የግጥሜ ርዕስ 🌹ማን ነዉ የሚነካዉ !?
ማን ነዉ የሚነካዉ ያን ጥቁር ካባየን
አላህ በቁርአኑ ቀድሞ ያዘዘዉን
የረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ሚስቶች የተዋቡበትን
እነዚያ ሰሀቦች የተገበሩትን
ማን ነዉ የሚነካዉ !!
ከኔ የሚያወልቀዉ !!
🌷💫🌷💫🌷💫🌷💫🌷💫🌷💫
አላወቁም እንዴ ዉበቴ መሆኑን
የፊትና በር መዝጊያ ሰበብ መሆኑን
ከቆሻሻ ዝንቦች እኔደሚጠብቀኝ
ልቡ ከታመመ እንደሚከልለኝ
አልተረዱም መሰል የኒቃብን ጥቅም
ረሱት መሰለኝ የዛኛዉን አለም
💐🍁💐🍁💐🍁💐🍁💐🍁💐🍁
ማን ነዉ የሚነካዉ ያን ጥቁር ካባየን
ማን ነዉ የሚቀማኝ የኔን ነፃነቴን
በኒቃብ በጅልባብ ማንንም አልሰማ
መቶ ቢለፈልፍ የሚንም ጠማማ
ቤተሰብ ጎረቤት ቢሉኝ ድንኳን ለባሽ
ዉበትሽን አሳይ ቆንጆ ነሽ አትልበሽ
ትዳር ከየት ይምጣ እንዲህ ተሸፍነሽ
ስራስ ከየት ይገኝ በጥቁር ተሸፍነሽ ልክ ሰይጣን መስለሽ
እስኪ ገለጥ አርጊዉ አይንሽ እንኳ ይታይ
የተጠቀለለ እሬሳ አትምሰይ
🌹💫🌹💫🌹💫🌹💫🌹💫
ኒቃቡን አዉልቂዉ ጅልባብ ብቻ ልበሽ
እስከመቼ ድረስ እንዲህ ተሸፍነሽ
ያኔ ትደርሻለሽ ከትዳር ቡሀላ
ባልሽ ይሸፍንሽ እንዳያይሽ ሌላ
አሁን ግን ተገለጭ ፈታ በይ እባክሽ
ባለ መኪናዉም መቶ እንዲጠይቅሽ
ሀብታሙም ሰዉየ እንድሆን ከጎንሽ
ተይ እህቴዋ ለአንቺ አስበን ነዉ
አዉልቂ ይቅርብሽ ብለን የምንለዉ
ስሬ እንዳታጪ ነዉ ባሉም እንዳይጠፋ
ብለዉ ይነግሩኛል አላህን ላስከፋ
🌷🥀🌷🥀🌷🥀🌷🥀🌷🥀
እኔስ ይገርሙኛል አላዋቂ ሰወች
እረ ይደንቁኛል እነ አዉቆ ጠፎች
የአሄራን ቅጣት ዛሬ ላይ ዘንጊወች
እኔስ ልንገራችሁ እሸፈናለሁኝ በጥቁር ልብሶቼ
በአላህ ትዕዛዝ በደንብ ተደስቼ
አቦ ተዉኝ በቃ ልሸፋፈንበት
በጥቁር ልብሶቼ ላጊጥ ልዋብበት
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
✍️كتبته
ام ريان بنت حسن (ام سكينه)
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ማሳሰቢያ ፦ስህተቴን ስታዩ አደራ ንገሩኝ
https://t.me/+Bcwn6tbrUn45ZmNk
ማን ነዉ የሚነካዉ ያን ጥቁር ካባየን
አላህ በቁርአኑ ቀድሞ ያዘዘዉን
የረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ሚስቶች የተዋቡበትን
እነዚያ ሰሀቦች የተገበሩትን
ማን ነዉ የሚነካዉ !!
ከኔ የሚያወልቀዉ !!
🌷💫🌷💫🌷💫🌷💫🌷💫🌷💫
አላወቁም እንዴ ዉበቴ መሆኑን
የፊትና በር መዝጊያ ሰበብ መሆኑን
ከቆሻሻ ዝንቦች እኔደሚጠብቀኝ
ልቡ ከታመመ እንደሚከልለኝ
አልተረዱም መሰል የኒቃብን ጥቅም
ረሱት መሰለኝ የዛኛዉን አለም
💐🍁💐🍁💐🍁💐🍁💐🍁💐🍁
ማን ነዉ የሚነካዉ ያን ጥቁር ካባየን
ማን ነዉ የሚቀማኝ የኔን ነፃነቴን
በኒቃብ በጅልባብ ማንንም አልሰማ
መቶ ቢለፈልፍ የሚንም ጠማማ
ቤተሰብ ጎረቤት ቢሉኝ ድንኳን ለባሽ
ዉበትሽን አሳይ ቆንጆ ነሽ አትልበሽ
ትዳር ከየት ይምጣ እንዲህ ተሸፍነሽ
ስራስ ከየት ይገኝ በጥቁር ተሸፍነሽ ልክ ሰይጣን መስለሽ
እስኪ ገለጥ አርጊዉ አይንሽ እንኳ ይታይ
የተጠቀለለ እሬሳ አትምሰይ
🌹💫🌹💫🌹💫🌹💫🌹💫
ኒቃቡን አዉልቂዉ ጅልባብ ብቻ ልበሽ
እስከመቼ ድረስ እንዲህ ተሸፍነሽ
ያኔ ትደርሻለሽ ከትዳር ቡሀላ
ባልሽ ይሸፍንሽ እንዳያይሽ ሌላ
አሁን ግን ተገለጭ ፈታ በይ እባክሽ
ባለ መኪናዉም መቶ እንዲጠይቅሽ
ሀብታሙም ሰዉየ እንድሆን ከጎንሽ
ተይ እህቴዋ ለአንቺ አስበን ነዉ
አዉልቂ ይቅርብሽ ብለን የምንለዉ
ስሬ እንዳታጪ ነዉ ባሉም እንዳይጠፋ
ብለዉ ይነግሩኛል አላህን ላስከፋ
🌷🥀🌷🥀🌷🥀🌷🥀🌷🥀
እኔስ ይገርሙኛል አላዋቂ ሰወች
እረ ይደንቁኛል እነ አዉቆ ጠፎች
የአሄራን ቅጣት ዛሬ ላይ ዘንጊወች
እኔስ ልንገራችሁ እሸፈናለሁኝ በጥቁር ልብሶቼ
በአላህ ትዕዛዝ በደንብ ተደስቼ
አቦ ተዉኝ በቃ ልሸፋፈንበት
በጥቁር ልብሶቼ ላጊጥ ልዋብበት
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
✍️كتبته
ام ريان بنت حسن (ام سكينه)
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ማሳሰቢያ ፦ስህተቴን ስታዩ አደራ ንገሩኝ
https://t.me/+Bcwn6tbrUn45ZmNk