“ወደ አዲስ አበባ ጉዞ በምናደርግበት ሰዓት 10:30 መሰለኝ... [ኬላ እንደነበረ አላውቅም] ኬላ ተደርጎ ነበር... እንግዲህ እኔ በአጀብ ነው የምሄደው። ኬላ ሲያስቆሙ፣
የኔ ጠባቂዎች ‘የምን ኬላ ነው?’ የሚል ጥያቄ አቀረቡ።
አጃቢዎቼ ‘የፕሬዜዳንቱ ነው መኪናው’ ሲሏቸው፣
‘አይ! ማጣራት እንፈልጋለን እንደውላለን’ አሉ።
ከዛ እኔ መስኮት ከፈትኩና፤
‘ማን ጋር ነው የምትደውሉት የኔን ጉዞ በሚመለከት??...’ ስል እዛ አካባቢ ሲያስተባብር የነበረው ወጣት [የሠራዊት ኃላፊ ይመስለኛል] እኔን እንዳየ መከራከር አልፈለገም...መንገዱን ከፍተውልን ሄድን።
...ኤርፖርት ገባሁ። አውሮፕላን በምንሳፈርበት ሰዓት እዚህ ግባ የሚባል ምንም ነገር አልነበረም። አውሮፕላን ውስጥ ከገባን በኋላ የገባን ነገር ምንድነው? የዛ አካባቢ ይሄን ኃላፊነት የወሰደ ከፍተኛ የሠራዊት ኃላፊ፣
‘እንዴት ታሳልፉታላችሁ’ በሚል ደንፍቶ... ፓትሮል ይዞ ኤርፖርት ድረስ እንደመጣ... በኋላ ሰማን።
እኔ ምንም ‘ኖቲስ’ አላደረኩም... ፓትሮል ይዞ መምጣት ብቻ ሳይሆን የፌዴራል ፖሊስ የሚጠብቀውን ኤርፖርት... የፌዴራል ፖሊስን ጥሶ መግባት አይችልም.. ወይ ወደ ግጭት ይገባል። የኔም አጃቢዎች አሉ። ያኔ ወደ ግጭት ይገባል። ወደ ግጭት ከተገባ የሚፈጠረውን ነገር እርግጠኛ መሆን አይቻልም። በቁጥር የኔ አጃቢዎች የሚበልጡ ይመስለኛል። የኔ ጠባቂዎች ደስ የማይል ነገር እየተፈጠረ እንደሆነ ገምተዋል.... ግን መመለስና መሟገት አንችልም።
አውሮፕላኑ ተነስቶ ሄድን.... አዲስ አበባ እንደገባን የነበረውን ሁኔታ ስናጣራ ኬላው ዝም ብሎ ተራ ኬላ እንዳልነበር... [በነገራችን ላይ ምንም አይነት ኬላ መንግሥት ሳያውቀው መቀመጥ አይችልም] እዛ አካባቢ ያሉ የጦር ኃላፊዎች ብቻቸውን ያደረጉትም አልነበረም... ከበላይ በተሰጠ ትዕዛዝ ነው ኬላ የተደረገው። ያ ፓትሮል ይዞ የመጣው የሠራዊት ኃላፊ የአየር መንገድ [አቬዬሽን ሴኩሪቲ] አባል ጋር ስልክ ደውሎ ‘እሱ ብቻ ነው? ወይስ ሌሎችንም ይዞ ነው እየወጣ ያለው?’ የሚል ጥያቄ ሁሉ እንደጠየቀው አውቃለሁ።
ከዛ በኋላ ያወኳቸውን መረጃዎች ግምት ውስጥ በማስገባት ምናልባት ጫን ያለ ሥራ ለመስራት ፍላጎት እንደነበራቸው፣ እንዲህ ያለው ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ምንም ነገር ባይፈጠር ጭምር እጅግ እጅግ አደገኛና ተቀባይነት የሌለው ተግባር እንደሆነ ብቻ ነው የማውቀው።
ከዛ እስከወጣሁበት፣ አውሮፕላን ላይ እስከ ተሳፈርንበት ሰዓት ድረስ ኬላውን ጭምር አይቼ... ይሄን ያክል ህይወቴን አደጋ ላይ የሚጥል ነው ሳይሆን፣ ምናልባት የተለዩ እንቅስቃሴዎች ይኖራሉ... ከዛ ጋር የተያያዘ ነው የሚል እምነት ነበረኝ። ከወጣሁ በኋላ የእነሱ ደጋፊዎች የሆኑ ስለማምለጤ በተደጋጋሚ ሲያወሩ ስሰማ ግን ምናልባትም አምልጬ መምጣቴ ወይም ማምለጤ ነው የገባኝ - ሀሳቤ የማምለጥ የነበር ባይሆንም። ደጋፊዎቻቸው እና እነሱ የሚከፍሏቸው የሚዲያ ተቋማት ስለ ማምለጤ ሲያወሩ ምናልባትም ይዘውት የነበረ እቅድ መክሸፉን ራሳቸው ናቸው እያጋለጡ ያሉት እንጂ እስከዛ ድረስ የማውቀው አልነበረም።”
ጌታቸው ረዳ በርዕዮት ሚዲያ ላይ ከተናገሩት