TIMRAN (ትምራን)


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Inglizcha


Website: timran.et
FB: facebook.com/timranethiopia
Twitter: https://x.com/timranethiopa
Timran is dedicated to advancing women’s participation in politics and public decision-making in Ethiopia regardless of their political opinion or party affiliation.

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Inglizcha
Statistika
Postlar filtri


ለምርጫ ቦርድ አመራር ቦርድ እጩዎችን የማቅረብ ቀነ-ገደብ በፍጥነት እየቀረበ ሦስት ቀናት ብቻ ቀርተውታል!
ቀጣዩ ቦርድ ለሴቶች መብት እና ተሳትፎ ቅድሚያ እንዲሰጥ ድምፅ በመስጠት እናረጋገጥ! ድምፅዎት ልዩነት ይፈጥራል!
#ሴቶችን ማብቃት #ሴቶችበአመራርነት #የእጩነትጥሪ #ትምራን@5

The deadline for nominating candidates to the NEBE Management Board is fast approaching and left three days only!
Let’s ensure the next board prioritizes women’s rights and participation. Your voice matters!
#NominateNow #WomenInLeadership #NominationCall #TIMRAN@5




አራት ቀናት ቀረው
ለምርጫ ቦርድ አመራር እጩዎችን ለመጠቆም አራት ቀናት ብቻ ቀርተዋል።
ሴቶች ግንባር ቀደም መሆናቸውን እናረጋግጥ።
እጩዎችን በማቅረብ እንዲሁም የእጩዎችን ዝርዝር መረጃ በመስጠት ሴቶች የሚመሩበትን እድል ለመፍጠር ያግዙን!
#ሴቶችንእንምረጥ #ሴቶችበአመራርነት #የእጩነትጥሪ #ትምራን@5

Only four days left to nominate candidates for the NEBE Management Board.
Let’s make sure women are at the forefront. Share your nominees list and help us advocate for a future where women lead!
#VoteforWomen #WomenInLeadership #NominationCall #TIMRAN@5




አምስት ቀናት ብቻ ቀረው
ለምርጫ ቦርድ አመራር ቦርድ እጩዎችን ለመጠቆም 5 ቀናት ብቻ ቀረው!
በቅንነት መምራት የሚችሉ እና የሴቶችን በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ ቁርጠኝነት ያላቸውን ብቁ ሴት እጩዎችን እናቅርብ።
#ሴቶችንእንምረጥ #ሴቶችበአመራርነት #የእጩነትጥሪ #ትምራን@5
Only 5 days left
Only 5 days left to nominate candidates for the NEBE Management Board! Let’s uplift and support qualified women candidates who can lead with integrity and commitment for women’s participation in decision making process.
#EmpowerWomen #WomenInLeadership #NominationCall #TIMRAN@5


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
“VAWiE is a red flag that all of us need to be alert of. We have to work collectively both as a group and as institution.” #TIMRAN@5


ትምራን የሴቶችን ድምፅ በጥምረቱ በኩል ለማሰማት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር ተፈራረመች

የጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር መድረክ ጽ/ቤት የሆነችው ትምራን ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በጋራ ጉዳይ ላይ በትብብር ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሚያዚያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በጉባኤው ጽ/ቤት ተፈራረመች።

በመግባቢያ ስምምነት መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ ትምራን ከጉባኤው ጋር በመቀናጀት በጋራ ጉዳይ ላይ ለመሥራት በመምጣቷ ለአመራሮቿ ምስጋና አቅርበው ያለንን የተቋማት ሀብት በማቀናጀት ውጤታማ ሥራ ለመሥራት አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ ይገባናል ብለዋል።

አክለውም ትምራን የሴቶችን ድምፅ በጥምረቱ በኩል በማቀናጀት የሴቶችን የመምራት አቅም ለማሳደግ እና ሴቶች ተገቢውን የሓላፊነት እና የሥራ ደረጃ እንዲያገኙ የምትሠራ ድርጅት በመሆኗ፣ በጉባኤው በኩል አስፈላጊው ትብብር እንደሚደረግላት ተናግረዋል።

አያይዘውም ሴት እናት፣ ሚስት፣ እኅት እና ልጅ ነች የሚለው አባባል ትልቅ ትርጉም ያለው በመሆኑ፣ ሴቶችን መደገፍ እና ማብቃት የራስን አካል መደገፍ እና ማብቃት ነው፤ ሴቶች በሁሉም መስክ ትርጉም ያለው ውክልና እና ሓላፊነት ያገኙ ዘንድ በጥምረቱ በኩል የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ውጤታማ ሥራ ለመሥራት ሁሉን አቀፍ ጥረት እንደሚደረግ ገልጸዋል።

የትምራን ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ኢየሩሳሌም ሶሎሞን በበኩላቸው፣ ትምራን የሴቶችን የአመራር ተሳትፎ ትርጉም ባለው ደረጃ ማረጋገጥ ይቻል ዘንድ ሁሉንም የጥምረቱን አባላት በማሳተፍ፣ የሴቶችን አቅም በማጎልበት እና ድምፃቸው ከፍ ብሎ እንዲሰማ የምትሠራ ሀገር በቀል ድርጅት መሆኗን ገልጸው፣ የሴቶች ተሳትፎ በሀገራዊ ምክክር ሂደት እና ውጤት፣ በሀገር ልማት እና እድገት፣ በኢኮኖሚው ዘርፍ፣ ወዘተ ሁሉ በተገቢው ሁኔታ ይታይ ዘንድ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የምትሠራ ድርጅት እንደሆነች አብራርተዋል።

በተጨማሪም የሴቷ አጀንዳ ማለት የባለቤቷ፣ የአባቷ፣ የልጇ፣ የወንድሟ አጀንዳ በመሆኑ፣ የሴቶችን አጀንዳ መደገፍ የሁሉንም ማኅበረሰብ አጀንዳ እንደ መደገፍ የሚቆጠር ነው። በዛሬው ዕለት በተፈራረምነው የመግባቢያ ስምምነት መሠረት ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር ሴቶች በመሪነት፣ በሰላም ግንባታ፣ በሥራ፣ በትምህርት፣ ወዘተ መስኮች ያላቸው ተሳትፎ ትርጉም ያለው ይሆን ዘንድ አቅም የፈቀደውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነን ብለዋል።

#TIMRAN@5




"Enhancing the electoral participation of women can’t be achieved with the only efforts of women; it needs the contribution of all actors." #TIMRAN@5


Call for Nomination for the Management Board of NEBE

The committee established by the FDRE Prime Minister is calling the public, political organizations, and civil society groups to submit one Deputy Chairperson and two Board Members nominees for the Management Board of the National Election Board of Ethiopia (NEBE).
This call for nominations comes as the current board of Managements completes their six-year term. Therefore, this call for nominations is crucial to advancing women's rights and increasing women's participation in decision-making.
We particularly encourage the nomination and support of qualified women candidates who are committed to women’s rights and actively promote the participation of women in decision-making processes.

⏳ Deadline: April 29, 2025
Given the short time remaining, we kindly request that coalitions and civil society organizations use your networking platforms to nominate candidates and actively campaign.

📝 How to nominate
Please find the nomination form linked below.
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdIkWE0eJ1mnywpuWZRYTqjfYQrJpEuhsQfKnhmeE93eQ6CPA/viewform


የምርጫ ቦርድ አመራር እጩነት ጥሪ

በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር የተቋቋመው ኮሚቴ ኅብረተሰቡን፣ የፖለቲካ ድርጅቶችንና የሲቪል ማኅበራትን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አመራር ቦርድ ብቁ የሆኑ አንድ ምክትል ሰብሳቢ እና ሁለት የቦርድ አባላት የሚሆኑ እጩዎች እንዲያቀርብ ጥሪ አድርጓል።

ይህ ጥሪ የተደረገው የአሁኑ የሥራ አመራር ቦርድ የስድስት ዓመት የሥራ ዘመን በመጠናቀቁ ነው፡፡ በመሆኑም ይህ የእጩነት ጥሪ የሴቶችን መብት ለማስከበር እና የሴቶችን የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ለማሳደግ ወሳኝ ነው፡፡ ስለዚህም ለሴቶች መብት የሚተጉ እና የሴቶችን በውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ውስጥ ተሳትፎን በንቃት የሚያበረታቱ ብቁ የሆኑ ሴት እጩዎችን ጥቆማ እና ድጋፍ እናበረታታ።

 ቀነ ገደብ፡- ሚያዚያ 21 ቀን 2017 ዓ.ም

የቀረውን አጭር ጊዜ በመመልከት ጥምረቶች እንዲሁም የሲቪል ማኅበር ተቋማት የኔትወርክ መድረኮቻችሁን ተጠቅማችሁ እጩ እንድታቀርቡ እና በንቃት እንድትሟገቱ በትኅትና እንጠይቃለን።

በምርጫ ሥርዓታችን ውስጥ ሴቶችን በውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ውስጥ የሚያሳትፍ እና ውጤታማ አመራርን ለማረጋገጥ በጋራ እንሥራ።

📝 የእጩነት ጥቆማ ሂደት https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdIkWE0eJ1mnywpuWZRYTqjfYQrJpEuhsQfKnhmeE93eQ6CPA/viewform




Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
እንኳን ለ2017 ዓ.ም ብርሃነ ትንሣኤ አደረሳችሁ!

TIMRAN wishes a Joyous 2025 G.C. Easter!

#TIMRAN@5


“Everyone should contribute to the ratification of a gender-responsive electoral law and to share activism- related content centered on women and politics.”
Mrs. Eyerusalem Solomon, Executive Directress of TIMRAN
#TIMRAN@5


TIMRAN WISHES A BLESSED GOOD FRIDAY-2025 G.C.
#TIMRAN@5


A panel discussion focused on the Women Peace and Security Agenda will be aired today on Amhara Media Corporation (AMECO) immediately after the 1:00 LT newsa. TIMRAN warmly invites you all to tune in and follow the discussion.


The FDRE Prime Minister has established an independent committee to recruit nominees for the Management Board of the National Election Board of Ethiopia (NEBE), including a Deputy Chairperson and two Board Members, in accordance with Article 5(1) of the NEBE Establishment Proclamation.
The committee is now inviting the public, political organizations, and CSOs to submit recommendations for qualified candidates.

This call for nominations comes as the 6-year term of the current Management Board has concluded. Board members are eligible for reappointment for a second term.

Women must take the lead!

We particularly encourage the nomination and support of qualified women candidates individuals who are committed to women’s rights and actively promote the participation of women in decision-making processes.

📝 How to Nominate
Please find the nomination form linked below:

Google Forms Link

#Ethiopia #WomenInLeadership #NationalElectoralBoard #NominationCall #PublicParticipation #WomensRights #TIMRAN@5


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሥራ አመራር ቦርድ የእጩነት ጥሪ

በምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ አንቀጽ 5(1) መሰረት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አመራር ቦርድ አንድ ምክትል ሰብሳቢ እና ሁለት የቦርድ አባላትን ጨምሮ እጩዎችን ለመመልመል ገለልተኛ የሆነ ኮሚቴ አቋቁሟል።

ኮሚቴው ህብረተሰቡን፣ የፖለቲካ ድርጅቶችን እና የሲቪክ ማህበራትን ብቁ የሆኑ እጩዎችን እንዲጠቁሙ ጥሪ አቅርቧል።

ይህ የእጩነት ጥሪ የቀረበው የአሁኑ የሥራ አመራር ቦርድ የስድስት ዓመታት የሥራ ዘመን በመጠናቀቁ ነው። ሆኖም ግን የቦርድ አባላት ለሁለተኛ ጊዜ ለመመረጥ ብቁ ናቸው።

ሴቷ ትምራን!

ለሴቶች መብት የሚተጉ እና የሴቶችን በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ውስጥ ተሳትፎን በንቃት የሚያበረታቱ ብቁ የሆኑ ሴት እጩዎችን ጥቆማ እና ድጋፍ እንዲደረግ እናበረታታ።

📝 የእጩነት ጥቆማ ሂደት
እባክዎትን ከዚህ በታች የተያያዘውን የእጩነት ፎርም ያግኙ፡፡

Google Forms Link

#ኢትዮጵያ #ሴቶችበአመራር #ብሔራዊምርጫቦርድ #የእጩነትጥሪ #የህዝብተሳትፎ #የሴቶችመብት #ትምራን@5


ezra ejigu dan repost

19 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.