#FactCheck የትምህርት ሚኒስቴርን ስምና አርማ በመጠቀም ተዘጋጅቶ እየተጋራ የሚገኝ ይህ ደብዳቤ ትክክለኛ አይደለም
ይህ ምስሉ የሚታየው ደብዳቤ ከትምህርት ሚኒስቴር ለባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ እንደተፃፈ ተደርጎ በመዘጋጀት በማህበራዊ ትስስር ገፆች እየተጋራ አንደሚገኝ ተመልክተናል።
በምስሉ እንደሚታየው “ደብዳቤው” ሐምሌ 06፣ 2016 እንደተፃፈና ጉዳዩም የአንደኛ አመት ተማሪዎች የትምህርት መስክ (ዲፓርትመንት) ምደባን እንደሚመለከት ተጠቅሷል።
በዚሁ መሰረት አዲስ ገቢ ተማሪዎች ውጤት አያያዝ እንዴት መሆን እንዳለበት “በደብዳቤው” ተዘርዝሯል።
የዚህን ደብዳቤ ትክክለኛነት እንድናጣራ የኢትዮጵያ ቼክ ተከታዮችም ጥቆማ የሰጡን ሲሆን እኛም የትምህርት ሚንሰትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን መረጃ ጠይቀናል።
እርሳቸውም ይህ በማህበራዊ ትስስር ገፆች እየተጋራ የሚገኝ ደብዳቤ ሀሰተኛ መሆኑን ነግረውናል።
በተጨማሪም የደብዳቤው ይዘት ላይ ባደረግነው የፎቶፎረንሲከስ ምልከታ በርካታ አጠራጣሪና የተነካኩ ይዘቶች መኖራቸውን ተመልክተናል።
[ይህን መረጃ አጣርቶ ትክክለኛ አለመሆኑን ያረጋገጠው ኢትዮጵያ ቼክ ነው]
@Remedial_Hub