(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል አበበ ተክለ ሃይማኖት (ጆቤ)፣ "ከ28 ዓመታት በፊት በተካሄደው የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት ሻዕቢያን የመደምሰስ አቅም የነበረ ቢሆንም ይህ አለመደረጉ ትልቅ ስህተት ነበር" አሉ።
የቀድሞው የአየር ኃይል ዋና አዛዥ፣ ከዚያ በኋላ በነበሩት 18 ዓመታት የተሠራው ጠላትን በዝምታ የማቆየት ትልቅ ስህተት ከባድ ዋጋ ማስከፈሉን ተናግረዋል፡፡ በተለይም በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የትግራይ ሕዝብ ዋጋ እንዲከፍል ምክንያት ሆኗል ብለው፣ አሁንም ጦርነት ከተቀሰቀሰ የትግራይ ክልል የጦርነት ዓውድማ ሊሆን የሚችልበት ዕድል ሰፊ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያና የኤርትራ ግንኙነት መጀመሪያውንም ያልተቀደሰ ግንኙነት እንደነበር ጠቁመው፣ ወደ ግጭት ሊያመሩ እንደሚችሉ የሚያመላክቱ ፍንጮች እንዳሉ ገልጸዋል።