ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም!!!ድንግል_ሆይ ❤️የሚወዱሽ የተወደዱ ናቸው።
ንግስት_ሆይ ❤️የሚያከብሩሽ የከበሩ ናቸው።
ንፅሕት_ሆይ ❤️የሚቀድሱሽ የተቀደሱ ናቸው።
ፍስሕት_ሆይ ❤️የሚመርቁሽ የተመረቁ ናቸው።
ልዕልት_ሆይ ❤️የሚያደንቁሽ የተደነቁ ናቸው።
ውድስት_ሆይ ❤️ለንግሥትነትሽ የሚገዙ ሁሉ የተባረኩ ናቸው።
ቤዛዊት አለም ድንግል_ሆይ ❤️
ንፅህናን እንደ መላዕክት የለበሽ ፣ እንደ ነብያት መንፈስ ቅዱስን የተሞላሽ ፣ አሸናፊ በሚሆን በልዑል እግዚአብሔር እጅ የታነፅሽ የመለኮት ማደሪያ ነሽ። ስለዚህ ክብርት ነሽ እናከብርሻለን
ቤዛዊት አለም ድንግል ሆይ ❤️ባንቺ ያመንን ልጆችሽን ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ አድኝን። ከልጅሽ ከወዳጅሽ አማልጂን🙏
አሜን አሜን አሜን 🙏🙏🙏
በወላዲተ አምላክ የነገረ ድኅነት ሱታፌ ላይ በጳጳስ ደረጃ ሲቀለድ አይተን ዝም ልንል አንችልም:: ከቅዱስ ሲኖዶስ ጠንከር ያለ ውሳኔ እንጂ ማስተባበያ አንጠብቅም:: የተነቃነቀ ጥርስ ቀን ይጠብቃል እንጂ መውለቁ አይቀርም:: እንደ ተራ ስኅተት ይቅርታ እንዲጠይቁም አንጠብቅም:: ያስተማሩት የታሰበበት ክህደት ነውና የተብራራ መልስ ከቀኖና ጋር እንጠብቃለን:: "የበራላቸው" ለመባል
የብርሃን እናትን ሊጋርዱ የሚጥሩ ሰዎች ማላገጫ ሆነንም አንቀርም!!! •✥• •✥• •✥• •✥• •✥•
@ortodox_27