ታምሪን ሚዲያ(Tamrin Media)✍✍✍✍✍


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


Introducing daily news and information all over the world including our country ethiopia
ለፈጣን እና ተዓማኒ መረጃዎች ቻናላችንን ይቀላቀሉ። 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ቻናላችንን በመቀለቀል ወቅታዊ መረጃዎቸችን በፍጥነት ያግኙ👇👇👇
https://t.me/Tamrinmedia
✉️inbox 👉 @tamrin_bot

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


በጉጂ ዞን በመሬት መደርመስ የ8 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በጎጂ ዞን ሳባ ቦሩ ወረዳ በባሕዊ መንገድ ማዕድን እያወጡ በነበረው ሰዎች ላይ በደረሰው የመሬት መደርመስ የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ኮሚኒኬሽን ገልጸዋል፡፡ የዞኑ ኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ አሸናፊ ዳንቆ ለዲዳቢሊው እንደገለጹት በትናትናው ዕለት 9፡00 ገደማ አደጋው መድረሱን ገልጸው በቦታው በባሕላዊ መንገድ ሲያወጡ የነበሩ ሕይወታቸው ያለፈው 8ቱ ሰዎች አስከረን ዛሬ መውጣቱን አመልክተዋል፡፡

‹«ቦታው ጉጂ ዞን ሳባ ቦሩ ወረዳ ቃቲቻ የሚባል ቀበሌ ውስጥ ነው፡፡ በትናንትናው ዕለት ከ9፡00 በኋላ ነው ድርጊቱ የተፈጠረው፡፡ በባሕላዊ መንገድ ማዕድን በማውጣት እየሠሩ የነበሩ ሰዎች ላይ አፈር ተንሸራርቶ የስምንት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ ሕይወታቸውን ለማሻሻል በባሕላዊ መንገድ የሚሠሩ ሰዎች ናቸው መሬት ተንሸራርቶ ነው ሕይወታቸው ያለፈው አስከረናቸው ወጥቷል›› ብለዋል ።

ሳባ ቦሩ ወረዳ ከጉጂ ዞን አስተዳደር መቀመጫ ከሆነችሁ አዶላ ከተማ 70 ኪ.ሜ ገደማ ላይ የሚትገኝ ወረዳ ናት፡፡


🇮🇳 😎

ከአዲስ ፍቅረኛዋ ጋር ለመኖር የባሏን ኩላሊት ያሸጠችው ህንዳዊት

ኩላሊቱ በጥቁር ገበያ ቢሸጥ ለሴት ልጃቸው የትምህርት ወጪና ጥሎሽ እንደሚሆን አሳምና ነው የተሸጠው

ከኩላሊት ሽያጭ የተገኘውን ከ11 ሺህ በላይ ዶላር በፌስቡክ ከተዋወቀችው አዲሱ ፍቅረኛዋ ጋር እየተዝናናችበት ነው ተብሏል

በምዕራብ ቤንጋላ ሳንካሬል በተባለች ከተማ ነዋሪ የሆነችው እንስት ባሏ የአካል ክፍሉን እንዲሸጥ ያሳመነችው የሴት ልጃችን የትምህርት ወጪ ለመሸፈንና ለትዳር እድሜዋ ሲደርስ ለጥሎሽ የሚሆን ገንዘብ እንዳንቸገር በሚል ነው።

ባል መጀመሪያ ላይ የሚስቱን አንድ ኩላሊትህን ሸጠን ችግራችን እንለፍ በሚለው ሀሳብ በፍፁም እንደማይቀበለው ቢገልፅም የወራት ውትወታዋ አቋሙን እንዲለውጥ አድርጎታል።

ባል የቤተሰቡን ወቅታዊ የገንዘብ ችግር እና የልጁን የወደፊት ህይወት ለማቃናት መስዋዕትነት መክፈሉ ጥቅሙ እንደሚያመዝን አምኖበት የሚስቱን ጥያቄ መቀበሉን ያወሳል።

በህንድ የሰው የአካል ክፍልን መሸጥ ወንጀል በመሆኑ የኩላሊት ሽያጩ ሚስት በፈለገችበት ጊዜ አልተካሄደም፤ በጥቁር ገበያ ኩላሊት ገዥ ፍለጋው አንድ አመት ወስዷል ይላል የሂንዱስታን ታይምስ ዘገባ።

ከሶስት ወራት በፊት ስሙ ያልተጠቀሰውን ህንዳዊ ኩላሊት የሚገዛ አንድ ሰው ተገኝቶ 1 ሚሊየን የህንድ ሩፒ (11 ሺህ 500 ዶላር) ለሚስቱ መሰጠቱንም ዘገባው ጠቅሷል።

ድብቅ አቅዷን ለማሳካት ረጅም ጊዜን የጠበቀችው ሚስት ከባሏ አንድ ኩላሊት ሽያጭ የተገኘው ገንዘብ በእጇ እንደገባ በቤቷ ማደርን በመተው አድርሻዋን ታጠፋለች።

ጉዳዩ ግራ ያጋባው ባል የሚስቱን መጥፋት ለፓሊስ ሲያሳውቅ ልቡን በሀዘን የሚሰብር መረጃ ደርሶታል።

የባሏን ኩላሊት በልጃቸው አመካኝታ ያሸጠችው እንስት ባራክፖር በተባለ ከተማ በፌስቡክ ከተዋወቀችው አዲስ "ፍቅረኛዋ" ጋር እንደምትኖር ለማወቅ ተችሏል፡፡

ክህደት የተፈጸመበት ባል ከፖሊስ በተሰጠው ጥቆማ ሚሰቱና አዲሱ ፍቅረኛዋ ወደሚኖሩበት ቤት ከ10 አመት ልጃቸውና ቤተሰቦቻቸው ጋር ቢያቀናም የልጁ እናት ሚስቱ ከቤት አልወጣም ብላለች።

በር ለመክፈት ፈቃደኛ ካለመሆኗ ባሻገር ለልጇ አባት "የፈለከውን ነገር ማድረግ ትችላለህ፤ የፍቺ ማመልከቻ እልክልሀለው" ማለቷም ልቡን እንደሰበረው ተናግሯል።

ግለሰቡ በተደራረበ ሀዘን ውስጥ ልጁን በብቸኝነት ማሳደግ ጀምሯል።


በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ተከስቶ የነበረውን የእሳት አደጋ መቆጣጠር ተቻለ
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ቡልቡላ 40/60 እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ወደ ሌላ ቦታ ሳይዛመት መቆጣጠር መቻሉ ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ፥ የእሳት አደጋው ዛሬ ከቀኑ 11 ሰዓት ከ 10 ደቂቃ አካባቢ ተከስቷል።

በአካባቢው በሚገኘው በአንድ ጅምር ሕንጻ ግራውንድ ላይ የተከማቸ የሕንጻ መሳሪያ ልዩ ልዩ ቁሳቁስ ላይ የእሳት አደጋ አጋጥሞ እንደነበረም ነው የገለጹት።

እሳቱን ለማጥፋት የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ባደረጉት ርብርብ እሳቱ ወደ ሌላ ቦታ እንዳይዛመት በማድረግ መቆጣጠር መቻሉንም ተናግረዋል ባለሙያው፡፡

የእሳት አደጋውን ለማጥፋት ስድስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና 2 የውሃ ቦቴ ከ40 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች መሰማራቱን አንስተው ፥ በአደጋው በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩንና በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት እየተጣራ መሆኑን አመልክተዋል።


የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ ብርሃኑ አዴሎ፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን እንዲመሩ ተሾሙ

በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የስልጣን ዘመን ለስድስት ዓመት ገደማ የካቤኔ ጉዳዮች ኃላፊ ሆነው የሰሩት አቶ ብርሃኑ አዴሎ፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን (ኢሰመኮ) እንዲመሩ በፓርላማ ተሾሙ።

አቶ ብርሃኑ የብሔራዊው የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት፤ ተቋሙን ለአምስት ዓመታት የመሩትን ዶ/ር ዳንኤል በቀለን በመተካት ነው። ዶ/ር ዳንኤል ከኃላፊነታቸው የተሰናበቱት፤ የስራ ዘመናቸው ባበቃበት ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ነበር።

ላለፉት አምስት ወራት ኢሰመኮን የመምራት ኃላፊነት በተጠባባቂነት ተረክበው የቆዩት የእርሳቸው ምክትል የነበሩት ራኬብ መሰለ ናቸው።

ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሆነው ኢሰመኮ፤ ለሰብዓዊ መብቶች መስፋፋት፣ መከበር እና ጥበቃ የመስራት ስልጣን በአዋጅ የተሰጠው ነው።

በ2012 ዓ.ም. የተሻሻለው የኢሰመኮ ማቋቋሚያ አዋጅ፤ ተቋሙን በዋና ኮሚሽነርነት፣ በምክትል ዋና ኮሚሽነርነት እና በዘርፍ ኮሚሽነርነት የሚያገለግሉ ኃላፊዎች በተወካዮች ምክር ቤት እንደሚሾሙ ይደነግጋል። 

ዛሬ ሐሙስ ጥር 22፤ 2017 በተካሄደው የተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ፤ ኮሚቴው የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር እንዲሆኑ አቶ ብርሃኑ አዴሎን በዕጩነት አቅርቧል። ላለፉት አስር አመታት በግል አማካሪነት እና ጠበቃነት እየሰሩ የቆዩት አቶ ብርሃኑ፤ በኢህአዴግ የስልጣን ዘመን በከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ የሰሩ ናቸው። 
https://t.me/Tamrinmedia


ቀሲስ በላይ መኮንን በ5 ዓመት ጽኑ እስራትና በ10 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ተቀጡ።
https://t.me/Tamrinmedia


ሰበር ዜና

1,713 ኢትዮጵያዊያን ተጠርንፈው ሊባረሩ ነው

በዶናልድ ትራንፕ አስተዳደር ዉሳኔ ምክንያት ወደ ሀገራቸዉ ከሚመለሱ ሰነድ አልባ ዜጎች መካከል 1,713 ኢትዮጵያዊያን ተለይተዋል ተብሏል።

የትራምፕ አስተዳደር ላሁኑ ዙር ለማባረር ካዘጋጃቸው 1.4 ሚሊዮን ዶክመንት የሌላቸው ስደተኞች ውስጥ 1,713 ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል

የሚያሳዝነው አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን እርስ በርሳቸው የአሜሪካ መንግስት ላስቀመጠው የብር ሽልማት ብለው እየተጠቋቀሙ መሆኑ ተሰምቷል
አይ ሀበሻ😂😂


መነኸሪያ ሬዲዮ ይቅርታ ጠየቀ፣ ፕሮግራሙ ታግዷል።

ቲክቶከር ሮማን በመናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 በተባባሪ አዘጋጆች ከሚቀርቡ ዝግጅቶች መካከል አንዱ በሆነው  የብርሐን መንገድ በተሰኘ ፕሮግራም ላይ መቅረቧ ይታውቃል፡፡

የቀረበችው “ማኅበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ ማዋል” በሚል ከዚህ በፊት በማህበራዊ ሚዲያ ያስተላለፈችውን የተዛቡ አመለካከቶችን በተመለከተ ይቅርታ ለመጠየቅ እና ከስህተቷ ሌሎች ትምህርት እንዲወስዱ ነው፡፡

በመሆኑም በርካታ አድማጮቻችን በግለሰቧ መቅረብ መከፋታቸውን ነግረውናል፡፡ ለተፈጠረው ጉዳይ ጣቢያችን ይቅርታ እየጠየቀ ላልተወሰነ ጊዜ በተባበሪ አዘጋጆች የሚቀረበው የብርሐን መንገድ የተሰኘ ፕሮግራም የታገደ መሆኑን እናሳወቃለን፡፡ 

በተጨማሪም በቀጥታ ስርጭት ወቅት የፕሮግራሙ አዘጋጆች  በቀጥታ ስልክ መስመር የገባ አድማጭን ያቋረጡበት መንገድ  ከሙያ ስነምግባር ያፈነገጠ በመሆኑ አጣርተን እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
እውነትም መናኸሪያ😀
https://t.me/Tamrinmedia




ፕሬዝደንት ትራምፕ ወደ ስልጣን እንደመጡ የመጀመሪያ ስራቸው ይሆናል ተብሎ የሚገመተው ሰነድ አልባ ዜጎችን ጠራርጎ ማስወጣት ወይም ዲፖርት ማድረግ ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞ ሰነድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን ቁጥር 10500 እንደሚደርስ እየተነገረ ይገኛል።እናም እነዚህ ዜጎች በቅርብ ቀን እኛን የሚቀላቀሉ ይሆናል🙄
https://t.me/Tamrinmedia


ተይዘዋል‼
*
**
በትላንትናው እለተ በኦሮቶዶክስ እምነት የቅዱስ ሚካኤል ታቦት ላይ ሲያሾፉ የነበሩት እነዚህ የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል::

በህዝቡ ጥቆማ መሰረት ነዉረኞቹ በአስቸኳይ በቁጥጥር ስር እንዲዉሉ ላደረጉት ለአምቦ ዩኒቨርሲቲ እና ለኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ምስጋና ይገባቸዋል።
https://t.me/Tamrinmedia




የቀድሞው የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በ ትራምፕ በዓለ ሲመት ላይ ተገኝተዋል።


መረጃ‼️

የመንግስት ሚድያዎች በተለይ የመንግስት አመራሮች ላይ በታጣቂዎች የሚፈፀሙ ጥቃቶች እንዳይዘግቡ ጥብቅ መመርያ እንደተላለፈላቸው .ተሰምቷል
https://t.me/Tamrinmedia


ስልጣን በይፋ የተረከቡት ትራምፕ "የአሜሪካ ወርቃማ ዘመን አሁን ይጀምራል" ሲሉ ተናገሩ

ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው
በዩናይትድ ስቴትስ ካፒቶል ሮቱንዳ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።የአሜሪካ ወርቃማ ዘመን አሁን ይጀምራል በማለት በንግግራቸው ላይ "ሰላም እና አንድነት" በሀገሪቱ "ያብባል እናም አሜሪካ ትከበራለች ሲሉ ትራምፕ ገልፀዋል። ትራምፕ የባይደን አስተዳደርን በተመለከተ የስደተኞችን ቀውስ በመፍጠር በመንግስቷ ላይ “የመታመን” ችግር በህዝበ ዘንድ አስከትሏል ሲሉ ተናግረዋል ።

የቴክኖሎጂ ቢሊየነሮች፣ የካቢኔ ተሿሚዎች እና የቀድሞ ፕሬዚዳንቶችን ጨምረው በዩናይትድ ስቴትስ ካፒቶል በተካሄደው የበዓለ ሲመት ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል። ትራምፕ ቃለ መሃላ ከመፈፀማቸው ጥቂት ደቂቃዎች በፊት ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ተከትሎ ለቤተሰቡ አባላት ይቅርታ ሰጥተዋል። ቤተሰቤ እኔን ለመጉዳት ባለው ፍላጎት ብቻ የማያባራ ጥቃቶች እና ዛቻዎች እንዲሁም ክስ ደርሶባቸዋል ሲሉ ባይደን ተደምጠዋል። ከሁሉ የከፋው የወገንተኝነት ፖለቲካ መሆኑን ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ባይደን በመግለጫቸው ገልፀዋል።


አክለውም እንደ አለመታደል ሆኖ እነዚህ ጥቃቶች ያበቃል ብዬ ለማመን ምንም ምክንያት የለኝም ብለዋል። የባይደን የስልጣን ዘመን የመጨረሻ የይቅርታ እድል ያገኙት የባይደን ሁለት ወንድሞች ጄምስ እና ፍራንሲስ ይገኙበታል። እንዲሁም በዝርዝሩ ውስጥ የባይደን እህት ቫለሪ እና ባለቤቷ ጆን ይገኙበታል።ሳራ የተባለችው የጄምስ ባይደን ሚስት በተመሳሳይ የይቅርታ እድሉ ተጠቃሚ ናቸው።ትራምፕ ስልጣን መረከባቸውን ተከትሎ የአስፈፃሚ ትዕዛዞች አካል በመሆን "ብሄራዊ ድንገተኛ አደጋ" ለማወጅ ተዘጋጅተዋል።


ትራምፕ ዳግም ወደ ስልጣን መመለሳቸውን ተከትሎ ለአሜሪካ ህዝብ መልዕክት አስተላልፈዋል። አንድ ነገር ማድረግ የማይቻልን ነው ብሎ ማመን እንደሌለባችሁ ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ በፊታችሁ ቆሜያለሁ ሲሉ ተደምጠዋል። በአሜሪካ ውስጥ የማይቻለውን ማድረግ እንደምንችል አሳይተናል ብለዋል ። ከዚህ ቀን ጀምሮ ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ሉዓላዊ እና ነጻ ሀገር ትሆናለች በማለት አክለዋል። "መጪው ጊዜ የእኛ ነው፤ እናም ወርቃማው ጊዜያችን ገና ጀምሯል ብለዋል።ተቃዋሚዎች ባነሮችን እያውለበለቡ እና የመጪውን የትራምፕ አስተዳደር ፖሊሲዎችን በማውገዝ በኋይት ሀውስ ተቃውሞ አሰምተዋል።
https://t.me/Tamrinmedia


በጥምቀት በዓል ላይ የታዪ የወጣቶች ወኔ በጣም አስገራሚ ነው
https://vm.tiktok.com/ZMk9ufJNw/

15 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.