+ መስቀልም ምስጋና ይገባዋል ማለት...
ሠሞኑን ከምንሰማቸው ትችቶች አንዱ "መስቀል መከበሩንስ ይከበር፤ ግን እንዴት እንደሚሰማ አካል ምስጋና ይቀርብለታል?" የሚል ይገኝበታል። ይህም "ስብሐት ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ፤ ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልም ምሥጋና ይገባል፤" የሚለውን እና ተመሳሳይ የቤተ ክርስቲያን ጸሎቶችን በመተቸት ነው።
ይህ ትችት መጽሐፍ ቅዱሳዊውን የንግግር ዘይቤ ያለማወቅ (ወይም ሆን ብሎ ማሳሳት) የሚያመጣው ችግር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ መስማት የማይችሉ ነገሮችን እንደሚችሉ ቆጥሮ ቅኔያዊ በሆነ መንገድ (personification) ይናገራል። ለምሳሌ ሊቀ ነቢያት ሙሴ "ሰማያት ሆይ፥ አድምጡ፥ እኔም እናገራለሁ፤ ምድርም የአፌን ቃሎች ትስማ፤" ይላል። (ዘዳግም 32÷1) ክቡር ዳዊትም ጌታችን የተጠመቀባትን ዮርዳኖስን በትንቢት ቃል ያወራታል፦ "አንቺ ባሕር የሸሸሽ፥ አንቺም ዮርዳኖስ ወደ ኋላሽ የተመለስሽ፥ምን ሆናችኋል?" (መዝሙር 114/115÷5) ሰሎሞንም በምሳሌው ጥበብን እየዞረች የምትናገር ሴት አድርጎ ያቀርባታል፦ "ጥበብ በጎዳና ትጮኻለች፤ በአደባባይ ድምፅዋን ከፍ ታደርጋለች፤" (ምሳሌ 1÷20)
መስቀልም ምስጋና ይገባዋል ስንል የሚሰማ እና ነፍስ ያለው (personal) አድርገነው ሳይሆን እግዚአብሔር ትልቅ ሥራ የሠራበት ክቡር ነገር መሆኑን ጠለቅ ባለ ቅኔያዊ ቋንቋ የተገለጸበት መንገድ ነው። ሥርዓተ አምልኮ እግዚአብሔርን እና የከበሩ ሥራዎቹን የምንናገርበት እና ምሥጋና የምናቀርብበት ልባዊ ግብር በመሆኑ ጥልቅ እና ቅኔያዊ አገላለጾች አስፈላጊ ናቸው። በሥርዓተ አምልኮ ቀጥተኛ (plain) ቋንቋ ብቻ መጠቀም ለግብሩ ታላቅነት አይመጥንምና።
(በረከት አዝመራው)
#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ