#ቀን ሲጥል
ጓደኛዬ ኪያር ቅር ቢለውም በአባቴ ትእዛዝ መሰረት እንዳለ ጓዜን በሻንጣ ከግቢያችን ይዞት መጣ። ሻንጣውን ይዞት ላብ በላብ ሆኖ ሲገባ እህቴና ሰምሃል ተቀብለው አገዙት ከሰሙ ጋር ብዙም ሳንተዋወቅ ወደ አዲስ አበባ ልመለስ እንደሆነ ሳስብ ደበረኝ ሰሙም የደብራት ይመስለኛል ግን ምን ችግር አለው ቀጣይ አመት እመለሳለው ይሄ ሴሚስተር እንደሆነ ገና ሊጋመስ ነው::
ገና ወደቤት ሳልሄድ ይሄ አመት አልቆ ቀጣይ አመት መጥቶ የኤቤጊያን አይን ድጋሚ እስከማይ ድረስ ቸኮልኩ አረ... እኔማ የሷን አይን ሳላይ ለወራት መቆየት እምችል አይመስለኝም ብቻ ትንሽ ይሻለኝ እንጂ ተመልሼ መምጣቴ አይቀርም ናዝሬት እንደሆን የአንድ ሰአት መንገድ ናት አረ... እመጣለው ቀላል እመጣለው።
አባቴ በእኔ በጣም ተናዷል ዶክተሮቹ ሁሉንም ነገር ነግረውታል ሰክሬ ከሰው ጋር ተጣልቼ እንደሆነ አውቋል አሁን ስለታመምኩ ነው እንጂ ቢጮህብኝ ደስታው ነው ንዴቱ ከፊቱ ያስታውቃል አባቴ በጣም ሃይለኛ ሰው ነው እወደዋለው ግን እፈራዋለው ከልጅነቴ ጀምሮ ሳውቀው በትምህርት ቀልድ አያውቅም ለኔም ለእህቴም ከምንም ነገር በፊት ትምህርታችንን እንድናስቀድም ሁሌም ይመክረን ነበር። ኪያር ያመጣውን ጥቁር ተጎታች ሻንጣ አባቴ ከፈተው ልብሶቹ ከታጠቡ ዘመናት ስላለፋቸው እሚያስጠላ ሽታ አፈነው ወዲያው እየተገረመ አፍንጫውን ይዞ ዞር ብሎ አየኝና ተመልሶ ሻንጣውን መበርበር ጀመረ::
ድንገት የትምህርት ማስረጃዎቼን እማስቀምጥበት ሰማያዊ ባይንደር ከልብሶቹ መሃል ታየው በጣም ደነገጥኩ ያለፈውን ሴሚስተር ግሬድ ሪፖርት ፊት ለፊት እንዳስቀ መጥኩት በደምብ አስታውሳለው
ሰማያዊውን ባይንደር አነሳውና ቁጢጥ ብሎ ከተቀመጠበት ቀስ ብሎ ተነሳ የልብ ምቴ ሲፈጥን ይታወቀኛል።
ገልጦ ውስጡ ያሉትን ወረቀቶች ማየት ጀመረ ፊቱ ቀስ በቀስ ወደ ቀይነት ሲቀየር አይኖቹ ተጎልጉለው እስኪወጡ ድረስ ሲፈጡ አየኃቸው በጣም ተበሳጭቶ ባይንደሩን ከደነውና ሻንጣው ላይ እንደነገሩ ጣል አድርጎት ከክፍሉ በፍጥነት ወጣ ያለፈውን ሴሚስተር ምንም አልተማርኩም ፋይናል ፈተናም በአግባቡ አልተፈተንኩም ነበር የከዚቀደሙ ውጤቶቼ አሪፍ ቢሆኑም ያሁኑን ግን ከ2 ነጥብ በታች አምጥቼ በማስጠንቀቂያ ነበር ወደዚኛው ሴሚስተር ያለፍኩት አስተማሪዎቹም ቀድመው ስለሚያውቁኝ እንጂ ኤፍ እንደሚሰጡኝ እርግጠኛ ነበርኩ በብዛት ሲ እና ዲ አምጥቼ በማስጠንቀቂያ ነበር ያለፍኩት አባቴ ይህንን ሲያይ ነበር የተናደደው።
ውጪ ከእናቴ ጋር ሆነው ሲጨቃጨቁ ይሰማኛል። ታናሽ እህቴ ወደኔ ጠጋ ብላ አንተ ምን ሆነህ ነው ልብስህ እንዲ እስኪሆን ድረስ የማታጥበው በጣም ይሸታል ሌላው ቢያቅትህ እንኳን ላውንደሪ ቤት መስጠት ያቅትሃል ብር አልጎደለህ ለምን እንዲ ትዝረከረካለህ አለችኝ ለራሴ ወላጆቼን ይዛብኝ መጥታለች እዚው ራሴን አስታምሜ እነሱ ምንም ሳያውቁ እንድድን እንዳትነግራቸው ብላት ጭራሽ ይዛቸው መጣች ለምን ይዘሻቸው መጣሽ ብቻሽን ነይ አልነበር ያልኩሽ ብዬ ተቆጣኃት እንዴ እና ታዲያ እስክትሞት እንድጠብቅ ነው ምትፈልገው አለችኝ እሷም መልሳ እየተ ቆጣችኝ።
ሰምሃልና ኪያ ይህንን ሁሉ ድራማ ጥግ ላይ ካሉት ወንበሮች ላይ ተቀምጠው ከማየት ውጪ ምንም ቃል አይተነፍሱም እነሱም ለኔ ጨንቋቸዋል። ከታናሽ እህቴ ጋር እየተከራከርን እያለ አባቴ ከአንዲት ነርስ ጋር ወደውስጥ ገባ እና ወደኪያ እያየ እእእእ ኪያር እስኪ ሻንጣውን ወደመኪናው አስገባልኝ ብሎ አዘዘው ኪያር ምንም ሳያቅማማ ሻንጣውን ይዞት ወጣ አባቴ ብስጭቱ ጋብ ያለለት ይመስላል ነርሷ አጠገቤ መጥታ ጉሉካሱ የተሰካበትን ገመድ ከእጄ ላይ ነቅላ ማስተካከል ጀመረች እኔም ለመነሳት ስዘገጃጅ እህቴና ሰምሃል መጥተው አግዘውኝ ከአልጋዬ ተነስቼ መሬቱን ረገጥኩ።
አባቴ ከኃላ ሆኖ መድሃኒቶቹን በፊስታል ይዞ ተከተለን እናቴ ከጎን ሆና እንባ እንባ እያላት ከማየት ውጪ ምንም አትልም። እኛ በረንዳው ላይ ቀስ ብለን እየሄድን ኪያር ሻንጣውን የአባቴ መኪና ጌር አድርሶት እየሮጠ ሲመለስ ተገጣጠምን።
ይቀጥላል ....
ስለቆየሁባችሁ በጣም ይቅርታ ጠይቃለው ስላልተመቸኝ ነው 🙏
አሁንም አብሮነታችሁ አይለየን
#ከወደዱት
ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share
@QdistJoin and share👇👇
@qdist@qdist@qdistFor any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት
@e_t_l_bot