የደስተኛነት ምርጫ!፨፨፨፨///////፨፨፨፨
አንደኛው ምርጫህ በኑሮህ የጎደለውን ነገር እየቆጠርክ ማዘንና መነጫነጭ ነው፡፡ ሌላኛው ምርጫህ ግን ከሌለህና ከጎደለህ ነገር ላይ ትኩረትህን በማንሳት ባለህ ነገር ደስተኛ ሕይወትን ለመምራት መወሰን ነው፡፡
አንድ ሰው እንዲህ ሲል ተናገረ … "
ከ13ኛው ክፍለ-ዘመን በፊት የነበሩ አባቶቻችን ስኳር የሚባል ነገር አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ …
ከ14ኛው ክፍለ-ዘመን በፊት አባቶቻችን የኤሌክትሪክ ምድጃ ቀርቶ ከሰል የሚባል ነገር እንኳን አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ …
ከ15ኛው ክፍለ-ዘመን በፊት የነበሩ አባቶቻችን በቅጡ የተጋገረ ዳቦ የሚባል ነገር አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ …
ከ16ኛው ክፍለ-ዘመን በፊት የነበሩ አባቶቻችን ድንች የሚባል ነገር አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ …
ከ17ኛው ክፍለ-ዘመን በፊት የነበሩ አባቶቻችን ቡና፣ ሻይና ሾርባ የሚባሉ ትኩስ ነገሮች አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ …
ከ18ኛው ክፍለ-ዘመን በፊት የነበሩ አባቶቻችን ኬክና የመሳሰሉት ጣፋጭ ምግቦች የሚባል ነገር አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ …
ከ19ኛው ክፍለ-ዘመን በፊት የነበሩ አባቶቻችን እንቁላል፣ ክብሪትና የኤሌክትሪክ ኃይል የሚባል ነገር አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ …
ከ20ኛው ክፍለ-ዘመን በፊት የነበሩ አባቶቻችን ተዘጋጅቶ የታሸገ ምግብ የሚባል ነገር አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ …"
(Unknown Source)
በዚህ ላይ መጨመር ካለብን ከላይ በተዘረዘሩት ክፍለ-ዘመናት ይኖሩ የነበሩ አባቶቻችንና እናቶቻችን ዛሬ የምናውቃቸውን የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አያውቁም ነበር - ነገር ግን ደስተኞች ነበሩ፡፡
ምናልባት ይህንን ጽሑፍ እያነበብክ ያለህበት የዓመቱ ስንተኛው ወር ላይ እንደሆነ ባላውቅም፣ እስቲ ዓመቱ ከገባ ጀምሮ እስከዛሬዋ ቀን ድረስ አለኝ በምትለውና ጎድሎኛል በምትለው ነገር አንጻር የነበረህን ዝንባሌ ለማስታወስ ሞክር፡፡ ምናልባት ስለሌለህ ነገር ስትበሳጭና ስሜትህ ሲቃወስ ራስህን አግኝተኸዋል ብዬ እገምታለሁ፡፡ አሁን በተያያዝከው ሕይወት ውስጥ የምትፈልገውን ነገር ሁሉ ያለማግኘትህ እውነታ ደስተኛነትህን እንድታዘገየው ከተጫነህ የሕይወት ዘይቤ ምርጫህን ማስተካከል እንዳለብህ ጠቋሚ ነው፡፡
የሆነውን ሳይሆን ያልሆነውን ማሰላሰል በርካታ ጠንቆች አሉት፡፡ ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል፣ በሌለንና በጎደለን ነገር ላይ ብቻ ማተኮር ታላቅ የሆነን የስሜት ቀውስ ያስከትላል፡፡ የመነሳሳትና ወደፊት ለመቀጠል የሚኖረንን ግለት ያበርድብናል፡፡ በሁኔታው የሚኖረንን የመነጫነጭ ባህሪ በመመልከት የቅርብ ወዳጆቻችን ቀስ በቀስ እየራቁንና ከእኛ ጋር ለመሆን ያላቸውን ፍላጎት እያጡ ይሄዳሉ፡፡ እንግዲህ ከእነዚህና ከመሰል አጉል ተጽእኖዎች ለመዳን ትክክለኛውን ምርጫ መከተል የግድ ነው፡፡
ዛሬ ለሌለህ ነገር እየሰራህና መለወጥ ወደምትፈልገው የተሻለ የባህሪይ ማንነት ለመለወጥ እየተጋህ ሳለህ፣ ባለህ ነገር ግን ደስተኛ መሆን ትችላለህ፡፡
/ከምርጫና ውሳኔ መጽሐፍ ገፆች/
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
🔺🔻
በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን!SUBSCRIBE NOW! 👇
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1ምክረ-አዕምሮ/
@MentalCounsel 😊💪