አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ ፤ የግሮቭ ጋርደን ባለቤት እንደፃፈው!...
***
ግሮቭ ጋርደን ወደ ትዝታነት ተቀይሯል።
ለወንዝ ዳርቻ ልማት ቦታውን ለቋል።
ላለፉት አምስት አመታት አብራችሁን ለነበራችሁ የዕለት ተዕለት ደንበኞቻችን፣ ሠርጋችሁን በግሮቭ ጋርደን ለደገሳችሁ ሙሽሮቻችን፣ የፍቅር ጥያቄያችሁን በግሮቭ ጋርደን ያደረጋችሁ እጮኛሞቻችን፣ልደታችሁን እኛ ጋ ላደረጋችሁ ልጆቻችን፣
የጋብቻ በዓላችሁን በግሮቭ ላከበራችሁ አንጋፋዎቻችን፣ በኦፕን ኤር ሲኒማችን ተቃቅፋችሁ ለደመቃችሁ ፍቅረኞቻችን፣
በሰርከስ ዝግጅቶቻችን እርካታን ለሸመታችሁ ቤተሰቦቻችን፣ እግር ኳስ በሜዳችን ለተጫወታችሁም በስክሪናችን ለኮመኮማችሁም የስፖርት ወዳጆቻችን፣
መጽሐፎቻችሁን ላስመረቃችሁ ደራሲዎቻችን፣
ፊልሞቻችሁን ለቀረፃችሁ አርቲስቶቻችን፣
ክሊፖቻችሁን ላስከሸናችሁ ድምፃውያኖቻችን፤
ለሁላችሁም ከልብ የመነጨ ምስጋናችን ይድረሳችሁ።
በአገልግሎታችን ቅር ለተሰኛችሁ ምህረታችሁን እንሻለን።
ለተደሰታችሁ ደግሞ የትዝታችሁ አካል ስለነበርን ደስታችን ወደር የለውም።
የግዮን ሆቴል ሰራተኞችና አመራሮች ለነበረን ቆይታ እናመሠግናለን።
ባስከፋናችሁ ይቅርታችሁን እንሻለን።
ላስከፋችሁን ደግሞ ይቅር ብለናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!
አሽቃባጭም አልተረፈም ዘንድሮማ😂😂😂
https://t.me/Tamrinmedia