በአንካራው ስምምነት የታደሰው የኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎት
የአንካራው ስምምንት ኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ ስታቀርበው ለነበረው እና አብዛኛውን ጊዜ ትኩረት ሳያገኝ ለቆየው የባህር በር ጥያቄዋ ምላሽ የሰጠ፣ በሀገሪቱ ዲፕሎማሲያዊ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑ እየተገለጸ ይገኛል።
በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የአፍሪካ ጉዳዮች ጥናት ዳይሬክተር ጄኔራል ግዛቸው አስራት (ዶ/ር) በዚሁ ጉዳይ ላይ ባቀረቡት ጽሑፍ፣ “በሶማሊያ እና በቱርኪዬ እንዲሁም በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና ሀገራት እውቅና የተሰጠው ይህ ስምምነት፣ የኢትዮጵያን የባህር በር መሻት ሕጋዊነት ያረጋገጠ፣ ጉዳዩን በዓለም አቀፍም ሆነ ቀጠና አቀፍ መድረኮች ላይ ማንሣት እንደነውር ይቆጠር የነበረውን አስተሳሰብ የሰበረ ነው” ሲሉ ገልጸውታል።
ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው የአፍሪካ ቀንድ የለውጥ እርምጃ መሆኑን ጠቁመው፣ በተለይ ደግሞ ለኢትዮጵያ ላለፉት 30 ዓመታት ሊደረስበት የማይችል ነው የተባለውን ግብ በማደስ ረገድ ሥልታዊ እመርታ ነው ይላሉ።