አሁናዊ ሁነት
ዓባይ ባንክ በ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት ብር 8.4 ቢሊየን ጠቅላላ ገቢ አስመዘገበ። ይህ የተገለፀው የባንኩ ባለአክሲዮኖች 15ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በአዲስ አበባ ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ዛሬ እየተካሄደ ባለበት ወቅት ነው።
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የዓባይ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ስብሳቢ ዶ/ር አምላኩ አስረስ ባለፈው በጀት ዓመት በባንክ ኢንዱስትሪው አውንታዊና አሉታዊ ሁኔታዎችን የፈጠሩ አለም አቀፋዊና አገራዊ ክስተቶች የነበሩ ቢሆንም ባንኩ በሁሉም የአፈፃፀም መለኪያዎች ውጤት ማስመዝገቡን ገልፀዋል።
በበጀት ዓመቱ የዓባይ ባንክ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ መጠን 52.6 ቢሊየን ብር መሆኑ ተገልጿል።
የዓባይ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ የኋላ ገሠሠ በበኩላቸው የባንኩ አጠቃላይ ሃብት ባለፈው በጀት ዓመት የ21 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ ብር 66.4 ቢሊየን የደረሰ መሆኑን እና ደንበኞቹ 3.5 ሚሊዮን መድረሳቸውን ገልፀዋል፡፡