የክርስትና መልስ dan repost
✨ ርዕስ፡ "ደም ሳይፈስ ስርየት የለም" - ለምን? ✨
❓ ጥያቄ፡
"ደም ሳይፈስ ስርየት የለም" ይላል መጽሐፍ ቅዱስ። ታዲያ ለምንድነው ደም መፍሰስ ያስፈለገው? ፈጣሪ የደም መስዋዕት ይፈልጋልን?
መልስ፡
ይህን ጥያቄ በሁለት አቅጣጫዎች እንመልከተው፡
1. ከክርስቶስ አንጻር ✝️
• መጀመሪያ ሙሉውን ብናነበው መልሱ እዚያው ጳውሎስ ይነግረናል ዕብራውያን 9፡10 ላይ እንዲህ ይላል “ይህም ለአሁኑ ጊዜ ምሳሌ ነው”በማለት ይናገራል። ጌታ ኢየሱስ ከመጣቱ በፊት ሰዎች እሱን እንድረዱት እና እንድቀበሉት ምሳሌ ገና አስቀድሞ ማስቀመጥ አስፈላጊ ነበር። ለዚያም ነው ጳውሎስ የብሉይ ኪዳንን ሥራዓት በመጥቀስ ማስተማር ያስፈለገው እንጂ እግዚአብሔር የእንስሳትን ደም የሚፈልግ ሁኖ ሳይሆን ሊመጣ ላለው ለሰው ልጆች ሲል ደሙን ሊያፈስ ላለው ምሳሌ ይሁኖ ዘንድ እግዚአብሔር በእንስሳት ደም ይቅር እንደሚላቸው እንስሳትን እንድሰው አዘዛቸው።
• በብሉይ ኪዳን የእንስሳት መሥዋዕት ለኃጢአት ይቅርታ ይቀርብ ነበር። ይህ መሥዋዕት የኢየሱስን ፍጹም መሥዋዕትነት ያመለክታል። ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ተብሎ ተጠርቷል። (ዮሐንስ 1:29)
• እስራኤላውያን ከግብፅ ባርነት ነፃ የወጡበት የፋሲካ በዓል ላይ የሚቀርበው የበግ መሥዋዕት የኢየሱስን መሥዋዕትነት ያመለክታል። የበጉ ደም በእስራኤላውያን ቤቶች ላይ ተቀብቶ ሞት ከእነርሱ እንዲያልፍ እንዳደረገው፣ ይህ ደም የኢየሱስን ደም ምሳሌ ነው፣ የኢየሱስ ደምም ከኃጢአት ሞት ነፃ ያደርገናል።የኢሳይያስ 53 ፡5 "እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።" እንድል ጌታ ኢየሱስ ሰው መሆን እና ሞቶ ስለሰው ልጆች ደሙን ማፍሰስ በደሙም የሰው ልጆችን ማዳን ግድ ነበር ።
• እግዚአብሔር ያለ ደም መፍሰስ ሊያድን ይችል ነበር? የሚል ቢኖር አዎ ይችል ነበር ግን ደግሞ ስለመቻል ስላለምቻል ሳይሆን አዳም በሠራው ኃጢአት ምክንያት ሞት በሰው ልጆች ላይ ተፈርዶአል። እግዚአብሔር ያለ ምንም ቅጣት ሰዎችን ቢያድን፣ ይህም የእግዚአብሔርን ፍትሃዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነበር።ያለ ደም መፍሰስ ይቅርታ ቢደረግ፣ የኃጢአት ክብደት በቀላሉ የሚታይ ነገር ይሆናል።
• የደም መስዋዕትነት የኃጢአትን አስከፊነት፣ እና የህይወት ዋጋን ያሳያል። ስለዚህ ያለ ደም መፍሰስ ይቅርታ ቢደረግ የኃጢአት አስከፊነትን ማሳየት ይሳነው ነበር።እግዚአብሔር ያለ ምንም መስዋዕትነት ሰዎችን ቢያድን፣ የእርሱ ምህረት በቀላሉ የሚታይ ነገር ይሆናል።እግዚአብሔር አስቀድሞ በአዳም ላይ የሞትን ፍርድ አውጥቶአል። ይህንን ፍርድ ያለ ምንም ቅጣት ቢሽረው ቃሉን ያፈረሰ ይሆናል።
• በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ኃጢአት ከእግዚአብሔር ይለየናል እንዲሁም ሞትን ያመጣል።
• ደም የህይወት ምልክት ነው፣ ስለዚህም የኃጢአት ዋጋ ህይወት ነው።
• ይህም ማለት ኃጢአት በጣም ከባድ ከመሆኑ የተነሳ ህይወትን መስዋዕት ማድረግን ይጠይቃል።
• እግዚአብሔር የሰው ልጆችን ስለሚወድ፣ ከኃጢአት ባርነት ነፃ ሊያወጣቸው ፈለገ።
• ነገር ግን፣ እግዚአብሔር ፍትሃዊ ነው፣ እናም ለኃጢአት ካሳ መቅረብ ነበረበት።
• ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ኃጢአት በመሸከም የእግዚአብሔርን ፍቅር እና ፍትህ በአንድ ጊዜ አሳይቷል።
• ኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢአት የሌለበት ፍጹም አምላክ በመሆኑ፣ የሰው ልጆችን ኃጢአት ሊሸከም ቻለ።
• የእርሱ ደም መፍሰስ የሰው ልጆች ከእግዚአብሔር ጋር እንዲታረቁ መንገድ ከፍቷል።
• የክርስቶስ መስዋዕትነት ፍፁም እና ምትክ የሌለው ነው።ከዚህም የተነሳ “ደም ሳይፈስስ ስርየት የለም” ተባለ
2. ከእኛ ከሰው ልጆች አንጻር
• እግዚአብሔር የእንስሳትን ደም አይፈልግም፣ ነገር ግን የልባችንን ንስሐ እና ለእርሱ መታዘዝን ይፈልጋል።
• በእኛ ውስጥ ያለውን ክፉ ባህሪ ለማስወገድ መንፈሳዊ ትግል ማድረግ አለብን።
• "የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን የመንፈስን ሰይፍ" በመጠቀም ከኃጢአት እንድንርቅ ተጠርተናል።
• “ደም ሳይፈስ ስርየት የለምና፤”ይህ ምክንያቱም ሥጋ እና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም የእግዚአብሔር ቃል የሆነው የመንፈስ ሰይፍ ነው የሚያስፈልገን።
• እንደ ኤርምያስ ነቢይ የተናገረው፡-“ከደም ሰይፉን የሚከለክል የተረገመ ነው።”ይህ ሰይፍ የሚያስወግደው የኃጢአትን ቁሳቁስ የሚኖርበትን ክፉ ደም የሚያፈስና እና በነፍሳችን ውስጥ ያደገውን ሥጋዊና ምድራዊ ክፉነት ነው።
• ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል የሚያደርገን ለኃጢአት ሞተን ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንድንሆን ነው።ይህ ለዘላለማዊ ደስታ የሚያመራ መንገድ ነው።
• ሰይፉን ከደም መከልከል ማለት ኃጢያትን ከመግደል መከልከል ነው።ስለዚያ ሰይፍ ደግሞ “ሰይፌም ሥጋን ትበላለች” ተብሏል።
• “ደም የተባለው የሥጋ ሥራ ኃጢያትን ነው። “እናንተ ግን በሥጋ ውስጥ አይደላችሁም” ሲል፤ ደግሞም “ስለዚህ በሥጋ ያሉት እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም” ሮሜ 8፡8-9።እንዲል