የ58 ዓመቱ ማይክ ታይሰን ከ27 ዓመቱ ጄክ ፖውል ጋር ነገ ቡጢ ይገጥማል
ኅዳር 5/2017 (አዲስ ዋልታ) ዝነኛው አሜሪካዊ የከባድ ሚዛን ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን ራሱን ከፕሮፌሽናል ውድድር ካገለለ ከ19 ዓመታት በኋላ ወደ ውድድር ሊመለስ ተመልሷል።
የ58 ዓመቱ ማይክ ታይሰን ነገ ከ27 ዓመቱ የቀድሞው ዩቱዩበር ጄክ ፖውል ጋር በኤቲ ኤንድ ቲ ስታዲየም ከ19 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቡጢ ይገጥማል ሲል ሲኤንኤን ዘግቧል።
ታይሰን በዚህ ዕድሜው ወደ ፕሮፌሽናል የቡጢ ውድድር መመለሱ በቀደመው ጊዜ ካካሄዳቸው ውድድሮች የተሻገረ የነርቭ ጤንነት ችግር ውጤታማነት እንቅፋት ሊሆንበት ይችላል ተብሏል።
አሁን በሚደረገው ውድድርም ላይ ከበድ ያለ ጉዳት ሊገጥመው ስለሚችል ለጤንነቱ አስጊ መሆኑ ተገልጿል።
የሁለቱን ፕሮፌሽናል ቡጢኞች ግጥሚያ ማን ያሸንፋል ለሚለው ጥያቄ በርካታ የቀድሞ ቦክስኞችና ባለሙያዎች የአሸናፊነት ግምታቸውን ለታይሰን ሰጥተዋል።
ጄክ ፖውል እስካሁን ካደረጋቸው 10 ውድድሮች በአንዱ ብቻ የተሸነፈ ሲሆን ማይክ ታይሰን ደግሞ ካደረጋቸው 56 ውድድሮች 50 አሸንፏል። ከእነዚህ ውስጥ 44ቱን በዝረራ ነው ያሸነፈው።