🌸የዕውቀት መዓድ💎


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


✍ﻭَﻗُﻞ ﺭَّﺏِّ ﺯِﺩْﻧِﻲ ﻋِﻠْﻤًﺎ
«ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትንም ጨምርልኝ በል!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


Qualitymovbot dan repost
ቤተሰብ ዛሬ አንድ Channel ይዤላችሁ ቀርቤያለው ስሙም " samir-post 🩶" ይሰኛል እዚህ ምታገኙት👇

#°Quranic 🎧
#°ωαℓℓραρєя'ѕ🌒
#°ǫυσтєѕ✍️
#°ғᴜɴɴʏ ᴍᴇᴍᴇs😂
#°የፍቅር ልቦለዶች 💔

#እናም_ብዙ_ብዙ_ምትዝናኑበት_ነገሮች 😉

         𝑃𝑙𝑒𝑎𝑠𝑒 𝑑𝑜𝑛'𝑡 𝑗𝑜𝑖𝑛 𝑡𝑜 𝑙𝑒𝑎𝑣𝑒🙏
     እኛ እያለን No ድብርት😄

#Request በመላክ ይቀላቀሉን🫧 እናመሰግናለን🫶🏼


በጥቅም ላይ የተመሰረተ ወዳጅነትና ዝምድና ጥቅሙ ሲቀር ይረሳል ወይም ጥላትነትን ያተርፋል።በዙሪያችን ለጥቅም ብለው የቀረቡን ሰዎች ካሉ በጊዜ መፍትሔ እናብጅለት። ትናንት በጥቅም ሲወዷቸው የነበሩ ወዳጆች ዛሬ ላይ ጥቅሙ ሲቀር ዓይንህን ላፈር የተባባሉ ሰዎች ብዙ ናቸው። እነዚህ ዓይነት ሰዎች Materialist ናቸው። በቃ ሁሌ ጥቅም ብቻ !

ሰው ማለት ሰው መሆን የሚችል ነው ሰው በጠፋ ዕለት ።በችግር በመከራ በሐዘን በስቃይ ከጎን መሆን የሚችል!!


የመሬት መንቀጥቀጥ መብዛቱ…

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لا تَقُومُ السّاعَةُ حتّى يُقْبَضَ العِلْمُ، وتَكْثُرَ الزَّلازِلُ﴾

“ሰዓቲቱ ‘ትንሳዔ’ አትቆምም እውቀት እስከሚነሳና የመሬት መንቀጥቀጥ እስከሚበዛ ድረስ።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል (1036 )


🇸🇦يونس ابن حسن🇸🇦 dan repost
✅የወንጀሎች ተፅዕኖ በልቦች ላይ፡ ልክ በሽታዎች በሰውነት ላይ ተፅዕኖ እንደሚፈጥሩት ነው✅

" تأثير الذنوب على القلوب مثل تأثير الأمراض على الأبدان "

አሏህ ልባችንን እንዲያፀዳልን እንለምነዋለን።

ጁሙዓ ነው፡
💜ገላችን እንታጠብ
💜ካለን ልብስ የተሻለውን እንልበስ [ነጭ ቢሆን ይመረጣል]
💜ወንዶች ካገኘን አሪፍ ሽቶ እንቀባ
💜በጊዜ ወደ መስጂድ እንሂድ
ሱረቱል ከህፍ እንቅራ
💜መስጂድ ስንገባ በሰዎች ትከሻ አንረማመድ፡ ሰዎችን ለይተን አንቀመጥ፡
💜ሶለዋትና ዱዓ እናብዛ

🔈አደራችሁ!
አስታዋሽ ብቻ አንሁን፡ ይልቁንስ መጀመሪያ እራሳችን እንተግብር።


✅صلوات ربي وسلامه عليه✅

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat


♻️የጁሙኣ ኹጥባ

"የመጨረሻው ዘመን ፈተናዎች"


🎙በኡስታዝ ኢብራሒም ኸይረዲን

29/04/1446ዓ/ሂ

https://t.me/ibrahim_furii


"አሏህ ሱበሀነሁ ወታዓላ በቃሉ ምን ይላል:-

( لاتخافيِ ولا تحزنيِ)

-لا تحزنيِስላለፈው ነገር አትዘኝ


- ولاتخافيِ ወደፊት ስለሚመጣው ነገር አትፍሪ


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
🌺 የጁምአ ስጦታዬ  ነው ሱረቱል ካፍ ተጋበዙልኝ

🌺🎧ካህፍ የቻለ ይቅራ📖 ያልቻለ ያዳምጥ
በአላህ መልዕክተኛ(ሰዐወ) ላይ ሰለዋት ማውረድ እናብዛ

🌺﴿إِنَّ ٱللَّهَ وَمَلَٰٓئِكَتَهُۥ يُصَلُّونَ عَلَى ٱلنَّبِىِّ ۚ يَٰٓأَيُّهَا 🌺ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ صَلُّواْ عَلَيْهِ وَسَلِّمُواْ تَسْلِيمًا ۝﴾

🌺قَالَ ﷺ: «مَنْ صَلَّ عَلَيَّ صَلاةً صَلَّ اللهُ عَلَيْهِ بِهَا عَشَراً»
🌺በኔ ላይ አንድ ጊዜ ሶላዋት ያወረደ አላህ በርሱ ላይ አስር ጊዜ ሶለዋት ያወርድለታል🍂

🌺اللهم صل وسلم وبارك على نبينا محمدﷺ🍃
🌺اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
🌺اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ


ረሱል ﷺ ቀብር ሲዘይሩ ፋቲሃ ይቀሩ ነበር የሚል ምንም ማስረጃ ከሳቸው ﷺ አልተገኘም።

ሸይኽ ሷሊህ ኢብኑ ዑሰይሚን አሏህ ይዘንላቸውና።

قال العلامة العثيمين رحمه الله :

ولم يرد عن النبي صلى الله عليه وآله وسلّم أنه كان يقرأ الفاتحة عند زيارة القبور .

[مجموع الفتاوى ٢٤٥]


አላህም በጠባቂነት (ከሁሉ) የበለጠ ነው፡፡ እርሱም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነው፤» አላቸው፡፡..

surah yusuf #64


ታውቃላቹሀ .... አይነ ስውር ሰው እድል ተሰጥቶት አይኑ
ቢበራለት መጀመሪያ የሚጥለው ነገር እድሜውን በሙሉ
አብሮት የቆየውን ምርኩዙን መሆኑን።

አብዘሀኛው ሰው ........
ምንም ያክል ብትደክምለት ፣ ብትለፋለትም
አንድ ቀን ሲያልፍለት ትቶህ መሔዱ አይቀርምና

«ለራስህ መኖርን ልመድ ወዳጄ!!»


አስበኸዋል!
ልክ እንደወደድከው
አንተም ስትወደድ!!


ለምንድን ነው የኢሳን (አለይሂ ሰላም)፣ የአቡበክር፣ የኡመርን፣ የኡስማንን፣ የአልይን ልደት የማናከብረው?

እነሱ ስሜታቸውን ተከትለው
‹‹የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ልደት የምናከብረው ለሳቸው ያለንን ውዴታ ለመግለፅ ነው፡፡›› ይላሉ
ጥያቄው

ሙስሊም የሆነ ሰው ነብያትን፣ ሰሃባዎችን መውደድ፣ እናት አባቱን መውደድ፣ ኡለማዎችን መውደድ ግዴታው ነው፡፡ ታድያ ከነብያት ውስጥ ለምሳሌ ከ5ቱ የቁርጠኝነት ባለቤት ከሚባሉት ውስጥ የሆነውን ታላቁን ነብይ ኢሳ (አለይሂ ሰላም) ለሱ ያለንን ውዴታ የምንገልፀው የልደት ቀኑን በማክበር ነውን?
በፍፁም
ሰሃባዎችን እንድንወድ ታዘናል፡፡ ታድያ ለምን የአቡበክር ሲዲቅን፣ የኡመርን፣ የኡስማንን፣ የአልይን ልደት አናከብርም?
መልሱም
ስላልታዘዘ እና በዚህ መንገድ ስላልሆነ ለነሱ ያለንን ውዴታ የምንገልፀው፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ከአላህ ቀጥሎ ከነፍሳችን፣ ከልጆቻችንና፣ ከማንም በላይ አስበልጠን መውደድ አለብን፡፡ ለሳቸው ያለንን ውዴታ የምንገልፀው
1) ያዘዙትን ሁሉ አቅም በቻለው መልኩ በመታዘዝ፣
2) የከለከሉትን ሁሉ በመከልከል፣
3) የተናገሩትን ሁሉ እውነት ነው በማለት፣
4) የተዉትን፣ ያላሳዩንን እኛም በመተው፡፡ ምክንያቱም መልካም ሆኖ ያላሳዩን ነገር የለምና፡፡
5) ሰለዋት በማውረድ እና የመሳሰሉትን

እሳቸው በህይወት በነበሩ ግዜ አላህ ዘንድ የተከበረ፣ የተወደደ፣ ቅርብ የተባለው ወንድማቸውን ኢሳን (አለይሂ ሰላም) ልደት ነሷራዎች ቢያከብሩትም እሳቸው ግን አላከበሩትም፡፡ በጣም የሚወዷት ልጃቸው ፋጢማ (ረድየላሁ አንሃ) ልደቷን አክብረውላት አያውቁም፡፡ ምክንያቱም አላህ እንዳላቸው ‹‹ወዳንተ የተወረደልህን ተከተል›› እሳቸው ከአላህ የታዘዙትን ብቻ ነው የሚከተሉት፡፡

በሸሪዐችን አቂቃ የተባለ አንድ ሰው ሲወለድ ደስታችንን በግለጫ፣ ጌታችንን ማመስገኛ ወንድ ልጅ ከተወለደ 2 በግ፣ ሴት ልጅ ከተወለደች 1 በግ ይታረዳል፡፡ አበቃ፡፡
ታድያ ለነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምና) ለነዛ ውድ ሰሃባዎች የበቃቸው ዲን ለእኛ አይበቃንምን?
ሱና ላይ እንቁም ከሃቅ በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ የለም፡፡ ከሱና በኋላ ቢድዐ እንጂ ሌላ የለም፡፡

‹‹እኛ መውሊድን የምናከብረው ለነብዩ ያለንን ውዴታ ለመግለፅ ነው፡፡›› የሚሉ ሰዎች የሚከተሉት ምርጦች
-) ሙሃጂሮች፣ አንሷሮች፣ 10ሩ የጀነት ሙሽሮች፣
-) ታቢኢኖች፣ አትባኡ ታቢኢን፣
-) ኢማም አቡ ሃኒፋ፣ ኢማሙ ማሊክ፣ ኢማሙ ሻፊኢ፣ ኢማሙ አሕመድ፣
-) ኢማሙል ቡኻሪ፣ ኢማሙ ሙስሊም፣ ነሳኢ፣ አቡ ዳውድ፣ ትርሚዚ፣ ኢብን ማጃ፣ እነ ሱፍያን አሰውሪ፣ እነ አብደላህ ኢብን ሙባረክ፣ እና ሌሎችም ፈርጦች አይወዷቸውም ነበርን ልትሉን ነው?

ወይንም እንዴት ውዴታቸውን መግለፅ እንደነበረባቸው አልገባቸውም ወይንም አያውቁም ልትሉን ነው?
ይልቁንስ መውሊድን የጀመሩት የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፣ የሰሃባዎችና፣ የአማኞች ጠላቶች የሆኑት ሺዐዎች ናቸው፡፡ ይህ ብቻ ይበቃናል ሸር ለመሆኑ፡፡
አላህ ሃቁን ይምራን፣ በሃቅም ላይ ያፅናን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts


~ለራሷ ዱዓ ማድረግ አስታውሳ አታውቅም። ለልጆቿ እንጂ።ትንሽ ሆነው ሳለና
ትልቅ ሆነዉም ለልጆቿ ብላ ራሷን የረሳች
ከእናት ዉጪ ማን አለች።


ትዳርን ፈልጋ የራቀባት እንስት

#ክፍል አንድ {1}

እንደማንኛውም ሰው ጥሩ ትዳር ለመመሰረት ፅኑ ጉጉት ስለነበራት እህታችን ላወጋችሁ ነው።
‌‌
“ በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ (CAIRO) ከሚገኝ አንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በከፍተኛ ማዕረግ ከተመረቁ ተማሪዎች መካከል አንዷ ነበርኩ ። ወደ ስራው ዓለም ከመቀላቀሌ በፊት ከተለያዩ አካባቢዎች የትዳር ጥያቄዎች ይጎርፉልኝ ጀመር ። ነገር ግን የእያንዳንዱን ጥያቄ በሰከነ መንፈስ ሳጤነው ለእኔ የሚበጀኝ ሆኖ አላገኘውም ። በዚህ መሃል ሳለሁ ወደ ስራው ዓለም ገባሁ ። ስራየ ውጥረት የበዛበት ነው ። ለእኔ ዕረፍት ማለት ብርቅ የሆነ ነገር ነበር ። ስጋዊም ሆነ መንፈሳዊ ፍላጎቴን በወጉ ማጣጣም የምችልበትን እድል የማይፈጥር ስራ ። ጊዜው ነጎደ ፤ እድሜየም ጨመረ ። የትዳር ጥያቄዎቹም እንደወትሮው አልሆኑም ። ቀዘቀዙ ። ከዩኒቨርሲቲ ስመረቅ እድሜየ በሃያዎቹ መጀመሪያ የነበርኩት ልጅ ዛሬ ሰላሳ አራት ዓመት ሆኖኛል ። በዚህ የእድሜ እርከን ውስጥ መግባቴን እና ትዳር አለመያዜን ስረዳ ያኔ ይቀርቡልኝ ከነበሩት የትዳር ጥያቄዎች መካከል የትኛው ይሻል ነበር እያልኩ በሃሳብ ስሌት ውስጥ እሰጥማሁ ። አሁን ላይ ሆኖ መምረጡ ግን ትርጉም የሌለው ምርጫ ሆነብኝ ። የብቸኝነት ስሜት ይሰማኝ ገባ ። ስለመጪው በማሰብ አሁን ላይ እረበሻለሁ ። ውስጤ ይቆስላል ።

የተስፋ ጭላንጭል የምመለከትበት ቀዳዳ ያጣሁ እየመሰለኝ እጠበባለሁ ። ጨቅላ ህፃናቶችን ስመለከት < የኔ በሆኑ > በሚያሰኝ ምኞት እራሴን ሩቅ ተሻግሬ አገኜዋለሁ ። ጥንዶች በየጎዳናው ሲጓዙ ስመለከት የእኔ ጉዞ መቼ ይሆን እያልኩ ጥያቄውን እራሴ ለራሴ አቀርበዋለሁ - < አንድ ቀን ! > በሚል የውስጤ ስሜት መልስ ይሰጣል ። ይህን የብቸኝነት ድባብ ሊያወድም ያለ አንድ ወጣት ግን እያደነኝ መሆኑን በውል አልተገነዘብኩም ነበር ። ዕድሜው ከእኔ በሁለት ዓመት ይበልጣል ። ሰላሳ ስድስት ዓመት መሆኑ ነው ። የእርሱም የስራ ሁኔታ እጅግ አስቸጋሪ ነበር - ፋታ የማይሰጥ አይነት ስራ ነው ። ነገር ግን በዚህ ሰዓት ይህን እድል ማምከን ማለት በቀጣይ የትካዜ ቀንበር ተሸክሜ የምኖርበትን ዓለም እንደማመቻቸት ቆጠርኩት ። የልጁን ጥያቄ በክብር ተቀበልኩ ። ኢስላማዊውን ሸሪዓ በማይፃረር ሁኔታ የሁለታችንም ወገኖች በአካል ባሉበት ቃልኪዳን እንዲፈፀም ወሰን ። ጮኛየ ሊሆን ያሰበው ወጣት ቃል ኪዳኑ እንዲፈፀም የሚያስችል ሁለት ጉርድ ፎቶግራፎችን እንዳመጣ መልዕክት ላከብኝ ። ፎቶግራፎቹን ላኩለት ። ይህን ካደረኩ ከሁለት ቀናት በኋላ የልጁ እናት በአስቸኳይ እንደሚፈልጉኝ ስልክ ደውለው ነገሩኝ ። ተገናኘን ። በእጃቸው ከያዙት ጥቁር ቦርሳ ውስጥ የእኔ ፎቶ ግራፍ ያለበትን መታወቂያ አውጥተው አሳዩኝ ።

“ ለመሆኑ መታወቂያሽ ላይ የሰፈረው እድሜ በስህተት ነው ወይስ ምንድን ነው ?! ” ብለው ጠየቁኝ ። “ አይ ! ትክክለኛ ነው ፤ እድሜየ ነው ” አልኳቸው ።

“ ታዲያ አንቺ አርባ ዓመት ሆኖሻል አይደል እንዴ ? ” ብለው ቅስምን የሚሰብር ጥያቄ ጠየቁኝ ። “ ኧረ እማማ ገና ሰላሳ አራት አመቴ ነው ” አልኳቸው ። “ ኧረ እባክሽ ያው ነው ! ሰላሳ አራት እና አርባ ዓመት ምን ልዩነት አላቸው ብለሽ ነው ። አንቺ ከሰላሳ አራት ዓመት በላይ ተሻግረሻል ። ዘርሽን የመተካት እድልሽ ሲበዛ መንምኗል ። እኔ ደግሞ የልጅ ልጄን ተመልክቼ መሳም እሻለሁ ” አሉኝ ።

ክፍል ሁለት ይቀጥላል……………


ወደ አላህ ሽሹ ።


🇵🇸 አግራሞቴን በብዕር

▮ ጠንካራ ሰው ማለት:-

በአጠገቡ ያሉ ሰዎችን የሚያስደስት
በህይወቱ ሁልጊዜ ስህተት ማይሰራ፤ አንዳንዴም ስህተት ሲፈፅም ስህተቱን አምኖ ተቀብሎ ይቅርታ የሚጠይቅ።
ምላሽ ሳይጠብቅ ሰዎችን የሚረዳ፣ ፍትሃዊና እውነተኛ የሆነ ሰው ነው። በእርግጥም ይህ ሰው ምንኛ ታደለ!!

አንተ በቻልከው መጠን የሰው ልጆችን እርዳ! አንተን ፈጣሪ ይረዳሃል።

መልካም ሁን ለመልካምነትህ ግን ምላሽ አትጠብቅ። ለመልካምነትህም ዋጋ (ተመን) አታውጣለት፤ መልካምነትህን የሚለካው ለሰው ልጆች ያለህ እውነተኛ ፍቅርና አክብሮት ብቻ ነው።


ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"من غشنا فليس منا"
"ያታለለን ከኛ አይደለም።" ሙስሊም፡ 146




يارب عوَّضني عن تعبي ، وجازيني علىٰ صبري ، وارضيني بنصيبي ، اضعاف ما تحمِّلت .
ጌታ ሆይ ድካሜን ክፈልልኝ መታገሴንም መልሰኝ የታገስኩትንም እጥፍ አርካኝ


💥ትዕግስት የሌላት ሴት ብዙ ነገር ከምታስተካክለው ይልቅ የምታበላሸው ነገር ይበልጣል .... እናማ ሶbር ይኑረን!

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.