በዓለም ላይ የሴቶች ጭቆና አሁንም አልቀረም፤ ነገር ግን በመማራቸው፣ መብታቸውን በመጠየቃቸው እና አብረው በመቆማቸው አሸንፈውታል-የጥምረቱ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ወርቅነሽ ቤጊ
ጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር መድረክ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር ሴቶች ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሚቀርብላቸው አጀንዳ እንዲያረቅቁ ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ላይ ያዘጋጀው መድረክ አዲስ አበባ ውስጥ ተካሄደ።
ጥምረቱን በጽ/ቤት የምታገለግለው እና ሴቶች ወደ ውሳኔ ሰጭነት እንዲመጡ ራእይ ሰንቃ የምትሠራው ትምራን የተሰኘችው ሀገር በቀል የሲቪክ ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ኢየሩሳሌም ሶሎሞን መድረኩን በንግግር ከፍተውታል።
በዚሁ ወቅት ባለፉት ሁለት ዓመታት ጥምረቱ ሴቶች በሀገራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዲኖራቸው ለማድረግ ያከናወናቸውን አንኳር ስኬቶች መካከል በዐሥር ክልሎች እና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች ተንቀሳቅሶ ለስድስት ሺህ ገደማ ሴቶች የአቅም ግንባታ በመስጠት አጀንዳዎቻቸውን ማሰባሰብ መቻሉንና የዐሥሩን ክልሎች አጀንዳ ለኮሚሽኑ ማስረከቡን ጠቅሰዋል።
ከ20 በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች በታደሙበት መድረክ ላይ ተርካንፊ ለዘላቂ ልማት የተሰኘ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር እና የጥምረቱ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ወርቅነሽ ቤጊ ተገኝተው ለተሳታፊዎች የሚከተለውን መልእክት አስተላልፈዋል።
“እናንተ ዛሬ የተቀመጣችሁበት ቦታ ብዙ ሴቶች ዋጋ ከፍለውበታል፣ ተርበውበታል፣ ታስረውበታል፣ ሞተውበታል። መብትን እንዲሁ ማንም አይሰጥም፤ መጠየቅ ያስፈልጋል። ጠያቂዎች መሆን፣ ለመብት፣ ለእውነት፣ ላመኑበት ዓላማ መቆም ያስፈልጋል። ሁላችሁም ራሳችሁን እንደ ሴት ማየት አለባችሁ። የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ተወዳዳሪ ብትሆኑም እኅታችሁ ስትጎዳ፣ ስትገፋ ድምፅ መሆን አለባችሁ። እዚህ ላይ በደንብ ልትሠሩ ይገባል። ከፋፍለው እንዲጥሏችሁ አትፍቀዱ፤ ተመካከሩ፤ ተደጋገፉ። አንዷ የማታውቀውን አንዷ ልታውቅ ትችላለች። አንብቡ፤ ተማሩ፤ የተማረች ሴት ነች ልቃ የምትሄደው እና አሸናፊ የምትሆነው። በዓለም ላይ የሴቶች ጭቆና አሁንም አልቀረም፤ ነገር ግን በመማራቸው፣ መብታቸውን በመጠየቃቸው፣ አብረው በመቆማቸው አሸንፈውታል። ስለሆነም አትፍሩ፤ መብታችሁን ጠይቁ።”
#TIMRAN@5