አስደማሚ ታሪክ
~~~~~~~~~~
ኢስሓቅ ኢብኑ ዐባድ አልበስሪ ይባላሉ። በአንድ ወቅት ተኝተው ሳለ በህልማቸው የሆነ አካል መጥቶ "ችግረኛውን እርዳ!" አላቸው።
ከእንቅልፋቸው ተነስተው በጎረቤት የተቸገረ ካለ ቢጠይቁ "አናውቅም" የሚል ምላሽ አገኙ።
ተመልሰው ተኙ። አሁንም ለሁለተኛ፣ ከዚያም ለሶስተኛ ጊዜ መጥቶ "ችግረኛውን ሳትረዳ ትተኛለህ?" አላቸው።
ተነሱ። 300 ዲርሃም ያዙ። በቅሏቸው ላይ ሆነው ወደ መስጂድ ወጡ። ሲደርሱ ሶላት የሚሰግድ ሰው አለ። ማጠናቀቁን ሲገምቱ ተጠጉና
"አንተ የአላህ ባሪያ! ምነው በዚህ ሰዓት? በዚህ ቦታ? ምን አወጣህ?!" አሉት።
ሰውየው:– "እኔ ወረቴ መቶ ዲርሃም የሆንኩ ሰው ነበርኩ። ግን ጠፋብኝ። ከዚያም የ200 ዲርሃም እዳ ተጫነኝ" አለ።
ዲርሃሞቹን አውጥቶ "ይሄው እነዚህ 300 ዲርሃሞች ናቸው። ውሰድ" አሉት። ወሰደ።
ከዚያም "ታውቀኛለህ?" አሉት።
"አላውቅህም" አለ።
"እኔ ኢስሓቅ ኢብኑ ዐባድ ነኝ። ችግር ከገጠመህ ከኔ ዘንድ ና" ብለው ቤቱ የሚገኝበትን አካባቢ ነገሩት።
•
ሰውየው በዚህም ጊዜ እንዲህ አለ:–
"አላህ ይዘንልህ። ችግር ከገጠመን አንተን ከቤትህ አውጥቶ እኔ ዘንድ ወዳመጣህ ጌታ ነው የምሸሸው።"
📚 [ረሳኢሉ ኢብኒ ረጀብ: 3/128]
ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር (حفظه الله)
https://t.me/Setoch_Be_Islam