Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ይህን ድንቅ ፕሮግራም ፀረ-ኦርቶዶክስ ተብለው በግልጽ ከሚታወቁት በላይ የሚቃወሙት ወይም ለማጥላላት የሚሞክሩት በተለይም በለውጡ ዋዜማና ለውጡን ተከትሎ ወደፊት እንዲመጡ የተደረጉትና ኦርቶዶክስ ልትጠፋ ነው እያሉ በኦርቶዶክስ በኩል የዶ/ር ዐብይን መንግሥት ለመጣል በእነ ጌታቸው አሰፋ ቡድን በደህንነት መስሪያ ቤቱ የተመለመሉና ለ27 ዓመትም ፀረ-ኦርቶዶክስ ነው የሚባለውን ወያኔን ሲያገለግሉ የኖሩ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ አቀንቃኝ መምህር አባ ዲያቆን ቄስ ተብዮ ማፍያና ማፈሪያ የሆኑ ታጋዮች ናቸው።ለእነዚህ ሰዎች እንዲህ አይነት ፕሮግራም ሰላም አይሰጣቸውም። የሚፈልጉት ሰላም ሳይሆን አመጽ ዘማሪ ሳይሆን ዘማዊ ሲበዛ ማየት ነውና ተቆርቋሪ መስለው ሲስተማቲካሊ ሲያጣጥሉ ሊታዩ ይችላሉ። እነዚህ በደህንነት መስሪያ ቤቱ ስር ተጠርንፈው ቤተክርስቲያንን ከላይ እስከታች በመቆጣጠር የኦርቶዶክስን አከርካሪ ለመስበር በአንድ በኩል ለ27 ዓመት ሲነዙት የነበረውን የሀሰት ትርክት ለውጡን ተከትሎ በሌላኛው በኩል መጥተው ለዛ ትርክት ማረጋገጫ ማህተም ለመምታት የተንቀሳቀሱና የሚንቀሳቀሱ ናቸውና ሁሉም ሊነቃባቸው ይገባል። ይህን ፕሮግራም ሲቃወም ወይም በተጠና መንገድ ለማጣጣል ሲሞክር የምታዩት የኦርቶዶክስ ተቆርቋሪ መሳይ መምህር ዲያቆን አባ ወይም ሰባኪ ተብዮ ካያችሁ ወዲ በሉት። በርግጠኝነት የእነ ጌታቸው አሰፋ ቡድን አባል የሆነ ወንበዴ ማፍያ ነው።