በክብር ተቀበል!
ማንም ሰው የእራሱ መገለጫ፣ የእራሱ እምነትና የእራሱ የህይወት ዘይቤ ይኖረዋል። አስተዳደጉ፣ ባህሉ፣ አመለካከቱና አቋሙ ሁሉ የማንነቱ መገለጫ ነው። እስካመነበትና እስከተቀበለውም ድረስ ለእርሱ ልክ ነውና ከብሩና ኩራቱ ነው። የሌላውን ሰው የክብር መገለጫ፣ የሌላውን ባህልና እምነት ማክበር ደግሞ እራስን እንደማክበር፣ ለእራስም ጥበብን እንደማስተማር ነው። ከጥላቻ በላይ እለት እለት ፍቅርን የሚመግበን፣ መተሳሰብ መከባበርን የሚያስተምረን፣ ሰብዓዊነት ሰውነትን የሚያሳድርብን አምላክ አለን። የጎሪጥ በመተያየት የሚመጣ ነገር ቢኖር ጥላቻና መጠፋፋት ብቻ ነው። መከባበር፣ መፈቃቀር፣ መዋደድ ውስጥ ዋናውን የሰውነት ማንነት እናገኘዋለን። እንደጠዋቷ ጀምበር እንዲሁ እያየናት ለምትጠልቅ አጭር የህይወት ዘመናችን እርስበእርስ ባንገፋፋና ባንጠላላ ጥቅሙ ለእራሳችን ነው።
አዎ! ጀግናዬ..! በክብር ተቀበል! ማንም የወደደውን ቢያደርግ፣ ማንም የትም ቢገኝ፣ ማንም በእምነት በአመለካከቱ ቢመላለስ አንተን እስካልነካና እስካልተጋፋህ ድረስ በክብር ተቀበለው፤ ወግ ባህሉን፣ አስተምህሮውንና እሳቤውን አክብርለት። ቢሳሳት እንኳ በቂም በቁርሾ አትመልሰውም፤ ቢያጠፋ እንኳን ፊት በመንሳት፣ የማይሆን ስም በመስጠት አታስተምረውም። ፍቅር ሰውን ይገዛል፤ አክብሮትም ልብን ያቃናል። ጠልቶህ ጠልተሀው፣ ገፍቶህ ገፍተሀው፣ አርሱም ልታይ አንተም ልታይ ብለህ መቼም ደህንነትህን ልታስጠብቅ፣ ቁስልህን ልትሽርና ሰላምህን ልታስጠብቅ አትችልም። አፋፍና አፋፍ ቆመህ እርስበእርስ ብትነታረክ ነገህን ይባስ ታስከፋው፣ መጪውንም ጊዜህን ታጨልመው ይሆናል እንጂ አንዳች ትርፍ አይኖርህም።
አዎ! በፍቅር ግዛ፣ በክብር ተቀበል። ቂም ያነገበ፣ በእልህ የሚጓዝ፣ በጥላቻ የታወረ፣ ሁሌም እኔ ብቻ የሚል ሰው አትሁን። እግዚአብሔር በጊዜ መረብ ሁሉን ሲያነሳ ሌላውንም ሲተካ አይተናል። ትናንት ብዙ የተባለላቸው፣ ትናንት ስማቸው ብቻ የሚያስፈራ፣ ትናንት ደጋግ የነበሩ እንዲሁም ክፉዎች የነበሩ ዛሬ ጠፍተው፣ ተረስተው ከስመዋል። የዛሬውም ሆነ የነገው የህይወት ጉዞ ከዚህ የተለየ አይደለምና በአጋጣሚ ሁሉ እትመካ፤ ከአንተም በላይ ሰው የሌለ እይምሰልህ። በታሪክ እስራት እራስህን አትግረፍ፤ ውዷ ዛሬ ውስጥ ሆነህ በማታውቀው ትናንት ክስተት ጨጓራህን አትታመም፤ ውስጥህን አታቁስል። ወንድምህ ቢሳሳት በጥላቻ ከምትርቀው በፍቅር መልሰው፣ ማስተዋልን ቢያጣ፣ በጭፍን ቢጓዝ ዞር ብለህ ከምትፈርድመት፣ ስሙንም ከምታጠለሽ በክብር ተቀበለው፣ በትህትናም አስተምረህ መልሰው።