#Psychology
አንድ የሳይኮሎጂ መምህር ወደ ክፍል ገብቶ የእለቱን ትምህርት ለመጀመር ወደ ቦርድ እንደዞረ ከተማሪዎቹ አንዱ ያፏጫል።መምህሩም ወደ ተማሪዎቹ ዞሮ ማን እንዳፏጨ ጠየቃቸዉ። ሁሉም ተማሪዎቹ ዝም አሉ።
ፕሮፌሰሩም ተረጋግተው"የዛሬዉን ሌክቸር ጨርሰናል፤ ከክፍል ከመዉጣቴ በፊት ግን አንድ ታሪክ ልንገራችሁ።" አላቸዉ ሁሉም ተማሪዎች በጉጉት ወደ መምህራቸዉ አፈጠጡ።"ትላንት ማታ እንቅልፍ አልወስደኝ ብሎ ሲያስቸግረኝ፣ወክ ለማድረግ ወደ ዉጭ ወጣሁ።ከአንድ ግሮሰሪ የምትወጣ ቆንጅዬ ወጣት ጋር ተገናኘን።ምሽት ስለነበረ ወደ ቤቷ ልሸኛት ተስማምተን እያወራን መንገዳችንን ቀጠልን።ባወራንባቸዉ ትንሽ ደቂቃዎች ዉጫዊ ዉበት ብቻ ሳይሆን ዉብ የሆነ አስተሳሰብ እንዳላት ለማወቅ አልከበደኝም።እኔ ፕሮፌሰር እንደሆንኩና የት እንደማስተምር ነግሬያት ስልክ ተልዋዉጠን በሌላ ጊዜ ለመገናኘት ቀን ወሰንን።ልንለያይ ስንል ግን 'አንድ ነገር ላስቸግርህ አንተ የምታስተምርበት ኮሌጅ የኔ ወንድም ይማራል በእኛ ግንኙነት እንዳይጎዳ' አለችኝ።ችግር የለዉም ብዬ ስሙን ስጠይቃት ነገረችኝ። ተመሳሳይ ስም ያላቸዉ ብዙ ተማሪዎች አሉ ።እንዴት ከዚያ ሁሉ ተማሪ ልለየዉ እችላለሁ? ስል ጠየኳት።
እሷም 'ወንድሜ አንድ መለያ ባህሪ አለዉ በእሱ ትለየዋለህ ፣ፉጨት ማፏጨት ይወዳል አለችኝ።"
ፕሮፌሰሩ ይህን ሲናገር ሁሉም ተማሪዎች ወዳፏጨዉ ልጅ ዞሩ።
ፕሮፌሰሩም "የሳይኮሎጂ PhDዬን ተምሬ እንጂ ገዝቼ አይደለም ያገኘሁት!!!!" 😏 በማለት ያፏጨዉን ልጅ ጆሮዉን ይዞ ከክፍል አስወጣዉ።
ችግሮችን ለመፍታት ሁልጊዜም ጭንቅላታችንን እንጠቀምበት!!!!
...✍Fikr Fantahun
ደና ሁኑልኝ 😊