በመሬት መንቀጥቀጥ “ከፍተኛ ጉዳት” የደረሰበት የከሰም ስኳር ፋብሪካ፤ ሰራተኞቹን በመጪዎቹ ወራት ሊያሰናብት ነው
ባለፉት ወራት በተደጋጋሚ በተከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጦች “ከፍተኛ ጉዳት” የደረሰበት የከሰም ስኳር ፋብሪካ፤ ከአንድ ሺህ በላይ ሰራተኞቹን እስከ መጪው ግንቦት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ለማሰናበት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።
የስኳር ፋብሪካው የሰራተኞች ማህበር በበኩሉ ሰራተኞቹ ሳይሰናብቱ ወደ ሌሎች ፋብሪካዎች እንዲበተኑ ለማድረግ ጥረት እያደረገ መሆኑን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስታውቋል።
በስሩ ከአራት ሺህ በላይ ሰራተኞችን የሚያስተዳድረው የከሰም ስኳር ፋብሪካ፤ የቅድመ ማስጠንቀቂያ በመስጠት የሰራተኞቹን የስራ ውል ያቋረጠው ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ የካቲት 11፤ 2017 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ ነው።
በፋብሪካው የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ የተለጠፈው እና “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው ይህ ማስታወቂያ፤ የስራ ውላቸው የተቋረጠ ከአንድ ሺህ በላይ ሰራተኞችን ስም ዝርዝር የያዘ ነው።
የከሰም ስኳር ፋብሪካ የሰው ሀብት ስራ አመራር እና አቅርቦት ዘርፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ዝናቡ ብርሃኑ ፊርማ ያረፈበት ማስታወቂያ፤ ፋብሪካው ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከታህሳስ 20 ጀምሮ በተደጋጋሚ የተከሰተው ርዕደ መሬት ባስከተለበት “ከፍተኛ ጉዳት” መሆኑን ያስረዳል።
የስኳር ፋብሪካው በዚህ ምክንያት “ስራውን ሙሉ ለሙሉ ያቆመ በመሆኑ”፤ በማስታወቂያው ስማቸው የተዘረዘረ ሰራተኞቹ የስራ ውል ከየካቲት 10፤ 2017 ጀምሮ “በቅደመ ማስጠንቀቂያ” መቋረጡንም አትቷል።
ይሁንና በዚያው ዕለት ፋብሪካው ማስተካከያ በማድረግ በለጠፈው ማስታወቂያ፤ ሰራተኞቹ ከየካቲት 10 ቀን ጀምሮ መሰናበታቸውን በማስቀረት ከዚሁ ቀን ጀምሮ እንደ የአገልግሎት ቆይታቸው ቅድመ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መሆኑን ገልጿል።