ምስባክ ወማኅሌት


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


👉የንባብ እና የዜማ ትምህርት
👉ሥርዓተ ዋይዜማ፤ ማኅሌት፤ መዝሙር
👉ምስባክ
👉ሥርዓተ ቅዳሴ
የስንክሳር ቻናላችን👉 @metsihafe_sinksar
የመዝሙር ቻናላችን👉 @Mezmur_ZeOrthodox21
🎯ለማግኘት ቻናላችንን ይጐብኙ።
ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ።
መወያያ 👉 @Mezgebe_Thewadho
ለአስተያየት 👉 @Zethewahdobot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri


[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱


'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'>⛪️📚🙏
1, እመጓ
2, ዝጎራ
3, መርበብት
4, ዴርቶጋዳ
5, ዮራቶራድ
6, ዣንቶዣራ
7,መጽሐፈ ሄኖክ
8, ቤተክርስቲያንህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ
9, ፍኖተ አእምሮ
9, አዳም እና ጥበቡ
10, ዝክረ መስቀል
11, ሰይፈ ሥላሴ
12, ፍትሐ ነገስት
13, መጽሐፈ መነኮሳት
14, ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
16, ህግጋተ ወንጌል
17, ነገረ ማርያም በጥንታዊቷ ቤተከርስቲያን
18, ድርሳነ ሚካኤል ወ ገብርኤል
19, ውዳሴ ማርያም በግእዝ
20, ግድለ ተክለሃይማኖት
21, ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ
22, የወጣቶች ህይወት
23, መጽሐፈ ገድለ ሐዋርያት
24, ኦርቶዶክስ መልስ አላት
25, የዋልድባ ገዳም ታሪክ

📚📚የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ ይፈልጋሉ የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት ያንብቡ መልካም ንባብ📖

    
'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'>✝                      ይቀላቀሉን                    ✝


በሰሙነ ሕማማት፦

፩. ቤተ ክርስቲያን መዋል ተገቢ ነው።
፪. ግብረ ሕማሙን መስማት ይገባል።
፫. ተድላ ደስታ አለማድረግ። ሽቶ እና ቅባት ሳይቀቡ፣ የጆሮ የጣት፣ የወርቅ የብር ጌጣጌጥ አለማድረግ።
፬. በሰሙነ ሕማማት ማማተብ ይቻላል።
፭. የሚቀር፣ የሚታጐል ጸሎት የለም። መልክእ መድገምም ይቻላል።
፮. ሐሙስ እግር መታጠብ ይገባል። ንዑሰ ክርስቲያን ቢኖሩ እነሱም ይታጠቡ።
፯. የጸሎተ ሐሙስ ሁሉም ክርስቲያን መቊረብ ይገባዋል።
፱. ዓርብ ምሽት "ንሴብሖ" ተብሎ ዑደት ከተደረገ በኋላ ጸሎት ተደርጐ። "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ተብሎ "እግዚአብሔር ይፍታ" ይባላል። መስቀል መሳለም ግን የለም።
፲. የሚቻለው ከዓርብ ጀምሮ፣ የማይቻለው ግን ቅዳሜን ማክፈል ይገባል።

የበረከት ሳምንት ያድርግልን። ለበዓለ ትንሣኤውም በሰላም ያድርሰን። አሜን።

ከ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ ትምህርት የተወሰደ




👆👆👆
👆👆👆
VIEW MESSAGE (ጽሑፉን) በመንካት ሙሉውን ያንብቡ።
በተጨማሪም የየዕለቱን ለማግኘት Join እያደረጋችሁ👏👏👏




አምነስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ
Em-nees the-tee mo-ki-riey enti vasilia so
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም "ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ" ማለት ነው።

አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ
Em-nees the-tee mo-a-geh-e enti vasilia so
የቅብጥ ቃል ሲሆን "ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ- ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን " ማለት ነው።

አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ
Em-nees the-tee mo-zess-pota enti vasilia so
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም "ተዘከረነ እግዚኦ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ- የሁሉ የበላይ የሆንክ ሆይ በመንግሥትህ አስበን "  ነው።
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
    🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪    
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲ 
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ


በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ  የውጭ ቃላት አሉ ቀጥታ ሳይተረጓሙ ከዕብራይስጥ፣ቅብጥ፤ግሪክ ቃላት ይገኛሉ።

ኪርዬ ኤሌይሶን/ኪርያላይሶን/

ኪርዬ ማለት እግዚኦ ሲሆን ኪርያ ሲሆን ግን እግዝእትነ ይሆናል ኪርያላይሶን የምንለው በተለምዶ ነው እንጂ መባል ያለበት ኪርዬ ኤሌይሶን ነው ትርጉሙም አቤቱ ማረን ማለት ነው።

እብኖዲ ማለት አምላክ ማለት ነው።

ናይናን ማለት ማረን ይቅር በለን ማለት ነው።

ታኦስ የግሪክ ቃል ሲሆን ጌታ አምላክ ማለት ነው።

ማስያስ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ መሲሕ ማለት ነው 

ትስቡጣ ማለት ዴስፖታ ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ደግ ገዥ ማለት ነው።

ኢየሱስ ማለት መድኃኒት ማለት ነው።

ክርስቶስ ማለት መሲሕ ማለት ነው።

አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት ነው።

በሰሙነ ሕማማት የሚባሉ ቀለሞች እንደ ሌላው ጊዜ ወጥ ከግዕዝ የመጡ አይደሉም ይልቁንሙ ከዕብራይስጥ ፣ ከሮማይስጥ ፣ ከግሪክ የተውጣጡ ናቸው።

ቅዱስ ያሬድ ይህንን ያደረገበት ምስጢር ጲላጦስ ጌታን ካሰቀለ በኋላ ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሠ አይሁድ የሚለውን ቃል በእነዚህ ቋንቋዎች ጽፎ በትራፈ መስቀሉ ላይ ጠርቆት ነበርና ያንን ለማስታወስ ነው።

                                     መ/ር ነቢዩ ኤልያስ

ለመከታታል፦
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
    🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪    
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲ 
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ






መልክዓ ኅማማት.pdf
12.4Mb
መልክዓ ኅማማት.pdf


💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
    🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪    
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲ 
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ


ስርዓተ ሕማማት

በሕማማት ወቅት የሚጸለዩ ሲሆን እኛም በጸሎት ጊዜ ጠዋት ወይም በ3፣ በ6 ፣ በ9፣ በ11ሰዓተ መዓልት እየሰገድን አብዝተን ልንጸልይ ይገባናል፡፡ 🤲 🤲 🤲

የሚባለውም የሚከተለዉ ነው፦

✥ "ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም ፡፡"

✥ "አማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም፡፡"

✥ " ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም፡፡ "

✥ " ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ፤ እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኰቴት ፡፡"

❖ " ለአምላክ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም፡፡

❖ "ለሥሉስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለማሕየዊ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለዕበዩ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖"ለእዘዙ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለመንግሥቱ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለስልጣኑ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለኢየሱስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

"ለክርስቶስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለሕማሙ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለመስቀሉ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም፡፡ "

❖ "ለከ ይደሉ ኃይል፣ ወለከ ይደሉ ስብሐት ወለከ ይደሉ አኰቴት ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለመ ዓለም"

ካህኑ ‹ጸልዩ በእንተ ጽንዓ ዛቲ . . .› ብሎ በሚያነብ ጊዜ በየምዕራፉ "እግዚኦ ተሳሃለነ" ወይም "አቤቱ ይቅር በለን" እየተባለ ይሰገዳል፡፡

"ክርስቶስ አምላክነ፤ ዘመጽአ ወሐመ በእንቲአነ በሕማማቲሁ ቤዝወነ፤ ንሰብሖ ወናልዕል ስሞ ኅቡረ፤ እስመ ውእቱ ገብረ መድኃኒተ በዕበየ ሣህሉ" (በዐርብ) ዘሐመ ወሞተ በእንቲአነ ይባላል፡፡

ኪርያላይሶን ፤ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን ፤ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤

#አብኖዲ ናይን ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን

#ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን ፤ኪርያላይሶን ፤

#ታዖስ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤

#ማስያስ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤

#ኢየሱስ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤

#ክርስቶስ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤

#አማኑኤል ናይን፣ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤

#ትስቡጣ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን

ከዚህ በኋላ አርባ አንድ ጊዜ ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን እየተባለ ይሰገዳል፡፡

ንሰግድ ለከ ክርስቶስ ምስለ አቡከ ኄር ሰማያዊ ወመንፈስከ ቅዱስ ማሕየዊ እስመ መጻእከ ወአድኀንከነ
መልክዓ ሕማማት ከጨረሱ በኃላ፦

✥ ስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነ ዘፈጠረ ከመ ናምልኮ (እናመልከው ዘንድ ለፈጠረን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል)፡፡

✥ ስብሐት ለማርያም እመ አምላክ እግእዝትነ ወመድኃኒትነ (እመቤታችንና መድኃኒታችን ለሆነች ለአምላክ እናት ለማርያም ምስጋና ይገባል)፡፡

✥ ስብሐት ለመስቀለ ክርስቶስ ዕፀ መድኃኒት ኃይልነ ወፀወንነ(ኃይላችን መጠጊያችን ለሆነ ድኅነት ለተገኘበት ለክርስቶስ ምስጋና ይገባል)፤፤ ጸሎተ ሃይማኖትን ሐመ እስከ ሚለው ድረስ መድገም ነው፡፡ /ከሰኞ እስከ ረቡዕ ይባላል/

💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
    🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪    
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲ 
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ


ማስታወቂያ

🛸ሰላም የዚህ ቻናል ተከታታዮች

🧱ማስታወቂያ ማሰራት ለምትፈልጉ ብቻ 🧱

☎️ ምርትና አገልግሎታችሁን እንዲሁም አዲስ የከፈታችሁትን  ቻናል ወይም ግሩፕ ማስታወቂያ ማሰራት የምትፈልጉ የማስታወቂያውን ይዘት ተመልክተን ካረጋገጥን በኋላ በተመጣጣኝ ዋጋ የምንሰራ መሆኑን ስንገልፅ በደስታ ነው።

🚀ማስተዋወቅ የምትፈልጉትን በዚህ አድራሻ
@Zethewahdobot ላይ መላክ ትችላላችሁ።

🛑በተመጣጣኝ ዋጋ ነው😁


#ሆሳዕና
በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው  ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15)

#የዘንባባ_ዝንጣፊ፡-
☞ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አነተ ደሰታ የምታስገኝ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው አኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳእና በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡

#የቴምር_ዛፍ_ዝንጣፊ፡-
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ሂወታችን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ አካል አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንት ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው።

#የወይራ_ዛፍ_ዝንጣፊ፡-
☞ የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና።

በዓሉን በዓለ ክብር በዓለ ፍስሐ ያድርግልን፡፡
💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
    🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪    
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲ 
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ


🍀​​🌿 ሆሣዕና 🌿🍀


🌿 “ሆሣዕናስምንተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ሲኾን፣ የሰሙነ ሕማማት መጀመሪያ ነው፡፡ ሆሣዕና ስያሜው በማቴዎስ ወንጌል ፳፩፥፱ ከሚገኘው ትምህርት የተወሰደ ሲኾን ትርጕሙም መድኀኒት ወይም ‹አሁን አድን› ማለት ነው፡፡

🌿 ክብር ይግባውና አምላካችን በአህያ ጀርባ ላይ ተቀምጦ ‹‹ሆሣዕና በአርያም›› የሚሉ የአዕሩግ፣ የሕፃናት ምስጋና እየቀረበለት ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ጉዞ ያደረገበት፤ ትሕትናውን የገለጠበት፤ ይህን ዓለም ከማዕሠረ ኃጢአት መፍታቱን በምሳሌ ያስረዳበት ዕለት ነው፡፡ ‹‹ተጽዕኖ›› ተብሎ ከሚጠራው የዐቢይ ጾም መጨረሻ (ዕለተ ዓርብ) እና ከሰሙነ ሕማማት መግቢያ ጀምሮ ያለው ሳምንት ሆሣዕና ይባላል፡፡


🌿 የክርስቶስን ነገረ ሕማሙን፣ ስቅለቱን፣ ሞቱን፣ ትንሣኤውን ሆሣዕና ተብሎ ዓለምን ማዳኑን የሚናገሩ ቅዱሳት መጻሕፍት የሚነበቡበት፤ አምላካችን ለሰው ልጅ መዳን መከራ መቀበሉና የማዳን ሥራው በሰፊው የሚታወጅት፤ በሰሙነ ሕማማት ለሚያርፉ ምእመናን ጸሎተ ፍትሐት የሚደረግበት፤ ወንጌል በአራቱ ማዕዘን የሚሰበክበት ሳምንት ነው – ሆሣዕና፡፡ ከዚያው አያይዞም ሰሙነ ሕማማት ይቀጥላል፤ ወቅቱም የክርስቶስን ነገረ ሕማሙንና ዓለምን ያዳነበት ጥበቡን የምንሰማበት ሳምንት ነው፡፡

በሞቱ ሞታችንን አጥፍቶ መንግሥቱን እንድንወርስ የፈቀደልን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይኹን!🌿


💚💛❤ @Misbak_WeMahlet ❤💛💚
    🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪    
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲ 
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ




ግብረ ሕማማት


⚠️#ማሳሰቢያ!!  👫

📌 በአዲሱ የቴሌግራም ፖሊሲ መሠረት ይህን  ከታች Unmute ሚለው ላይ የሚያደርጉ አባላት ቻናሉ ላይ እንደሌሉ ይቆጠራሉ። ይህንን ማድረግ የሚፖሰቱትን እያንዳንዱ መረጃዎች የእይታ መጠን (VIEW ) ይቀንሰዋል።

ምንም እንኳን የምንፖስተውን እየተመለከቱ ቢሆንም ቻናሉ ላይ እንዳሉም አይቆጠርም ስለዚህ...🚫 ከታች #MUTE የሚለው ላይ ከሆነ ምንም አይንኩት ነገር ግን✔️ #UNMUTE ላይ ከሆነ 1 ግዜ በመንካት MUTE የሚለው ላይ አድርጉት።🔥

በተጨማሪም ቻናሉን #PIN በማድረግ ዜናዎች ሲፖሰቱ ቶሎ መረጃውን መመልከት ያስችላቹዋል 📌


የሆሳዕና ሙሉ ቃለ እግዚአብሔር ስለተለቀቀ ወደ ኋላ በመመለስ ይመልከቱ።

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.