«የታሰሩ ሙስሊም ተማሪዎች ዜና!
እለተ ማክሰኞ ጥቅምት 2017 E.C.
በኒቃብ ጉዳይ ከታሰሩት የአዲስ ከተማ ት/ቤት ሙስሊም ተማሪዎች መካከል አንዱ የሆነው ተማሪ አሚር አ/ከሪም ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር፤ ተማሪ አሚር በት/ቤት ውስጥ ት/ቱን በአግባቡ በመከታተል እና ተማሪዎች በአካዳሚም ይሁን በዲናዊ ህይወታቸው የተሻሉ እንዲሆኑ በመምከር የሚታወቅ አርአያ ተማሪ ሲሆን፤ ከት/ቤቱ ሙስሊም ተማሪዎች ጋር አብሮ እህቶቻችን ለምን ኒቃብ መልበስ ይከለከላሉ ብሎ በሰላማዊ መንገድ በመጠየቁ ብቻ ት/ቤቱ በከፈተው የውሸት ክስ እለተ አርብ በትምህርት ገበታ ላይ እያሉ ስም ዝርዝራቸው ለፖሊስ ተሰጥቶ በየክፍላቸው እየተዞረ ከተለቅሙት ሙስሊምች ተማሪዎች አንዱ ነበር።
በዛሬው እለት በዋለው ችሎት አቃቢህጉ ት/ቤቱን በማስረበሽ እና የት/ቤት ንብረትን በማውደም የሚል የውሸት ክስ በተማሪ አሚር አ/ከሪም ላይ ያቀረበ ሲሆን ከአዲስ አበባ መጅሊስ ተወክሎ የቆመለት ጠበቃ ሁሴንም በችሎቱ ላይ ባቀረበው ብርቱ ክርክር የዋስ መብቱ ተጠብቆ በመጨረሻም በ5ሺ ብር ዋስ እንዲፈታ ተወስኗል፤ በቅድሚያ አላህን እናመሰግናለን በመቀጠል ለአዲስ አበባ መጅሊስ እና ለጠበቃ ሁሴን ምስጋናችን ይድረስ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ተማሪ ነቢል እና ተማሪ ሰሚር በመጪው ሀሙስ ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ሲሆን የክስ መዝገብ ላይ ስማቸው ሰፍሮ ያልተያዙ ሙስሊም ተማሪዎች አሁንም ድረስ በፖሊስ እየተፈለጉ በመሆኑ ሁሉም የት/ቤታችን ሙስሊም ተማሪዎች በነፃነት የመማር መብታቸው ተከብሮ ወደ ቀድሞው የትምህርት ገበታቸው እስኪመለሱ ድረስ ሁሉም ሙስሊም የሚችለውን አስፈላጊ ትብብር እንዲያደርግልን በአላህ ስም እንጠይቃለን።
ኒቃቧንም ትለብሳለች‼️
ትምህርቷንም ትማራለች‼️»
©: የአዲስ ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዐ