ትዳርን ፈልጋ የራቀባት እንስት
#ክፍል አንድ {1}
እንደማንኛውም ሰው ጥሩ ትዳር ለመመሰረት ፅኑ ጉጉት ስለነበራት እህታችን ላወጋችሁ ነው።
“ በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ (CAIRO) ከሚገኝ አንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በከፍተኛ ማዕረግ ከተመረቁ ተማሪዎች መካከል አንዷ ነበርኩ ። ወደ ስራው ዓለም ከመቀላቀሌ በፊት ከተለያዩ አካባቢዎች የትዳር ጥያቄዎች ይጎርፉልኝ ጀመር ። ነገር ግን የእያንዳንዱን ጥያቄ በሰከነ መንፈስ ሳጤነው ለእኔ የሚበጀኝ ሆኖ አላገኘውም ። በዚህ መሃል ሳለሁ ወደ ስራው ዓለም ገባሁ ። ስራየ ውጥረት የበዛበት ነው ። ለእኔ ዕረፍት ማለት ብርቅ የሆነ ነገር ነበር ። ስጋዊም ሆነ መንፈሳዊ ፍላጎቴን በወጉ ማጣጣም የምችልበትን እድል የማይፈጥር ስራ ። ጊዜው ነጎደ ፤ እድሜየም ጨመረ ። የትዳር ጥያቄዎቹም እንደወትሮው አልሆኑም ። ቀዘቀዙ ። ከዩኒቨርሲቲ ስመረቅ እድሜየ በሃያዎቹ መጀመሪያ የነበርኩት ልጅ ዛሬ ሰላሳ አራት ዓመት ሆኖኛል ። በዚህ የእድሜ እርከን ውስጥ መግባቴን እና ትዳር አለመያዜን ስረዳ ያኔ ይቀርቡልኝ ከነበሩት የትዳር ጥያቄዎች መካከል የትኛው ይሻል ነበር እያልኩ በሃሳብ ስሌት ውስጥ እሰጥማሁ ። አሁን ላይ ሆኖ መምረጡ ግን ትርጉም የሌለው ምርጫ ሆነብኝ ። የብቸኝነት ስሜት ይሰማኝ ገባ ። ስለመጪው በማሰብ አሁን ላይ እረበሻለሁ ። ውስጤ ይቆስላል ።
የተስፋ ጭላንጭል የምመለከትበት ቀዳዳ ያጣሁ እየመሰለኝ እጠበባለሁ ። ጨቅላ ህፃናቶችን ስመለከት < የኔ በሆኑ > በሚያሰኝ ምኞት እራሴን ሩቅ ተሻግሬ አገኜዋለሁ ። ጥንዶች በየጎዳናው ሲጓዙ ስመለከት የእኔ ጉዞ መቼ ይሆን እያልኩ ጥያቄውን እራሴ ለራሴ አቀርበዋለሁ - < አንድ ቀን ! > በሚል የውስጤ ስሜት መልስ ይሰጣል ። ይህን የብቸኝነት ድባብ ሊያወድም ያለ አንድ ወጣት ግን እያደነኝ መሆኑን በውል አልተገነዘብኩም ነበር ። ዕድሜው ከእኔ በሁለት ዓመት ይበልጣል ። ሰላሳ ስድስት ዓመት መሆኑ ነው ። የእርሱም የስራ ሁኔታ እጅግ አስቸጋሪ ነበር - ፋታ የማይሰጥ አይነት ስራ ነው ። ነገር ግን በዚህ ሰዓት ይህን እድል ማምከን ማለት በቀጣይ የትካዜ ቀንበር ተሸክሜ የምኖርበትን ዓለም እንደማመቻቸት ቆጠርኩት ። የልጁን ጥያቄ በክብር ተቀበልኩ ። ኢስላማዊውን ሸሪዓ በማይፃረር ሁኔታ የሁለታችንም ወገኖች በአካል ባሉበት ቃልኪዳን እንዲፈፀም ወሰን ። ጮኛየ ሊሆን ያሰበው ወጣት ቃል ኪዳኑ እንዲፈፀም የሚያስችል ሁለት ጉርድ ፎቶግራፎችን እንዳመጣ መልዕክት ላከብኝ ። ፎቶግራፎቹን ላኩለት ። ይህን ካደረኩ ከሁለት ቀናት በኋላ የልጁ እናት በአስቸኳይ እንደሚፈልጉኝ ስልክ ደውለው ነገሩኝ ። ተገናኘን ። በእጃቸው ከያዙት ጥቁር ቦርሳ ውስጥ የእኔ ፎቶ ግራፍ ያለበትን መታወቂያ አውጥተው አሳዩኝ ።
“ ለመሆኑ መታወቂያሽ ላይ የሰፈረው እድሜ በስህተት ነው ወይስ ምንድን ነው ?! ” ብለው ጠየቁኝ ። “ አይ ! ትክክለኛ ነው ፤ እድሜየ ነው ” አልኳቸው ።
“ ታዲያ አንቺ አርባ ዓመት ሆኖሻል አይደል እንዴ ? ” ብለው ቅስምን የሚሰብር ጥያቄ ጠየቁኝ ። “ ኧረ እማማ ገና ሰላሳ አራት አመቴ ነው ” አልኳቸው ። “ ኧረ እባክሽ ያው ነው ! ሰላሳ አራት እና አርባ ዓመት ምን ልዩነት አላቸው ብለሽ ነው ። አንቺ ከሰላሳ አራት ዓመት በላይ ተሻግረሻል ። ዘርሽን የመተካት እድልሽ ሲበዛ መንምኗል ። እኔ ደግሞ የልጅ ልጄን ተመልክቼ መሳም እሻለሁ ” አሉኝ ።
ክፍል ሁለት ይቀጥላል……………