የአማራ ክልልን ከትግራይ ክልል ጋር የሚያገናኘው የሃሚድ ወንዝ የብረት ድልድይ ትናንት ከሰዓት በኋል በደረሰበት ጉዳት ፈረሰ።አማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ከቆቦ ከተማ 14 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘዉ ድልድይ ሁለቱን ክልልሎች ለማገናኘት ትልቅ አገልግሎት ይሰጥ ነበር።የሰሜን ወሎ ዞን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ እንዳስታወቀዉ ድልድዩ በመፍረሱ ከወልዲያ ቆቦ፣ አላማጣ፣ ኮረም መቀሌ የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጧል ።
የመምሪያው ኃላፊ አቶ መብራቱ አሰፋ ለዶይቼ ቬሌ በስልክ እንደነገሩት ትናንት ከ9 እስከ 10 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ የድንጋይ ከሰል የጫነ ባለ ተሳቢ ከባድ መኪና ከወልድያ ወደ መቐለ ሲጓዝ ድልድዩን በመሻገር ላይ እንዳለ የመኪናውን ክብደት መሸከም ባለመቻሉ ድልድዩ ተሰብሯል። ዘገባዉን የላከልን አለምነው መኮንን ነዉ።