የት ይደርሳል የተባለውን ዛፍ ቀበሌ ቆረጠው አለ አንድ የኛ ሰፈር ቀልደኛ የፋሲል እንዲህ ተራ ጋዜጠኛና መሆኑና ብሽሽቅ ውስጥ የገባ በመሆኑ አዝናለሁ::
#FactCheck ይህ ቪዲዮ የ4 ኪሎ-ፒያሳ ኮሪደር ልማት ወቅታዊ ይዞታን አያሳይም
በፌስቡክ ከ160 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ‘ፋሲል የኔዓለም’ የተባለ ግለሰብ በአዲስ አበባ ከተማ በመሰራት ላይ ከሚገኙ የኮሪደር ልማቶች መካከል የአንዱን ወቅታዊ ይዞታ ያሳያል ያለውን ቪዲዮ ማጋራቱን ተመልክተናል።
ቪዲዮው ከቲክቶክ የተወሰደ ሲሆን “ዛሬ ያለቀው 1ኛው የኮሪደር ልማት በአራት ኪሎ” የሚል ጽሁፍ ይነበብበታል።
ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት ከላይ የተጠቀሰው ቪዲዮ የኮሪደር ልማቱ ከመጀመሩ በፊት የተቀረጸ መሆኑን አረጋግጧል።
ቪዲዮው የሚያሳየው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 4 ኪሎ ግቢ ዋና በር ፊት ለፊት ያለው አካባቢ ሲሆን በቪዲዮው ላይም የ4 ኪሎ-ፒያሳ የኮሪደር ልማት በተጀመረ የመጀመሪያዎቹ ቀናት የፈረሱ ህንጻዎች ይታያሉ።
ከነዚህም መካከል በቀይ ቀለሙ ጎላ ብሎ የሚታየውና ‘ኮርዲያል ካፌ’ ይገኝበት የነበረው ህንጻ ይገኝበታል። በተጨማሪም ከቀዩ ህንጻ ጎን የነበረው አባድር ሱፐር ማርኬትም በተመሳሳይ ወቅት መፍረሱ ይታወቃል። ኢትዮጵያ ቼክ በወቅቱ የህንጻዎቹን ፈረሳ መታዘብ ችሎ ነበር።
ይህም ከላይ የተጠቀሰው የፌስቡክ አካውንት ያጋራው ቪዲዮ የ4 ኪሎ-ፒያሳ ኮሪደር ልማት ከመጀመሩ ቀደም ብሎ የተቀረጸ መሆኑን ያረጋግጣል።
በአዲስ አበባ ከተማ በመሰራት ላይ ከሚገኙ የኮሪደር ልማቶች መካከል አንዱ የሆነው የ4 ኪሎ-ፒያሳ ፕሮጀክት መጠናቀቁን የከተማዋ ከንቲባ ማስታወቃቸው ይታወሳል።