እንዲህም ማለቱ በእግረ ነፍስ ነው እንጂ በእግረ ሥጋስ አታስቆምም፡፡ እንዲህማ ከሆነ ምን አድርጋ ትሻገረዋለች ቢሉ በዚህ ዓለም ያሉ አዕዋፍ ዳሩን ገደሉን ባሕሩን እሳቱን ላይ ላዩን በክንፍ እየበረሩ ተሻግረው እንዲሔዱ የእርሷም ሃይማኖቷና ግብሯ ክንፍ ሆኗት መላእክተ ብርሃን ላይ ላዩን ይዘዋት ይሻገራሉ፡፡ እርሷም ከመካከል ስትደርስ አቈልቁላ አይታ መላእክተ ብርሃንን ‹‹…ይህ እሳቱ፣ ባሕሩ፣ ገደሉ፣ ዱሩ ምንድነው?›› ብላ ትጠይቃቸዋለች፡፡ መላእክተ ብርሃንም ‹‹አንቺ ምግባር ብትሠሪ፣ ሃይማኖት ብትማሪ፣ ሰንበትን ብታከብሪ በዚህ መጣሽ እንጂ ምግባር ያልሠሩ፣ ሃይማኖት ያልተማሩ ዘመዶችሽስ በዚያው አረው ከስለው እንደ ጅማት ተኮማትረው መከራ አይተው ይሻገሩታል›› ይሏታል፡፡ እርሷም በዚህ ጊዜ ‹‹…ወየው! ወየው! በምድራዊው ዓለም ላሉ ሰዎች እንዲህ ያለ ብርቱ መከራ እንዳለባቸው ማን በነገራቸው!?...›› ብላ አዝና ተክዛ አልቅሳ ትሔዳለች፡፡
(የክብር ባለቤት ጌታችን ለድንግል እናቱ ለእመቤታችን በሰኔ 21 ቀን በጎልጎታ ስትጸልይ ሳለ ከገባላት ቃልኪዳን ውስጥ አንዱ ‹‹…በቃልኪዳንሽ የታመነውን ይህችን ጸሎት የያዘውን ሰው በደረቴ አቅፌ ባሕረ እሳትን አሻግረዋለሁ፣ ወደ መንበረ መንግሥቴም አቀርበዋለሁ›› የሚል መሆኑን ያስታውሷል፡፡) ወደ ቀደመው ነገር እንመለስና ያቺም ነፍስ አዝና ተክዛ አልቅሳ ስትሔድ ዛሬ በዚህ ዓለም ያለች ሙሽራ አባት እናቷ መልስ ጠርተዋት በደስታ እንድትሔድ እርሷም ከፈጣሪዋ ለመገናኘት ስትሔድ በፍሥሐ በደስታ ትሔዳለች፡፡ ዳግመኛ ዛሬ በዚህ ዓለም ያሉ እናት አባት ለልጃቸው የሚበላውን የሚጠጣውን አሰናድተው እንዲቆዩ ለእርሷም ፈጣሪዋ የመኖሪያዋን ቦታ መንፈሳዊ ምግብና መጠጥ አዘጋጅቶ በፍሥሐ በደስታ ይቆያታል፡፡ እርሷም ገሃነመ እሳትን አልፋ በመውጣቷ ደስ እያላት ከጌታ ዘንድ ስትደርስ ሰግዳ ትቆማለች፡፡ ሰግዳም ስትቆም ጌታ ይጠይቃታል፡፡ ምን ብሎ ይጠይቃታል? ቢሉ የወንድ ነፍስ እንደሆነች ‹‹አንቺ ነፍስ እንጨት መቁረጥ፣ መፍለጥ፣ ቤት ማነጽ፣ ፈረስ መጋለብ ውኃ ዋና፣ ሰንጠረዥ፣ እርሻ፣ ቁፋሮ፣ በገና፣ ጸናጽል፣ ከበሮ፣ ጽሕፈት፣ ድጉሰት ታውቂያለሽን?›› ብሎ አይጠይቃትም፡፡ የሴትም ነፍስ ብትሆን ‹‹አንቺ ነፍስ አልሞ መደቆስ፣ አለስልሶ መፍተል፣ ወጥ መሥራት፣ እንጀራ መጋገር፣ ጠጅና ጠላ መጥመቅ ታውቂያለሽን?›› ብሎ አይጠይቃትም፡፡
እንግዲያስ ምን ብሎ ይጠይቃታል? ቢሉ ‹‹አንቺ ነፍስ በማን ታምኛለሽ? አንድነቴን ሦስትነቴን፣ ምልዐት ስፋቴን፣ ርቀቴን፣ ከሰማየ ሰማያት መውረዴን፣ ከድንግል ማርያም መወለዴን፣ ወልደ አብ በመለኮት፣ ወልደ ማርያም በትስብእት በተዋሕዶ የከበርኩ መሆኔን፣ መገፈፍ መገረፌን፣ መሰቀል መሞቴን፣ መነሣት ማረጌን ታውቂያለችን? ብሎ ይጠይቃታል፡፡ እርሷም የተማረች ናትና ቃሏም እውነተኛ ነውና ‹‹አዎን አምላኬ ሆይ! አንድነትህን ሦስትነትህን፣ ምልዓት ስፋትህን፣ ርቀትህን፣ መውረድ መወለድህን፣ ወልደ አብ ወልደ ማርያም በተዋሕዶ የከበርህ መሆንህን፣ መገፈፍ መገረፍህን፣ መሰቀል መሞትህን፣ መነሣት ማረግህን ዐውቃለሁ›› ብላ ትመልሳለች፡፡ ከዚያም የጌታ በእውነተኛ ቃሉ መላእክተ ብርሃንን ጠርቶ ‹‹ይህቺ ነፍስ ምእመን (ታማኝ) ናትና መንግሥተ ሰማያት እንጂ ገሃነመ እሳት አይገባትም፣ ከሥጋዋ ጋር አዋሕጄ ፍጹም መንግሥተ ሰማያትን እስካወርሳት ድረስ 4 ቀን ገሃነመ እሳትን፣ 3 ቀን መንግሥተ ሰማያትን አዙራችሁ አሳይታችሁ ከጻድቃን ጋራ በገነት አኑሯት›› ብሎ ያዛል፡፡
ከዚህ በኋላ መላእክተ ብርሃን ይዘዋት ወጥተው መንግሥተ ሰማያትን፣ የባለ ሕጎች አገር የደናግልን፣ የጻድቃንን አገር 3 ቀን አዙረው አሳይተው ሽታዋን ጣዕሟን በልቡናዋ አሥርፀው፤ ‹‹አንቺ ነፍስ ሃይማኖት ስላለሽ በጎ ምግባር ስለሠራሽ በእንዲህ ያለ በደስታ ቦታ ያኖርሻል›› ብለው ወደ ገሃነመ እሳት ይዘዋት ይወርዳሉ፡፡ ከገሃነመ እሳት ውስጥ ያለውን የእሳቱን አክሊል፣ የእሳቱን ዘውድ፣ የእሳቱን ዘንዶ፣ የእሳቱን እባብ፣ የእሳቱን አንበሳ፣ የእሳቱን መጋዝ፣ የእሳቱን ሰይፍ፣ የእሳቱን ጦር፣ የእሳቱን ዝናር፣ የእሳቱን ጫማ ይህንንና የመሳሰለውን ሁሉ ካፋቱን ክርፋቱን፣ ግማቱን ሁሉ 4 ቀን አዙረው አሳይተው ‹‹አንቺ ነፍስ ሃይማኖት ባይኖርሽ በጎ ምግባር ባትሠሪ ኖሮ በእንዲህ ያለ መከራ ያኖርሽ ነበር፡፡ ነገር ግን ሃይማኖት ስላለሽ በጎ ምግባር ስለሠራሽ ጌታ በቸርነቱ ከእንዲህ ያለ መከራ አውጥቶ በደስታ ያኖርሻል›› ብለው ወስደው ከጻድቃን ጋር ያኖሯታል፡፡ ሀገረ ሕያዋንን፣ ሀገረ ሰማዕታትን፣ ሀገረ ደናግልን፣ ሀገረ መነኰሳትን፣ ሀገረ ሕጋውያንን እያዞሩ እያሳዩ ‹‹አንቺ ነፍስ ሃይማኖት ብትማሪ ምግባር ብትሠሪ ጌታ በቸርነቱ ከዲያቢሎስ መገዛት ከእንዲህ ያለ መከራ አውጥቶ ከእንዲህ ያለ ተድላ ደስታ አበቃሽ›› ብለው ወስደው ከጻድቃን ጋራ በገነት ያኖሯታል፡፡ ኋላም ከገሃነመ እሳት መውጣቷን፣ መንግሥተ ሰማያት መግባቷን እያሰበች እስከጊዜ ምጽዓት ድረስ በገነት በደስታ ትኖራለች፡፡
ገነት ያለችው በወዴየት ነው? ቢሉ በፀሐይ መውጫ ወይም በስተምሥራቅ በኩል ናት፡፡ በ4ቱ ማዕዛኗ ዐራት ተራሮች አሏት፤ በ4ቱ ተራሮች መካከል 4 አፍላጋት ገብተው ያጠጧታል፡፡
ደገኛይቱ ነፍስ የገሃነመ እሳትን ሥቃይ እያሰበች ከገሃነመ እሳት መውጣቷንና መንግሥተ ሰማያት መግባቷን እያሰበች ፈጣሪዋን እያመሰገነች እስከ ጊዜ ምጽዓት ድረስ በፍሥሐ በደስታ ትኖራለች፡፡ ከምጽአትም በኋላ ከሥጋዋ ጋራ ተዋሕዳ ተድላ ደስታ ካለበት ፍጹም መንግሥተ ሰማያት ትገባለች፡፡ መንግሥተ ሰማያት ያለችው በወዴት ነው? ቢሉ ከኢዮር በላይ ከሰማይ ውዱድ በታች በመካከላቸው ናት፡፡ ሃይማኖት ከምግባር አስተባብሮ የያዘ የመልካም ሰው ነፍስ በዚህ ሁኔታ ዘላለማዊ የክብር ዋጋዋን ተቀብላ ትኖራለች፡፡ ከገቡ መውጣት ካገኙ ማጣት ከሌለባት ከዚህች ፍጹም ተድላ ደስታ ካለባት ርስት መንግሥተ ሰማያት ለመግባት የመድኃኔዓለም ቸርነቱ የድንግል እናቱ የቅዱሳኑ የሰማዕታቱ ሁሉ ምልጃና ጸሎት ይርዳን! አሜን!!!
ሃይማኖት ያልተማረ ከምግባር ጎደለ የኃጥእ ሰው ነፍስስ እንዴት ትሆናለች? ቢሉ የኃጥእ ሰው ነፍስ ገና ከሥጋዋ ሳትለይ በጻዕረ ሞቷ ሳለች መላእክተ ጽልመት በግራ መላእክተ ብርሃን በቀኝ ሆነው ይመጡባታል፡፡ መጥተውም ባዩአት ጊዜ በጨለማ ቁርበት ተጠቅልላ በእሳት ሰንሰለት ታስራ የእሳት አክሊል ደፍታ የእሳት ዝናር ታጥቃ፣ የእሳት ጫማ ተጫምታ፣ ከቁራ 7 እጅ ጠቁራ፣ ከፍታ ከርፍታ ዲያብሎስን መስላ ትታያቸዋለች፡፡ ከዚህ በኋላ መላእክተ ብርሃንን ትገማቸዋለች፣ ትከረፋቸዋለች፤ እነርሱም ይፀየፏታል፡፡ ከእርሷ ርቀው ፈቀቅ ብለው ቆመው ይጠይቋታል፡፡ ምን ብለው ይጠይቋታል? ቢሉ ‹‹አንቺ ነፍስ በማን ታመልኪያለሽ? የሥላሴን አንድነት ሦስትነት፣ ምልዐት፣ ስፋት፣ ርቀት፣ የጌታን ከሰማይ መውረዱን፣ መወለዱን፣ ወልደ አብ ወልደ ማርያም መሆኑን፣ መገፈፍ፣ መገረፉን፣ መሰቀል፣ መሞቱን፣ መቀበሩን፣ መነሣቱን ማረጉን፣ ዳግም ለፍርድ መምጣቱን ታምኛለሽን? የእግዚአብሔርን እንግዳ ተቀብለሻል? ሰንበትን አክብረሻልን?›› ብለው ይጠይቋታል፡፡ እርሷም ያልተማረች ናትና ‹‹እኔስ የሥላሴን አንድነት ሦስትነት፣ ምልዐት፣ ስፋት፣ ርቀት፣ የጌታን ከሰማይ መውረዱን፣ መወለዱን፣ ወልደ አብ ወልደ ማርያም መሆኑን፣ መገፈፍ፣ መገረፉን፣ መሰቀል፣ መሞቱን፣ መቀበሩን፣ መነሣቱን ማረጉን፣ ዳግም ለፍርድ መምጣቱን አላውቅም፡፡ በምንሰ አውቃለሁ? መምህራንን አልጠየቅሁ፣ መጻሕፍትን አላነበብሁ፣ ቤተ