🔺በሙስሊሞች መካከል እየተፈፀሙ ካሉ የሽርክ ተግባራቶች መካከል፡ ክፍል 5
~~~
5 ﺍﻟﺘﺒﺮﻙ ﺑﻘﺒﺮ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﺃﻭ ﺍﻟﺘﻤﺴﺢ ﺑﻪ ﺃﻭ ﺍﻟﺴﺆﺍﻝ ﻋﻨﺪﻩ، ﻭﻛﺬﺍ ﻏﻴﺮﻩ ﻣﻦ ﻗﺒﻮﺭ ﺍﻟﺼﺤﺎﺑﺔ ﻭﺍﻵﻝ ﻭﺍﻷﻭﻟﻴﺎﺀ ﺍﻟﺼﺎﻟﺤﻴﻦ، ﻭﻛﺬﺍ ﺍﻟﺘﺒﺮﻙ ﺑﺎﻟﺸﺠﺮ ﻭﺍﻟﺤﺠﺮ ﻭﻧﺤﻮﻫﻤﺎ
በነብዩ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ መቃብር ተበሩክን/ ረድኢትን መፈለግ ወይም ሂዶ መተሻሸት / መንከባለል ወይም ሀጃው እንድፈፀምለት ሂዶ መጠየቅ እንደዚሁም ከነብዩ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ውጭ ያሉ እሰሀብዮች (ሪዷኑሏሂ አለይሂም) ቀብር ላይ ይመስል፣የአሏህ ደጋግ ባሪያዎች ቀብር ብሎም በተለያዩ ዛፎች ፣ድንጋይና መሰል ነገሮች ተበሩክ ማድረግ/ ረድኤትን መሻት።ሁሉም የሽርክ ተግባር ናቸው።
እንዲሁም ሌላኛው
6 ﺍﻟﺴﺤﺮ ﻭﺍﻟﻜﻬﺎﻧﺔ ﻭﺍﻟﺬﻫﺎﺏ إلى ﺍﻟﻤﺸﻌﻮﺫﻳﻦ ﻭﺍﻟﻤﻨﺠﻤﻴﻦ
⑥ አስማትና ጥንቆላ እንደዚሁም ወደ አጭበርባሪዎችና ኮኮብ ቆጣሪዎች መሄድ።
👌ﺭﻭﻯ ﺃﺣﻤﺪ ﻭﺍﻟﺤﺎﻛﻢ ﻭﺻﺤﺤﻪ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ ﻣﻦ ﺣﺪﻳﺚ ﺃﺑﻲ ﻫﺮﻳﺮﺓ ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ ﺃﻥ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻗﺎﻝ : « ﻣﻦ ﺃﺗﻰ ﻋﺮﺍﻓﺎً ﺃﻭ ﻛﺎﻫﻨﺎً ﻓﺼﺪﻗﻪ ﺑﻤﺎ ﻳﻘﻮﻝ ﻓﻘﺪ ﻛﻔﺮ ﺑﻤﺎ ﺃﻧﺰﻝ ﻋﻠﻰ ﻣﺤﻤﺪ » .
ኢማሙ አህመድና ኢማሙ አልሀኪም የዘገቡትና ኢማሙ አል አልባኒይ ሶሂህ ያሉት ሀድስ አባ ሁረይራ ነብዩ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ እንድህ አሉ አለ" አዋቂ ወይም ጠንቋይ ዘንድ የሄደና የሚናገረውን ሀቅ ብሎ የተቀበለው በእርግጥ በሙሀመድ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ላይ በወረደው ( በቁርአን) ክዷል"።
‼️ማስጨበጫ〰
ሲህር ወይም አስማት የሚባለው አደገኛ በሽታ ስለሆነ አሏሁ ሱብሀነሁ ወተአላ ቁርአን ላይ እሱን ያስተማረና በሱ የሰራ በጌታው የካደና በአኼራ ምንም ድርሻ የሌለው መሆኑን ገልፅዋል።ሲህር የሰራም ፣ያሰራም፣የተማረም፣ያስተማረም፣በድርጊቱ የወደደም ከኢስላም እንደሚወጣ ኦለማዎች ያስቀምጣሉ።
7 ﺍﻟﺤﻠﻒ ﺑﻐﻴﺮ ﺍﻟﻠﻪ تعلى
⑦ከአሏህ ውጭ ባሉ አካላቶች መማል፡
👌 ﺭﻭﻯ ﺃﺣﻤﺪ ﻭﺍﻟﺘﺮﻣﺬﻱ ﻭﺍﻟﺤﺎﻛﻢ ﻭﺻﺤﺤﻪ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ ﻋﻦ ﺍﺑﻦ ﻋﻤﺮ ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻬﻤﺎ ﺃﻥ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻗﺎﻝ : « ﻣﻦ ﺣﻠﻒ ﺑﻐﻴﺮ ﺍﻟﻠﻪ ﻓﻘﺪ ﺃﺷﺮﻙ » ،
ኢማሙ አህመድ፣ኢማሙ አቲርሚዚይና ኢማሙ አል ሀኪም እንደዘገቡትና ኢማሙ አል አልባኒይ ሶሂህ እንዳሉት ኢብኑ ኡመር ረደየሏሁ አንሁ እንድህ አሉ" የአሏህ መልእክተኛ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ እንድህ አሉ" ከአሏህ ሱብሀነሁ ወተአላ ውጭ ባለ ነገር የማለ በእርግጥም አጋርቷል"።
‼️ልብ በሉ〰
ከአሏህ ውጭ ባለ ነገር መማል ከከባኢር ወንጀሎች ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ወንጀል ነው።በአሏህ ምሎ ውሸት ማውራት ከአሏህ ውጭ ባለ አካል ምሎ እውነት ከማውራት ይሻላል።
https://t.me/WATESiMU