁሉ ቢሟላልህ ህይወትህ ምን ይመስል ነበር? በውስጠ ህሊናህ ልትኖረው የምትችለውን ህይወት ተመልከተው፤ የሚሰማህን ስሜት አዳምጠው፤ ደስታህንም አጣጥመው።

አዎ! ጀግናዬ..! አታቆመውም! እያማረርክ ጊዜውን አታቆመውም፤ ሰበብ እያበዛህ ኑሮ ውድነቱን አታቀለውም፤ እየተጨነክ የሆነውን እንዳልሆነ አታደርገውም፤ በስጋት እየኖርክ ፍራቻህን መሻገር አትችልም። ዋጋቸው የበዛ የድል ፅዋዎች ወዳንተ ይመጣሉ፤ ልፋት የሚጠይቁ ስራዎች ለውጤት ያበቁሃል። ስለለፋህ ሳይሆን ስላሸነፍክ ይጨበጨብልሃል፤ ጥረትህ ሳይሆን ውጤትህ ያሸልምሃል። ምንም ብታደርግ የሚቆም የህይወት ፍሰት፣ የጊዜ ሂደት አይኖርም። በአንድ ህይወት ብዙ ነገር ታያለህ፤ በአንድ አለም ለስንት ነገር ትበቃለህ። የቻልከውን ችሎ መገኘት ተዓምረኛ ወይም አስደናቂ ላያስብልህ ይችላል፤ ነገር ግን ስሜት በሚሰጥህ ምልልስ ውስጥህ እያደክ ከሆነ ግን ማስገረምህና ማስደነቅህ አይቀርም። ብዙዎች የሚያውቁህ በጭምትነትህ ይሆናል፤ ጥረትህ ግን ደፋርና አይበገሬ ያደርግሃል። ጥረትህን ባያዩም ውጤትህን ተመልክተው መደመማቸውም አይቀርም።

አዎ! ሰበብ ማብዛት የምትፈልገውን ሃይል አይሰጥህም፤ ምክንያት መደርደር ያለህን ጊዜ አያስረዝምም፤ ጣት መቀሰር የሚገባህን ህይወት አያጎናፅፍህም። በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን ላንተ አዝኖ የሚቆም የጊዜ ሰሌዳ የለም። ማድረግ ያለብህን ካላደረክ፣ እንደምትፈልገው ካልኖርክ ጊዜ ጥሩ ትምህርት ሊሰጥህ ዝግጁ ነው። ጊዜ ከማስተማሩ በፊት ግን አንተ እራስህን አስተምር። እድገትን ከፈለክ ለእራስህ ማዘን ጀምር፤ ለውጥን ከተመኘህ የህይወትን አጭርነት በሚገባ ተረዳ። ምንም ዋጋ ያለው ነገር ሳታደርግ የሚያልፉ ቀናት በበዙ ቁጥር እድሜህን እየቀስክ አጭሯን ህይወት ይባስ እያሳጠርካት ወደፊት ትጓዛለህ። በእርግጥም ብዙ የቀሩህ ጊዜያት ሊኖሩ ይችላሉ፣ ሃሳብህን ለመተግበር፣ ህልምህን ለመኖር፣ ግብህን ለመምታት፣ እቅድህን ለማሳካት ግን ጊዜ የለህምና በቻልከው ፍጥነት፣ በላህ ግብዓት ወደ እርምጃ ግባ።


ተጨነቁ!

ጭንቀትን አትሽሹ፣ ከሃሳብ ለመራቅ አትሞክሩ፣ ውጥረትን አትጠየፉ። አውቃችሁና መርጣችሁ ግቡበት። በሚገባ ተጨነቁ፣ ፈልጋችሁ ውጥረት ውስጥ ግቡ። ጭንቀታችሁ ግን ተራ ጭንቀት አይሁን፣ ሃሳባችሁ ግን የወረደ ሃሳብ አይሁን። ፍሬ ያለው የአሸናፊዎችን ጭንቀት ተጨነቁ፣ ውጤት የሚያመጣውን ትልቅ ሃሳብ አስቡ። ብዙ ሰው እንደ ጨነቀው ደጋግሞ ይናገራል የሚጨነቀው ግን ለትንሽና ለአላፊ ነገር ነው። ማንም ሰው ቢጨነቅ የጭንቀቱን ልኬት የሚወስነው የሰጠው ቦታና ትኩረት ነው። ትልቅ ነገር ማድረግ ፈልጋችሁ በትንሹ መጨነቅ አትችሉም፤ አላማ ኖራችሁ ብዙ እንቅልፍ አልባ ምሺቶችን አለማሳለፍ አትችሉም። ለውጥ አምጪ፣ ህይወት ቀያሪ፣ ዋጋን ጨማሪ ከሆነ ተጨነቁ፣ ደጋግማችሁ ተጨነቁ። ሲጀመር የእለት ጉረሱን በልቶ ለማደር የሚጨነቅና ብዙ ሰው ለመመገብ የሚጨነቅ ሰው እኩል የስራ ተነሳሽነት አይኖራቸውም። ለራሳችሁ ከሆነ ፆማችሁንም ታድሩ ይሆናል የሚጠብቃችሁ ሌላ ሰው እንዳለ ካሰባችሁ ግን ተጨናንቃችሁም ቢሆን ያንን ምግብ ኬትም ታመጡታላችሁ።

አዎ! ተጨነቂ! የአሸናፊዎችን ጭንቀት ተጨነቁ፣ የስኬታማ ሰዎችን ጭንቀት ተጨነቁ፣ የነዛን አንድ ሲናገሩ የሚደመጡት፣ ሰው ባያቸው ቁጥር ቦታ የሚለቅላቸውን፣ ከቁስና ከንብረት በላይ በስራቸው የሰውን ልብ የሚገዙትን፣ በሔዱበት ሁሉ ግርማቸው የሚያስፍሩት እነዛ ሰዎች የሚጨነቁትን ጭንቀት ተጨነቁ። ስለ ጥቃቅን ነገር ከልክ በላይ እያሰባችሁ ጊዜያችሁን አታጥፉ። ካሰባችሁ ትልቅ ሰው የሚያስበውን ሃሳብ አስቡ፣ ከተጨነቃችሁም በትልቅ ነገር ተጨነቁ። ብዙ ሰው ይጨነቃል ተጨንቆ ግን ምንም አያመጣም፣ ብዙ ሰው በሃሳብ ብዛት አፍጥጦ ያድራል ነገር ግን ተግባር ላይ ዜሮ ነው። ከአሁን ቦሃላ አልጨነቅም እያላችሁ ይባስ ትርጉም የሌለው ጭንቀት ራሳችሁን አታስጨንቁ። መፍትሔ ለማምጣት በደምብ ተጨነቁ፣ ልጥን እደሰገትን ለማስከተል ተጨነቁ። መጨነቃችሁ ካልቀረ ቢዘገይም እንኳን የጭንቀታችሁን ፍሬ ዓለም ማየት እንዳለበት እወቁ።

አዎ! ጀግናዬ..! በራስ ለመቆም መሞከር ስቃይ አለው ከስቃይ እጅግ በጣም የከፋ ስቃይ አለው። መቼም ከጭንቀት የፀዳ ህይወት ልትኖር አትችልም። ጭንቀትህ ግን የታላቅነት ጭንቀት ነው፣ ስቃይህ ለድል የሚያበቃህ ስቃይ ነው። መደበኛ ጭንቀት መደበኛ ውጤት ያመጣል፣ ከባድ ጭንቀትም ትልቅ ለውጥን ያመጣል። ባዶ ሜዳ ላይ እንዲሁ ምንም ሰታሰራ ራስህን በከባድ አዙሪት ውስጥ አታመላልሰው። መጀመሪያ የምትፈልገውን እወቅ፣ እንዴት እንደምታገኘው አስብ፣ እቅድ አውጣለት፣ መጨነቅ ካለብህ ተጨነቅለት፣ በስተመጨረሻም ተነስተህ ማደን ጀምር። በስቃይ ውስጥ ማደግን ምርጫህ አድርግ፣ በውጣውረድ መሃል ፈክቶ መውጣት መገለጫህ ይሁን። ሰው ባየው ይፈርዳል፣ በሰማውም የራሱን መደምደሚያ ያስቀምጣል። "ጭንቀታም ነው ወይም ሃሳብ ያበዛል" ስለተባልክ ጭንቀትህን አታቁም፣ ማሰብህን አትግታ። ጭንቀትህ ውስጥህ የተቀበረውን መዓድን ለማውጣት ከሆነ በደምብ ተጨነቅ፣ ሀሳብህ አዲስ ነገር ለመፍጠር ከሆነ በደምብ አስብ። ለፍላጎትህ እንጂ ፍላጎትህ ለሚያስከትለው ጫና ቦታ አትስጥ።


•// አላማችሁን ተረዱት ••\\

ሰው የተፈጠረለትን አላማ መረዳት ሲሳነው ደስታና እርካታ ይርቀዋል ስለዚህም .....

በህልውናችን ውስጥ ያለምክንያት የሚፈጠር ነገር የለም፡፡ ከእያንዳንዱ ፍጥረት በስተጀርባ አላማ አለ፡፡ ህይወትም ሆነ ሞት የተፈጠሩት በምክንያት ነው፡፡ ተፈጥሮ ማንኛውንም ነገር በከንቱ አትፈጥርም

ሰዎችም እንዲሁ የራሳቸው ተፈጥሯዊ አላማ፣ ግብና አቅጣጫ አላቸው፡፡ የአላማቸውና የተልእኳቸው ስኬት ውበት፣ እርካታና ደስታን ይፈጥራል፡፡ አምላክ ሰውን የፈጠረው በምክንያት፣ በአላማ ነው፡፡ ሰው የተፈጠረለትን አላማ መረዳት ሲሳነው ደስታና እርካታ ይርቀዋል፡፡ በአንጻሩ የተፈጠረበትን ምክንያት ተገንዝቦ ተልእኮውን ማሳካት ሲችል የአእምሮ ሰላምና የመንፈስ እርካታን ያገኛል፡፡

በብዙሀኑ ዘንድ ( Self - Realizationism) በመባል ፣ የሚጠራው የአርስቶትል የስነ ምግባር ፍልስፍና መልካም ህይወት ወይም ደስተኝነት ባህሪን፣ ሰብእናንና እምቅ ሀይልን ሙሉ ለሙሉ ጥቅም ላይ ከማዋል ይመነጫል የሚለውን እሳቤ መሰረት ያደረገ ነው፡፡

አንድ ህጻን እንደተወለደ ሰው አይባልም  ሰው የመሆን  እምቅ ሀይል ያለው ግን ሰው ለመባል ያልደረሰ ፍጡር ነው፡፡ እውነተኛ ሰው ለመሆን እምቅ ሀይሉ እውን ሆኖ መታየት አለበት፡፡

አንድ ሰው ከቤትሆቨን ያልተናነሰ ዜማዊ ተሰጥኦ ተችሮት ተሰጥኦውን ማወቅ ከተሳነው ወይም እያወቀ መጠቀም ካቃተው ከቶውኑ አርቲስት ሊሰኝ አይችልም፡፡ ታላቅ አርቲስት ለመሆን የሚያበቃ እምቅ ሀይል ቢኖረውም ሀይሉንና ተሰጥኦውን ጥቅም ላይ እስካላዋለው ድረስ የአርቲስትነት ተሰጥኦ ስላለው ብቻ አርቲስት አይባልም፡፡

እንደ አርስቶትል እሳቤ የሰው ልጅ ተቀዳሚ አላማ ተፈጥሮውና ተሰጥኦው እስከፈቀደለት አጥናፍ ተለጥጦ እምቅ ሀይሉን እውን ማድረግና ምሉእነትን መጎናጸፍ ነው፡፡ ይህን ማድረግ የቻለ ሰው ተልእኮውን ከመወጣት ስሜት የሚመነጭ የተሟላ እርካታና ደስታ ያገኛል፡፡

አንድ የአበባ ዘር ሊያብብ፣ ሊፈካና ሊያፈራ የሚችለው የእድገት ኡደቱን አጠናቆ ውበቱንና ሙሉነቱን አሟልቶ ሲገኝ ብቻ ነው፡፡ ሰው በርካታ ውስብስብ ባህሪያትን ይዞ ቢፈጠርም ተልእኮውን መወጣት ከቻለ ስኬታማ የሆነ ውብ፣ ደስተኛና ምሉእ ፍጡር ይሆናል ፡፡


ስልካችሁን ጣሉት!

እስካሁን አላወቃችሁትም ነገር ግን ትብታብ ውስጥ ናችሁ፣ እስካሁን አልገባችሁም ነገር ግን እየተሰለላችሁ ነው፣ አሁንም ተሸውዳችኋል ምክንያቱም ዛሬም ከስልካችሁ ተጣብቃችኋል። ጥቂቶች በስልካቸው ይጠቀማሉ፣ ብዙዎችን ግን ስልካቸው ይጠቀምባቸዋል። እናንተ ከየትኞቹ እንደሆናችሁ ጠንቅቃችሁ እወቁ። ማንም ሰው ስልኩን በነፃ አላገኘም። ምናልባትም ከሚበላው ቀንሶ፣ የሚለብሰውን ትቶ አጠራቅሞ እጅግ ውድ ስልክ የገዛ ይኖራል። ከገዛው ቦሃላም እንዴት መጠቀም እንዳለበት ሳያውቅ እንዲሁ ለመደዋወልና የማይረባ Content  ሲመለከትበት ይስተዋላል። የስልክ ጥሪ ለማንሳት፣ ሰው ጋር ለመደወል፣ ቪድዮ ለማየት ውድ ስልክ ምን ያደርግላችኋል? ተጠቅማችሁት ገንዘብ ማምጣት ካልቻላችሁ ስለምን ብዙ ገንዘብ ፈሰስ ታደርጉበታላችሁ? ይሔ ስልክ እየጠቀማችሁ ካልሆነ በእርግጠኝነት እየጎዳችሁ እንደሆነ አትጠራጠሩ። ራሳችሁን አትሸውዱ። ከሰው በላይ የሚያደርጋችሁ የያዛችሁት ስልክ ውድነት ሳይሆን በያዛችሁት ስልክ ተጠቅማችሁ የምታመጡት ውጤት ነው። በቁስ መወዳደር አቁሙ፤ ይልቅ ባላችሁ ቁስ ገንዘብ ስሩበት። ለመታየት ብቻ የምትጠቀሙበትን ኤሌክትሮኒክስ አትሰብስቡ፣ ገንዘብ ከተረፋችሁ ተጠቅሞበት ሊያመሰግናችሁ ለሚችል ሰው ስጡ።

አዎ! እርሱ እናንተን ከመጣሉ በፊት እናንተ አስቀድማችሁ ስልካችሁን ጣሉት፣ ከፊታችሁ ዞር አድርጉት፣ ድጋሜ እንዳታገኙት ከአካባቢያችሁ አርቁት። ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ህይወታችሁ ያለስልክ ምን እንደሚመስል ተመልከቱ። ብዙዎች ወደውና ፈቅደው በገዙት ስልካቸው ስቃይ ውስጥ ገብተዋል፣ ህይወታቸውን ያለስልክ ማሰብ አይፈልጉም፣ በስልካቸው ከሚመለከቱት ዓለም ውጪ ሌላ ዓለም ያለ አይመስላቸውም፣ እዛ ላይ የሚለቀቀውን መረጃ ሁሉ ያግበሰብሳሉ ሚዛናዊ እሳቤያቸውንም ያጣሉ። ነቃ ብላችሁን ራሳችሁን ፈትሹ። ዓለም በፈለገችው መንገድ እየመራቻችሁ ነው፣ በማይረባ መረጃ እየተበተበቻችሁ ነው፣ ሳታውቁት ትክክለኛ ማንነታችሁን እየቀማቻችሁ ነው፣ እንዲሁ በቀላሉ ስንፍናንና ድክመትን እያለማመደቻችሁ ነው። ህይወታችሁ ፈር አትቶ አቅሉን ስቶ መዳረሻ ሳይኖረው እንዲሁ እየባከነ እንዲቀጥል ካልፈለጋችሁ ከውጪው ዓለም ጋር ከሚያገናኟችሁ መሳሪያዎች ጋር ያላችሁን ግንኙነት በሚገባ አስቡበት። ሳታውቁት እየጠፋችሁ ነው፣ እየሳቃችሁ ወደ ጨለማው እየተጓዛችሁ ነው። በስልካችሁ ቁጥጥር ስር ከሆናችሁ ብዙ ያልኖራችሁት ህይወት እንዳመለጣችሁ አስተውሉ።

አዎ! ጀግናዬ..! ስልክህን አንተ ትገዛዋለህ ወይስ እርሱ ገዝቶሃል? መሪህ ይህ ትንሽዬ ቁስ ነው ወይስ ራስህ ነህ? ብዙ ሰው ከሚጠቀምበት በተለየ ስልክህን ለምንና እንዴት እየተጠቀምከው ነው? የስልክ አጠቃቀምህን ችላ ባልከው ቁጥር ዛሬ ሳይሆን ነገ ትልቅ ዋጋ ትከፍልበታለህ። ስልክህ ህይወትህን ካስተካከሉት ቁሱችህ መሃል እንጂ ህይወትህን ካመሰቃቀሉት ቁሱች መሃል መሆን እንደሌለበት እወቅ። ማንም ተነስቶ ትኩረትህን እንዲወስድ አትፍቀድ፣ የትኛውም ጊዜያዊ አጀንዳ እንዲረብሽህ አታድርግ። ከዓለም ጋር ወደ ፊት መራመዱን እወቅበት። በአንዲት ትንሽዬ ቁስ ጊዜህንና ስሜትህን አትሽጥ። ስልክህ ላይ ተደፍተህ እየዋልክ መቼም ልታሸንፍ እንደማትችል አስተውል፣ አላፊ አግዳሚውን እየሰማክ፣ ቀልድና ጫወታን እያዘወተርክ፣ ገፅህን እያበራህ ውስጥህን እየጨቆንክ መቼም ደስተኛ እንደማትሆን ተረዳ። ስልክህ ላይ ሳይሆን ራስህ ላይ ተደገፍ፣ ስልክህን ሳይሆን አዕምሮህን ተጠቀም። ለትንሽ ደቂቃ እንኳን ትኩረት ማድረግ የማይችል ደንዛዛ አዕምሮ አታድርገው። ውስጡ የተሰነጉትን የማይረቡ መረጃዎች አውጥተህ ጣል፣ አስቦ አመዛዝኖ የተረጋጋ ሚዛናዊ ህይወት እንዲያኖርህ አድርግ።


የማታንቀላፉ ሁኑ!

ውጪ ከቤታችሁ በር አፋፍ ላይ ሁለት አይነት ሰዎች ይጠብቋችኋል። በቁጥር የበዙት ከአሁን ከአሁን ስለመውደቃችሁና ተስፋ ስለመቁረጣችሁ ለመስማት በጉጉት ይጠብቃሉ፣ በቁጥር እጅግ ያነሱትና በጣት የሚቆጠሩት ደግሞ ተስፋ አለመቁረጣችሁን፣ አለመበገራችሁንና ማሸነፋችሁን በትልቅ ጉጉት ይጠባበቃሉ። ማንን ማሳፈር ትፈልጋላችሁ? ማንንስ ማስደሰት ትፈልጋላችሁ? የእናንተን ምርጫ ውጪ የቆሙ ሰዎች አይወስኑላችሁም። ሁሉም በእጃችሁ ነው። ውድቀታችሁን አብዝተው የሚፈልጉ ሰዎች አስቀድመው የወደቁ ሰዎች ናቸው፣ በእናንተ ተስፋ መቁረጥ፣ በእናንተ ጀምሮ ማቋረጥ የሚደሰቱ ሰዎች ቀድሞውኑ የተበለጡና ተስፋቢስ ሰዎች ናቸው። አስቀድማችሁ አንድ ነገር አስቡ። የጀመራችሁት ጠላታችሁን ለማሳፈር ወይም ወዳጃችሁን ለማስደሰት አይደለም። የጀመራችሁት የገዛ ነፃነታችሁን ለማወጅ ነው፣ የጀመራችሁት የራሳችሁን ደስታ በራሳችሁ ለመጀመር ነው፣ የጀመራችሁት አቅማችሁን አውቆ ለማሳወቅ ነው። ሰውን ለማስደሰትም ሆነ ለማስቀየም ብላችሁ አትዘናጉ። የእናንተ ትልቁ አጀንዳ ጊዜያዊው የሰው ስሜት ሳይሆን ዘላቂው የእናንተ ስሜት ነው።

አዎ! የማታንቀላፉ ሁኑ፣ የማትበገሩ፣ እጅ መስጠት የማትወዱ፣ አለት ላይ የተገነባ ማንነት ያላችሁ፣ ፅናት መገለጫችሁ፣ ትዕግስት መለያችሁ የሆነ ብርቱ ሰው ሁኑ። ምቀኛችሁ ይፈር ወዳጃችሁ ይኩራ፤ ጠላታችሁ ይዘን ወዳጃችሁ ይደሰት። ለማንም ቁልፋችሁን አትስጡ። ራሳችሁ ስትፈልጉ ብቻ ክፈቱት ካልፈለጋችሁም ቆልፋችሁ አስቀምጡት። ሺህ ሰው እየጠላችሁ አንድ ሰው ቢወዳችሁ ጉዳያችሁ ከሚጠሏችሁ ሰዎች ጋር ሳይሆን ከዛ ከሚወዳችሁ አንድ ሰው ጋር ነው። ምንም አይነት ሰው ብትሆኑ የሚወዳችሁንም የሚጠላችሁንም ሰው ማግኘታችሁ አይቀርም። የራሳችሁ ወዳጅ ስትሆኑ ለወዳጃችሁ ቦታ መስጠት ትጀምራላችሁ፣ በራሳችሁ ስትተማመኑ ብቻ ብርታት ጥንካሬያችሁን አደባባይ ማውጣት ትችላላችሁ። ማንቀላፋት መገለጫችሁ እንዲሆን አትፍቀዱ፤ ስንፍና እንዲሰብራችሁ አትፍቀዱ። ቆቅ መሆንን ልመዱ። ለማንም በቀላሉ አትሸወዱ፣ ጨለማውን መቆያ አታድርጉት።

አዎ! ጀግናዬ..! ብዙዎች እንደ ተኙ ጊዜ ጥሏቸው ሄዷል፣ ብዙዎች በምኞት ታስረው ሃሳብ ብቻ ሆነዋል፣ ብዙዎች ከጥንካሬያቸው ይልቅ በስንፍናቸው እየተመፃደቁ ነው። አንተ ግን ከብዙዎች መሃል ተነጥለህ ውጣ፣ እያንቀላፋህ ፀሃይ አትጥለቅብህ፣ ሰበብ እያበዛህ ዓለም አትደብዝዝብህ፣ ተዘናግተህ ባዶህን እንዳትቀር፣ ትልቁ ሃይልህን ቸል አትበለው፣ ድክመትህን በመሸፋፈን ራስህን አታድክም። ከራስ በላይ ለሰው መኖር ድክመትህ ከሆነ ፊትለፊት ተጋፈጠው፣ ከወዳጅ በላይ ለጠላት ቦታ መስጠት ካበዛህ እይታህን ቀይር። አንዳንዶች ምንም ነገር የሚያልፍ አይመስላቸውም። የሆነ ጊዜ ጠላትህ የነበረ ሰው ወደፊት ወዳጅህ እንደማይሆን እርግጠኛ መሆን አትችልም፤ የዛሬ ወዳጅህም እንዲሁ ነገ ጠላትህ ሊሆን እንደማይችል እርግጠኛ መሆን አትችልም። በተለዋዋጭ ዓለም ማንቀላፋት አያስፈልግም። ነቅተዋል የተባሉ ሰዎችም ብዙ ተሸውደዋል። የማታንቀላፋ ንቁ ሰራተኛ ሁን። ዓለም ልትረሳህ ብትሞክርም አንተ ግን መኖር በውጤትህ አሳይ።


ሁሉን ያስችልሃል!
፨፨፨፨/////፨፨፨፨
መንፈሳዊነት ስድብን ያስችላል፤ የትቺትን ሃይል ያሳንሳል፤ የዘለፋን አቅም ያከስማል። መንፈሳዊነት በፈሪሃ እግዚአብሔር (አላህን በመፍራት) የተቃኘ ማንነትን ያጎናፅፋል። በአምላክህ ስትተማመን ፍረሃትህ ይወገዳል፤ ስሜትህ ይስተካከላል፤ ውስጥህ ይነፃል፤ ትናንትህ የፀዳ፣ ዛሬህ የፈካ፣ ነገህም በብሩህ ተስፋ የተሞላ ይሆናል። ለመንፈሳዊ ህይወትህ ተገቢውን ትኩረትና ጊዜ ስጥ። ሃይማኖታዊ አስተምህሮዎችን ማዳመጥ፣ ቅዱሳት መፅሃፍትን ማንበብ፣ በጎ ምግባራትን መፈፀም፣ ሰዎችን መርዳት፣ መልካም ልበ ቀና ሰው ሆኖ መገኘት የመንፈሳዊነት መሰረት ነው። እውቀት እንደሚኖር ሁሉ መንፈሳዊነትም በህይወት የሚገለጥና በመሬት ላይ የሚታይ ነው። ብዙ ተምረናል፣ ብዙ አውቀናል፣ ብዙ ተግባራትን ፈፅመናል፣ ብዙ ቦታ ተገኝተናል ነገር ግን የማይኖር ተምህርት፣ የማይተገበር እውቀት፣ ፍሬ የሌለው ተግባር፣ ተርፍ የሌለው ቦታ መገኘት ከድካም ውጪ ጥቅም የለውም።

አዎ! ጀግናዬ..! ሁሉን ያስችልሃል። ወደ እራስህ መመለስህ፣ ከአምላክህ ጋር መነጋገርህ፣ እውነተኛው ስሜትህን ማዳመጥህ፣ ለውስጣዊ ማንነትህ ጊዜ መስጠትህ፣ በመንፈሳዊነት መቃኘትህ፣ በአምላክ ህግጋት መመራትህ፣ ከሰው በላይ ፈጣሪህን መፍራትህ፣ ለእርሱ ለመታመን መጣርህ በእርግጥም ሊጎዳህና ሃይልህን ሊያሳጣ የመጣውን የትኛውንም አሉታዊ ተፅዕኖ ያስችልሃል፤ የሚወረወርብህን ያልተገባ ቃል ያሳልፍሃል፤ ከሚደርስብህ ጫና ነፃ ያወጣሃል። የሰው ልጅ በሙሉ በደል አለበት፣ ሀጢያት አለበት። በደሉም አንድም አምላክን ሲሆን ሌላውም የሰውን ልጅ መበደሉ ነው። አለምም ለየትኛውም ሰዋዊ በደል ቅጣትን ትበይናለች፤ አምላክ ግን ይቅርታን ያስቀድማል፤ ጊዜን ይሰጣል፤ በትዕግስት ይጠብቃል፤ በመንፈሳዊነት ሊቃኘን ይሞክራል።

አዎ! ሁሉን እችላለሁ ብትል የሚያስችል ቸሩ አምላክ ነው፤ የመጣብኝን ሁሉ እሻገራለሁ ብትል የሚያሻግር ደግ ፈጣሪ ነው። እውቀትን ያደለን፣ ብርታትን ያጎናፀፈን፣ ደግ ልቦናን የሰጠን አምላክ እውቀታችንን የምንኖርበት ጥበብ፣ በብርታታችን የምናተርፍበት ንቃተ ህሊና፣ ደግ ልቦናችንን የምንጠቀምበት ብሩክ ሃሳብ ይሰጠን ዘንድ መልካም ፍቃዱ ይሁን። ሰላምህን በመንፈሳዊነት አግኘው፤ ፍቅርን ከአምላክ በረከት አትርፍ። መንፈሳዊነት አለምን ያስረሳኛል፤ መኖር ከሚገባኝ ህይወት ያግደኛል፤ ማፍራት ያለብኝን ንብረት ያሳጣኛል የምትል ከሆነ ከዚህ አመለካከት ውጣ። በመንፈሳዊነትህ የሚጨመርልህ እንጂ የምታጣው አንዳች ነገር የለም። በአዎንታዊ አመለካከቶች የምትቃኘው፣ በፈጣሪ የተወደዱ፣ ለሰው ልጆች የሚጠቅሙ፣ ህይወትህን የሚያረጋጉ ተግባራትን የምትፈፅመው በመንፈሳዊነት ሃይል ነው። በሔድክበት ሁሉ ከደግነትህ አትለይ፤ በምታደርገው ሁሉ ቅንነት አይለይህ፤ ላገኘሀው ሰው ሁሉ መልካም ሁን። ምናልባት ርህራሔህ ሊያስጠቃህ ቢችልም አምላክ ልብህን አይቶ በበረከት እንደሚሞላህ እመን።


መቼ ያበቃል?

አብዝታችሁ ተስፋ የጣላችሁበት ሰው ተስፋችሁን ሞልቶታል ወይስ መና አስቀርቶታል? ከልብ አምናችሁ የጠበቃችሁት ሰው የጠበቃችሁበትን ነገር ሰጥቷችኋል ወይስ ጊዜያችሁን አባክኗል? እራሳችሁን ገዝታችሁ፣ ስሜታችሁን ተቆጣጥራችሁ፣ ጥቅማችሁን አሳልፋችሁ ሰጥታችሁ፣ ለሰው ብላችሁ ተጎድታችሁ የኋላኋላ አትርፋችኋል ወይስ እንደ ጥፋተኛ ተቆጥራችሁ ተገፍታችኋል? ማንም ሰው ይሳሳት ይሆናል፣ ማንም ሰው ይባክን ይሆናል ተስፋ ማድረግ ያልነበረበትን ሰው ተስፋ እንደሚያደርግ፣ መጠባበቅ ያልነበረበትን ሰው እንደሚጠባበቅ፣ ወሳኙን የህይወቱን ክፍል ለሌላው ሰው አሳልፎ እንደሚሰጥ ሰው ግን ለከፋው ስህተትና ብክነት እራሱን የሚያመቻች ሰው የለም።

አዎ! ጀግናዬ..! መቼ ያበቃል? በሰዎች ትከሻ ተማምኖ የእራስን የስራ ድርሻ መርሳት መቼ ያበቃል? ሰዎችን መንገድ ጠቋሚ እራስን ተከታይ አድርጎ መጓዝ መቼ ያበቃል? እራስን እንደ ሰነፍ ሌላውን እንደ ጀግናና ብርቱ መቁጠር መቼ ያበቃል? ከእራስ ውሳኔ በላይ ለሰዎች ውሳኔ መገዛት፣ ከእራስ አቋም በተሻለ የሰዎችን አቋም ማራመድ ምንያክል አትራፊ ያደርጋል? እራስን እየጎዱ በሰዎች ዘንድ ተቀባይ ለመሆን መጣር መቼ ያበቃል? ሰውን በመጠባበቅ እራስን ችላ ማለት ምንያክል ያዋጣል? ከደካማው ሰው የፈጣሪን ያክል አንጀት አርስ ምላሽ መጠበቁስ መቼ ያበቃል?

አዎ! ሰዎችን ጥበቃ በሰዓቱ ማድረግ የምትችሉትን ነገር ሳታደርጉ እራሳችሁን ለከፋ ጫና አታጋልጡ። ማንም ሰው የእራሱ ብርቱ ጉዳይ አለበትና የትኛውም ጉዳያችሁ ለእናንተ አንገብጋቢና እንቅልፍ ነሺ እንደሆነው ለሌላውም ሰው እንደዛው ሊሆን እንደማይችል እወቁ። የናንተ የቤት ስራ የሚሰራው በእናንተ ብቻ ነው። ሰዎች ህይወታችሁን እንደሚቀይሩ መጠበቅ አቁሙ፣ ሰዎች እጃችሁን ይዘው ሰራ እስኪያሰሯችሁ አትጠብቁ፣ የሰዎችን ይሁንታ በመጠባበቅ ጥቂቷን ጊዜያችሁን ከማባከን ተቆጠቡ። ምንም ጉዳይ ከአቅማችሁ በላይ ካልሆነ በቀር ለህይወታችሁ ወሳኝ እስከሆነ ድረስ ሰዎች እንዲያስፈፅሙላችሁ ሙሉ በሙሉ ጉዳዩን ለእነርሱ አትተዉ። ሃላፊነታችሁን ተወጡ የሚባክነውን የጥበቃ ጊዜና ንፁ ተስፋችሁን አትርፉ።

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.