#ቀን_ሲጥል
አባዬ ብዙ ካሰላሰለ በኃላ ወደ ኪያር ዞረና ኪያር መኪና መንዳት ትችላለህ ብሎ ጠየቀው አው እችላለው ጋሼ አለው አባዬ የመኪናውን ቁልፍ አቀበለውና በል በቃ ደርሳችው ነገውኑ ዊዝድሮው እንደጨረሳችው ይዘኀው ተመለስ አደራ በጣም ተጠንቀቁ ብሎን ሄደ ልክ አባዬ የውጪውን በር ከፍቶ እንደወጣ yessss..ብዬ ከመቀመጫዬ ተነስቼ ዘለልኩ ወደ ሰሙ እያየው አይ ሰሙ መለኛ እኮ ነሽ ማነው በናትሽ ውሸት እንዲ ያስተማረሽ በአንዴ እዚው ፈጥረሽ አሳመንሽው እኮ አልኳት ሰሙ ኮስተር ብላ እየቀለድኩ አይደለም ናዲ እኔ የእውነቴን ነው የተናገርኩት ዊዝድሮው ሞልተህ ተመለስ እዛ ስንሄድ ምንም ነገር እንዳታደርግ just ዊዝድሮው ሞልተህ ነገውኑ ትመለሳለህ ተናግሪያለው አባትህ ለኛ ነው አደራ ብለውን የሄዱት ምንም ነገር እንዲፈጠር አልፈልግም አለችኝ እሺ ችግር የለውም ግን አንድ ነገር.ላስቸግርሽ እዛ ስንሄድ ኤቤጊያን እንድታገናኚኝ ብቻ ነው እምፈልገው ሌላ ምንም አልፈልግም አልኳት እእህህህህ ለካ ለሷ ብለህ ነው ናዝሬት እምትመጣው አለችኝ ልዋሻት ስላልፈለግኩ አዎ አልኳት እየተናደደች እሺ አለችኝ።
ከሰአቱን ከቤት ወጥተን እዛው ቦሌ አከባቢ ዞር ዞር ብለን ስንዝናና ዋልን ያው እኔ ከቤት ወጥቼ ስለማላውቅ እኔን ለማዝናናት ታስቦ ነው ታናሽ እህቴም አብራን ነበረች እኔና ሰሙ ከኃላ ቀስእያልን ወክ እናረጋለን መሃል ላይ ራኬብ እና ሊዲያ አንድ ላይ እያወሩ ናቸው ኪያር እና እህቴ ደሞ ከፊት ሆነው ይሄዳሉ። እዛው ከሰፈራችን ብዙም የማይርቅ ካፌ ገብተን ስንጨዋወት 11፡00 ሰአት ሆነ ሁላችንም ወደቤት ተመለስን እህቴ ስትቀር ሁላችን ናዝሬት ልንሄድ ተነሳን እናቴ ያዘጋጀችልኝን ትንሽዬ ሻንጣ መኪናው ውስጥ አስገባው እነሰሙም ቦርሳቸውን ምናምን ይዘው ከኃላ ገቡ ኪያር ቁልፉን ተጭኖ መኪናዋን አስነሳ እኔ እናቴን ቻው ብያት ወደመኪና ስሄድ ጠንቀቅ በል እሺ የትም እንዳታመሽ ደሞ አለችኝ ሃሳብ የገባት ይመስላል።
እሺ እማ የትም አልሄድም ቻው ብያት ጋቢና ገባው እህቴ ዋናውን በር እየሮጠች ሄዳ ከፈተችልን ዛሬ የእህቴ ቅልጥፍና እያሳቀኝ ነው ዘበኛው እያለ ምን እሷ ያጣድፋታል እየወጣን እያለ ኪያርን ቻው አለችውና ስንሄድ ቆማ አየችን ገዞ ወደናዝሬት! መንገድ ላይ ሁላችንም እየተንጫጫን እየቀወጥነው እያወራን ሄድን ሲመሻሽ ናዝሬት ገባን ኪያር መኪናዋን ቀጥታ ወደ ግቢ ይዟት ገባ እነሱሙን ወደ ዶርማቸው አከባቢ አደረሳቸውሊጠይቁኝ ስለመጡ በጣም አመስግኛቸው መሰነባበት ጀመርን ሰሙ ኤቤጊያን ጠራልሃለው መልካም እድል ብላኝ ከራኬብ ጋር ቶሎ ሄደች የሆነ የደበራት ነገር እንዳለ ቀልቤ ይነግረኛል ሊዲያን ምን ሁና ነው አልኳት አይ መንገዱ ነው ትንሽ አሟት ነበር ቅድምም አለችኝና እኔና ኪያርን ቻው ብላን ሄደች።
ኪያር በቃ በርታ በል እኔ እዛ ጋር ሆኜ እጠብቅሃለው እንዳትፈራ ሴቶች እሚፈራ ወንድ አይመቻቸውም እሺ መልካም እድል ብሎኝ ፊትለፊት ጨለማ ውስጥ ጥንዶች የሚቀመጡበት ወንደር ላይ ሄዶ ተቀመጠ። የመጨረሻዋ ሰአት ደረሰች!! ኤቤጊያ ከደቂቃዎች በኃላ ትመጣለች ልቤ በፍጥነት መምታት ጀመረ ሰውነቴ ከበደኝ እንደምንም ራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩና ቀና ብዬ መኪናዋን ተደግፌ ቆምኩ ከትንሽ ቆይታ በኃላ አንዲት ሸንቀጥ ረዘም ያለች ውብ ከሴቶች ዶርም ወጥታ ስትመጣ አየው።
ይቀጥላል.....
#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot