በሁሉም ክልል ብሔር አካባቢ በወያኔ ይመራ የነበረውን ፌኩን የፌደራሊስት ሃይል 1001% እንደ አደረጃጀት አከርካሪውን ሰብረን ውልቅልቁን አውጥተነዋል። መቼም እንዳይነሳ አድርገን ነው ድል የነሳነው። የሚቀረን በብልጽግና ፓርቲ እና በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ከዛሬ ነገ ከጥፋታቸው ይታረማሉ የበደሉትን ሕዝብና መንግሥት ይክሳሉ ተብለው ባላየና ባልሰማ ለጊዜው የታለፉና የተንጠባጠቡ (ዕድል ያገኙ) ተላላኪዎች ናቸው።እነሱም ቢሆን ለጊዜው መታለፉን እንደ አለማወቅ ወይም እንደ ድክመት የሚቆጥሩና በጥፋት መንገድ ለመረማመድ የሚሞክሩ፣ እውነተኛ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ መቃብር ጠባቂዎች ሆነው ለመታየት የሚሞክሩና ይህን ወርቃማ ዕድል የማይጠቀሙበት ከሆነ በሚገባቸው ቋንቋ የሚዳኙ ይሆናል። ያኔ ሁሉም ነገር ግልጽ ሆኖ ይገባቸዋል።