ጅማ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ተመደበለት፡፡
በዚህም ከህዳር 5/2017 ዓ.ም ጀምሮ የፍትህ ሚኒስትር ሀና አርዓያስላሴ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው እንዲሰሩ መመደባቸውን በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን ህዳር 4/2017 ዓ.ም ተፈርሞ የወጣ የምደባ ደብዳቤ ያሳያል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር በሚያዝያ 2014 ዓ.ም ገቢራዊ ባደረገው አዲስ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ምደባ መሰረት፣ የቀድሞዋ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሠ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ እና ጥላሁን ተሾመ (ፕ/ር) ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡
@tikvahuniversity