ተወዳጅ መሆን ከፈለክ ወይም ሰዎች ትክረት እንዲሰጡክ ከፈለክ...
አንደኛ ስማቸውን አትርሳ። በየትኛውም ቋንቋ ስምህን እንደመስማት የሚስደስትህ ወይም ትኩረት እንድትሰጥ የሚያደርግህ ነገር የለም። ለምሳሌ ብዙ ህዝብ ባለበት መሃል ስምህ ሲጠራ ብትሰማ፤ ቆም፤ዘወር አትልም? ያንን ነው ልነግርህ የፈለኩት... ሰዎች እንዲወዱህ አሊያም ትኩረታቸውን እንዲሰጡህ ከፈለግክ፣ ስማቸውን አትሳሳት! እናት እና አባትህን 'አባዬ' እማዬ' እያልክ ተጣርተህ ትኩረት ካልሰጡህ.... ለስለስ ባለ ድምጽ ስማቸውን ጥራ፤ በትክክል ትኩረታቸውን ታገኛለህ ይህ የተፈጥሮ እውነታ ነውና።
ሁለተኛ ለሰዎች እውነተኛ የሆነ ፍላጎት እንዲሰማህ ከእነሱ ምንም ሳትጠብቅ ውደዳቸው። ያኔ እነሱ ባንተ ላይ ፍላጎት ኖራቸው -አልኖራቸው፣ ወደዱህ አልወደዱህ ያ ያንተ ጭንቀት አይሆንም። ደስታህ አንተ ለእነሱ ካለህ ስሜት የሚመነጭ ይሆናል።
ሶስተኛ አንተ ከምትወደው ነገር ይልቅ እነሱ ስለሚወዱት ነገር የማውራት ልምድ ይኑርህ። ሁሉም ሰው ፊቱን በፈገግታ የሚሞላው አንዳች የጨዋታ ርእስ አይጠፋውም። ምናልባት ፊልም ማየት፣ ማነቃቂያ መድረኮችን መሳተፍ፣ ጋለሪ መሄድ 'ጀማ' ሆኖ መጨዋወት ሌላም ሌላም በዙሪያህ ያሉ ሰዎች ፍላጎት ሊሆን ይችላል። ግድ የለህም የእነሱን ሙድ ለማራመድ ሞክር፤ እነሱም ያንኑ ያደርጉልሃል።
አራተኛ አቦ ፈገግ በላ!😁 ብዙ ጊዜ ፈገግታ ቁምነገር መስሎ አይታይህም። ወዳጄ ፈገግታ የሚጋባ አስማት ነው። ሰዎች ፈገግ ስትል በድብቁ አእምሯቸው አንተ ለእነሱ ጥሩ ስሜት እንዳለህ ይሰማቸዋል። በዚህም ሊወዱህ ግድ ይሆንባቸዋል ማለት ነው። ለመወደድ ብለህ ብቻ ሳይሆን ውስጥህ እርጋታ እና ሰላም እንዲሰማህ ከፈለግክ፤ ደስታ የሚታይበት ፊት ያንተ ይሁን።
ሃዬ እኒህ ሃሳቦች የዴል ካርኒጌ ናቸው። ከተመቹህ ተጠቀምባቸውና ህይወትህን ቀለል አድርገው።
አሃ ፈገግ በላ ደ'ሞ😁😄👌
መልካም እሁድ ትሁንላቹ😇credit: Teklu T.