አንድ አንድ ግዜ ሀገር ሰላም ብላችሁ ተኝታችሁ በጣም አስፈሪ! ሰው አትሉት አውሬ በዱር በገደሉ ያራውጣችሁአል። ከያዛችሁ እንደሚገላችሁ ስለምታውቁ ባለ በሌለ ሀይላችሁ እሮጣችሁ ማምለጥ ትፈልጋላችሁ ግን የመሮጥ አቅም አይኖራችሁም እግራችሁ ሽባ ይሆናል፣ መጮህ ትፈልጋላችሁ ድምፃችሁ ግን ይዘጋል😢 ያ እምትፈሩት ነገርም ካሁን አሁን ደረሰብኝ፣ገደለኝ ብላችሁ ስትጨነቁ በሆነ ምክንያት ከቅዠታችሁ ብንን ትላላችሁ።
ከሞት ጠአር እማይተናነስ ከቅዠታችሁ ለመንቃት ባደረጋችሁት መፍጨርጨር ብዛት ሰውነታችሁ በላብ ተጠምቆ ታገኙታላችሁ
ፊልም የመሰለ አስፈሪ ቅዠት!
ቅዠት መሆኑን ስታውቁ አማትባችሁ እንደገና ሰላም ያለው እንቅልፍ ትተኛላችሁ።
ህይወትም ልክ እንደዚህ ቅዠት ለብዙዎቻችን ከባድ ናት። እምናልመው ሌላ እምንኖረው ህይወት ሌላ ይሆንብናል። መሮጥ መቅደም ትፈልጋላችሁ ግን እሮጣችሁ እንዳትቀድሙ ብዙ መሰናክሎች ከፊት ያደናቅፋችሁአል፣ እንዳትሮጡ ከሁኣላ ጨርቃችሁን እሚጎትቱት ጋሬጣዎች ብዙ ናቸው።
ግን አንድ ነገር እመኑ እግዚአብሔርን ተስፋ ካደረጋችሁ ከዚህ አስፈሪ ህይወት ተላቃችሁ እምትፈልጉትን ህይወት ትኖራላችሁ።
ከዛ አስፈሪ ቅዤት ለማምለጥ ያደረጋችሁትን መፍጨርጨር ግን እውነተኛው ህይወታችሁም ላይ እግዚአብሔርን ይዛችሁ መድገም ይጠበቅባችሁአል።
" አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? እግዚአብሔር አይደለምን? ትዕግሥቴም ከአንተ ዘንድ ነው።"
(መዝሙረ ዳዊት 39:7)
🌷እንደምን አደራችሁ ቤተሰብ☦🌺