Ministry of Revenues of Ethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


የገቢዎች ሚኒስቴር ኢኮኖሚው የሚያመነጨው ገቢ እንዲሰበስብ ኃላፊነት የተሰጠው የፌዴራል ተቋም ነው፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽንን በስሩ ይዞ ተደራጅቷል፡፡

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri




ኮንትሮባንድን ጨምሮ የተለያዩ ወንጀሎችን መቆጣጠር የሚያስችል የድሮን ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ልያውል መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አሳታወቀ

ጥር 09/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ጥቅም ላይ የሚውለው አዲሱ የድሮን ቴክኖሎጂ የኮንትሮባንድ፣ የድንደበር ላይ ጥበቃ፣ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን እና የከተማ ውስጥ ፀጥታ ቁጥጥር ሥራዎችን በብቃት ማከናወን የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በዋናው መስሪያ ቤት የተደራጀውን የድሮን ፓይለት ማሰልጠኛ ማዕከል (UAV Simulation Training Center) መርቀው ስራ ያስጀመሩ ሲሆን የድሮን ቴክኖሎጂው በተቋሙ ላለው የወንጀል መከላከል ሰርቪላንስ እና የምርመራ ስራ ከፍተኛ እገዛ እንዳለው ገልፀዋል፡፡

ኮሚሽነር ጀነራሉ አክለውም የሪፎርሙ መንግስት ለፖሊስ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ፖሊስ ዘመናዊ ትጥቆች እንዲኖሩትና ሰብዓዊ መብትን ባከበረ መልኩ የወንጀል መከላከልና የምርመራ ስራዎቻችን መስራት በሚያስችል መልኩ አቅሙን እያሳደገ ነው ብለዋል፡፡

ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ፌስቡክ ገጽ


የንግድ ሥራ ሀብት መዝገብ

ጥር 08/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ግብር ከፋዩ ያለውን የንግድ ሥራ ሀብት እንደ ዓይነቱ እና እንደ አገልግሎቱ በመለየት የሚመዘግብበት የንግድ ሥራ ሀብት መዝገብ ሊኖረው የሚገባ ሲሆን :-

📌እያንዳንዱ የንግድ ሥራ ሀብት የተገዛበት ወይም የተገኘበት ቀን እና ዋጋ፣
📌በግብር ዘመኑ የንግድ ሥራ ሀብቱን ለማሻሻል የተደረገ ማንኛውም ወጪ ከተጣራ
የመዝገብ ዋጋ ሃያ በመቶ በላይ ወይም በታች መሆኑን የሚያሳይ ስሌት \
የተከናወነበት ሰነድ፣
📌 በየዓመቱ መጨረሻ የንግድ ሥራ ሀብቱ ያለውን የተጣራ የመዝገብ ዋጋ ፣
📌 የእያንዳንዱ የተጠራቀመ የእርጅና ቅናሽ መጠን የሚያሳይ ስሌት የተከናወነበት
ሰነድ የያዘ መሆን አለበት፡፡
📌ኢንቨስትመንት የሚያካሂድ ግብር ከፋይ የኢንቨስትመንት ሥራው ተጠናቆ
የኢንቨስትመቱ አጠቃላይ ካፒታል እስኪታወቅ ድረስ በየጊዜው የሚወጣው
📌ወጪ ራሱን የቻለ መዝገብ (ledger) ሊኖረው ይገባል፡፡

በታደሰ ኢብሳ


‹‹በምንከፍለው ግብር ለህዝብ አገልግሎት የሚውሉ መሠረተ ልማቶች የሚገነቡነበት መሆኑን በመገንዘባችን ግብራችንን በወቅቱ ከፍለናል›› - ግብር ከፋዮች

ጥር 07/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በምንከፍለው ግብር ለህዝብ አገልግሎት የሚውሉ መሠረተ ልማቶች የሚገነቡ መሆናቸውን በመገንዘባችን ግብራችንን በወቅቱ ከፍለናል ሲሉ የአፋር ክልል ግብር ከፋዮች ገለጹ።

በክልሉ የሠመራ ሎጊያ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ግብር ከፋይ አቶ አንዋር መኮንን እንዳሉት እኛ የምንከፍለው ግብር መልሶ ለህዝብ ጥቅም የሚውሉ ልማቶች በጊዜያቸው እንዲጠናቀቁ ያደርጋል።

በዚሁ ግንዛቤ ግብራቸውን በጊዜው በመክፈላቸው የተለያዩ መሠረተ ልማቶች እንዲሟሉ ከማድረግ ባለፈ ለሀገር እድገት የራሳቸውን ሃላፊነት በወቅቱ እንዲወጡ እንዳስቻላቸውም ተናግረዋል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://shorturl.at/5QwJg


የንብረት ታክስ አዋጅ ፀደቀ

ጥር 07/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ጉባዔ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ከተሞች ውስጥ ተፈጻሚነት የሚኖረው የንብረት ታክስ አዋጅን በአራት ተቃውሞ በአስር ድምጸ ተዓቅቦና በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

የንብረት ታክስ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ለማስፈን፣ አገልግሎትን በተሻለ ጥራት ለማቅረብና የመሰረተ ልማት ማሻሻያዎችን በቀጣይነት ለመተግበር የሚወጣውን የኢንቨስትመንት ወጪ በንብረት ዋጋ ማደግ ምክንያት በሚጣል ታክስ አማካኝነት ለመሰብሰብ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡

የፀደቀው አዋጅ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ከተሞች ተፈጻሚነት የሚኖረው ሲሆን÷ ክልሎች አዋጁን መሰረት በማድረግ ከተጨባጭ ሁኔታቸው ጋር በተጣጣመ አኳኋን የየራሳቸውን የንብረት ታክስ ህግ እንዲያወጡ ያስችላልም ተብሏል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://shorturl.at/m663u


በግማሽ ዓመቱ የተመዘገበው የዕቅድ አፈፃፀም ስኬት አበረታች እና ተነሳሽነትን የፈጠረ መሆኑ ተገለፀ

ጥር 06/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን የ2017 በጀት ዓመት የገቢ አሰባሰብ ተግባርን በስኬት ለማከናወን አቅድው ወደ ተግባር መግባታቸው በእቅድ አፈፀፃም ግምገማ መድረክ የተጠቀሰ ሲሆን በዚህም በግማሽ ዓመቱ የተመዘገበው የዕቅድ አፈፃፀም ስኬት አበረታች እና መነሰሳትን የፈጠረ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በገቢዎች ሚኒስቴር የስትራቴጂክ ፕላንና ፕሮጀክት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ተሰማ የሚኒስቴሩን የስድሰት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖረት በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን በተለይም በማሰፈፀም አቅም ግንባታ፣ በታክስ ህግ ተገዥነትና አገልግሎት አሰጣጥ፣ በገቢ አሰባሰብ ስራዎች እንዲሁም በአፈፃፀም ሂደት ያጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ ገለፃ አድርገዋል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://shorturl.at/BlQHa


«ገቢ ለልማት» ጋዜጣ

ጥር 06/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ውድ የጋዜጣችን አንባቢዎች፤ እንደተለመደው «ገቢ ለልማት» ጋዜጣ ቁጥር 179/2017 ዓ.ም እትም ከየካቲት 3 ቀን ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ስለሚተገበረው ባለልዩ መለያ ደረሰኝ ጨምሮ ብዙ ጠቃሚ መልዕክቶችን ይዞ ቀርቧል፡፡

በመሆኑም ጋዜጣዋን በሚኒስቴሩ የፌስቡክ፣ ቴሌግራም እና ዌብሳይት ገጽ እንዲሁም ህትመቷ በነጻ እየተሰራጨባቸው ባሉ የገቢዎችም ሆነ ጉምሩክ ዋና መ/ቤቶች እና ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች፤ በከተማ አስተዳደር እና ከክልል እስከ ወረዳ ባሉ የገቢው ዘርፍ ጽ/ቤቶች በመውሰድ እንድታነቡ ጋብዘናችኋል፡፡

ጋዜጣውን ለማገኘት ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ፡-

https://shorturl.at/qWSi2



8 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.