በምድር በላይ በደል ፥ በተንሰራፋበት፣
የጣዖት አምልኮ ፥ ጫፍ በደረሰበት፣
ጎሳ ከጎሳ ጋ ፥ በሚጋደልበት፣
ባለሃብት ደሃውን ፥ በሚጨቁንበት፣
ሴት ልጆችን መውለድ ፥ ወንጀል በሆነበት፣
ደጋግ የአላህ ባሮች ፥ መጠጊያ ባጡበት፣
የባርነት ቀንበር ፥ ድካ ባለፈበት፣
ምድር አልችል ብላ ፥ የፈሳዱን ብዛት፣
በድቅድቅ ጨለማ ፥ በተሞላችበት፣
ውዱን ነቢይ ሰጠን ፥ ለዓለማት እዝነት።
በእርሳቸው መላክ ፥ ጨለማው ተገፏል፣
የተውሒዱ ፋኖስ ፥ እስከ ጥግ አብርቷል፣
የተጋጨ ጎሳ ፥ ወንድማማች ሆኗል፣
የባርነት ቀንበር ፥ ቀስ በቀስ አክትሟል፣
የተውሒዱ ጮራ ፥ ዓለምን አዳርሷል፣
የኡማው አንድ አካል ፥ ክብሯ ተመልሷል።
ከ'ናት አባት በላይ ፥ ለኛ ተቆርቋሪ፣
መጥፎ ሠሪዎችን ፥ በ'ሳት አስፈራሪ፣
መልካም ሠሪዎችን ፥ በጀነት አብሳሪ፣
በሁሉም ሁኔታ ፥ በጎ ተናጋሪ፣
ክፉ 'ማይወጣቸው ፥ ጀግና ትጉህ መሪ፣
በየመንገዳቸው ፥ ወደ ተውሒድ ጠሪ።
ስነ ምግባራቸው ፥ ምን ቃል ይገልፀዋል፣
እንኳን ወዳጃቸው ፥ ጠላትም ያውቀዋል፣
በበጎነታቸው ፥ ብዙውን ማርከዋል፣
የበደሏቸውን ፥ በይቅር አልፈዋል፣
ቁርኣንን ኑረው ፥ ለኛ አስተምረዋል።
ገና ሳንወለድ ፥ በዓይናቸው ሳያዩን፣
"ወንድሞቼ" ብለው ፥ "ናፍቀውኛል" አሉን።
ይገባን ይሆን ወይ ፥ ይሄ ሁሉ ፍቅር፣
ከተዘፈቅንበት ፥ ካለንበት አንፃር?
ጥለውን ሄደዋል ፥ ፍንትው ባለ መንገድ፣
ሐቁን አብራርተዋል ፥ ሁሉንም አንድ'ባንድ፣
አደራ ብለዋል ፥ ከዚህ እንዳንለቅ፣
እስከፍፃሜያችን ፦ ዱንያን እስክንለቅ።
ሐቃቸው አለብን ፥ ልንከተላቸው፣
ከነፍስያችንም ፥ ልናስበልጣቸው፣
ከናት አባት በላይ ፥ የምር ልንወዳቸው፣
በተጠሩ ቁጥር ፥ ልናወድሳቸው።
ባሰመሩት መስመር ፥ ቀጥ ብለን ልንጓዝ፣
ያዘዙንን እንጂ ፥ ያላሉንን ላንይዝ፣
ያፈነገጥን እንደሁ ፥ አለው ትልቅ መዘዝ።
መጸጸት ብቻውን የማይጠቅምበት ቀን ፥ ከመምጣቱ በፊት፣
ከሺርክ እንውጣና ፥ ከቢድዓህ አዙሪት፥፣
በሱንናቸው መንገድ ፥ ተሳስረን በአንድነት፣
በተውሒድ ጎዳና ፥ እንጓዝ ወደፊት።
ያኔ እንሆናለን ፥ የምር ተናፋቂ፣
የሐውዳቸው ቀማሽ ፥ አደራ ጠባቂ፣
ሚዛናዊ ህዝቦች ፥ ግሩም አስደናቂ።
አላህ ይዘንልን ፥ መንገዱን ያግራልን፣
ከተዘፈቅንበት ፥ በቶሎ ያስወጣን፣
የሚደሰትብን ፥ ምርጥ ባሮች ያር'ገን፣
የዓለማቱን እዝነት ፥ በጀነት ያሳየን፣
የርሱን ፊት ተመልካች ፥ ወዳጆቹ እንሁን።
||
t.me/MuradTadesse
የጣዖት አምልኮ ፥ ጫፍ በደረሰበት፣
ጎሳ ከጎሳ ጋ ፥ በሚጋደልበት፣
ባለሃብት ደሃውን ፥ በሚጨቁንበት፣
ሴት ልጆችን መውለድ ፥ ወንጀል በሆነበት፣
ደጋግ የአላህ ባሮች ፥ መጠጊያ ባጡበት፣
የባርነት ቀንበር ፥ ድካ ባለፈበት፣
ምድር አልችል ብላ ፥ የፈሳዱን ብዛት፣
በድቅድቅ ጨለማ ፥ በተሞላችበት፣
ውዱን ነቢይ ሰጠን ፥ ለዓለማት እዝነት።
በእርሳቸው መላክ ፥ ጨለማው ተገፏል፣
የተውሒዱ ፋኖስ ፥ እስከ ጥግ አብርቷል፣
የተጋጨ ጎሳ ፥ ወንድማማች ሆኗል፣
የባርነት ቀንበር ፥ ቀስ በቀስ አክትሟል፣
የተውሒዱ ጮራ ፥ ዓለምን አዳርሷል፣
የኡማው አንድ አካል ፥ ክብሯ ተመልሷል።
ከ'ናት አባት በላይ ፥ ለኛ ተቆርቋሪ፣
መጥፎ ሠሪዎችን ፥ በ'ሳት አስፈራሪ፣
መልካም ሠሪዎችን ፥ በጀነት አብሳሪ፣
በሁሉም ሁኔታ ፥ በጎ ተናጋሪ፣
ክፉ 'ማይወጣቸው ፥ ጀግና ትጉህ መሪ፣
በየመንገዳቸው ፥ ወደ ተውሒድ ጠሪ።
ስነ ምግባራቸው ፥ ምን ቃል ይገልፀዋል፣
እንኳን ወዳጃቸው ፥ ጠላትም ያውቀዋል፣
በበጎነታቸው ፥ ብዙውን ማርከዋል፣
የበደሏቸውን ፥ በይቅር አልፈዋል፣
ቁርኣንን ኑረው ፥ ለኛ አስተምረዋል።
ገና ሳንወለድ ፥ በዓይናቸው ሳያዩን፣
"ወንድሞቼ" ብለው ፥ "ናፍቀውኛል" አሉን።
ይገባን ይሆን ወይ ፥ ይሄ ሁሉ ፍቅር፣
ከተዘፈቅንበት ፥ ካለንበት አንፃር?
ጥለውን ሄደዋል ፥ ፍንትው ባለ መንገድ፣
ሐቁን አብራርተዋል ፥ ሁሉንም አንድ'ባንድ፣
አደራ ብለዋል ፥ ከዚህ እንዳንለቅ፣
እስከፍፃሜያችን ፦ ዱንያን እስክንለቅ።
ሐቃቸው አለብን ፥ ልንከተላቸው፣
ከነፍስያችንም ፥ ልናስበልጣቸው፣
ከናት አባት በላይ ፥ የምር ልንወዳቸው፣
በተጠሩ ቁጥር ፥ ልናወድሳቸው።
ባሰመሩት መስመር ፥ ቀጥ ብለን ልንጓዝ፣
ያዘዙንን እንጂ ፥ ያላሉንን ላንይዝ፣
ያፈነገጥን እንደሁ ፥ አለው ትልቅ መዘዝ።
መጸጸት ብቻውን የማይጠቅምበት ቀን ፥ ከመምጣቱ በፊት፣
ከሺርክ እንውጣና ፥ ከቢድዓህ አዙሪት፥፣
በሱንናቸው መንገድ ፥ ተሳስረን በአንድነት፣
በተውሒድ ጎዳና ፥ እንጓዝ ወደፊት።
ያኔ እንሆናለን ፥ የምር ተናፋቂ፣
የሐውዳቸው ቀማሽ ፥ አደራ ጠባቂ፣
ሚዛናዊ ህዝቦች ፥ ግሩም አስደናቂ።
አላህ ይዘንልን ፥ መንገዱን ያግራልን፣
ከተዘፈቅንበት ፥ በቶሎ ያስወጣን፣
የሚደሰትብን ፥ ምርጥ ባሮች ያር'ገን፣
የዓለማቱን እዝነት ፥ በጀነት ያሳየን፣
የርሱን ፊት ተመልካች ፥ ወዳጆቹ እንሁን።
||
t.me/MuradTadesse