"በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።
📣 እንኳን
#ለዐቢይ_ጾም_ሰባተኛ_ሳምንት_ለኒቆዲሞስ #እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰ።
#የዚህ_ሳምንት_የኒቆዲሞስ_መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፭ "ሖረ ኀቤሁ #ዘስሙ_ኒቆዲሞስ ወይቤሎ #ለኢየሱስ_ረቢ_ንህነ_ነአምን ብከ ከመ እምኀበ #አብ_መጻእከ መራሔ ሕይወትነ ወሠራየ ኀጢአትነ ከመ #እምኀበ_አብ_መጻእከ ከመ ትኩን መምህረ ዕጓለ አንበሳ ሰከብከ ወኖምከ አንሥአኒ በትንሣኤከ። ትርጉም፦ አስቀድሞ ሌሊት ወደ እርሱ ይሄድ የነበረ #ስሙ_ኒቆዲሞስ የሚባል መምህር ሆይ #ከአብ_አካል_ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ ተወልደህ ወደዚህ ዓለም እንደ መጣህ ፈጽሞ እናምንብሃለን፤ የሕይወታችን መሪ ኀጢአታችንን ይቅር የምትል ነህ አለው"። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በጾመ_ድጓው_ላይ።
#ቅዱስ_ኒቆዲሞስ፦ ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የነበረው ሰው ነው፡፡ የአይሁድ አለቆች #አምላካችንኢየሱስ_ክርስቶስን "ምልክት አሳየን" እያሉ ይፈታተኑት ነበር፡፡ #ጌታችን ስለ ሞቱና ትንሣኤው በምሳሌ እያስረዳ ቢያስተምራቸውም እነርሱ ግን አልገባቸውም ነበር፡፡ ከዚህም አልፎ #ጌታችን በተአምራቱ የታመሙትን ሲፈውስ "ሕጋችን ተሻረ" ይሉ ነበር፡፡ በዚህ ዅሉ ተአምራትና ትምህርት የአይሁድ አለቆች #ክርስቶስን ለመክሰስ በሚፈልጉበት ወቅት ከአይሁድ አለቆች አንዱ ኒቆዲሞስ በቀን እንዳያደርገው አይሁድን ቢፈራ፣ አንድም ጊዜ ባያደርሰው እንደ ባልንጀሮቹ #ክርስቶስን ሳይቃወም በሌሊት ወደ #ጌታችን ዘንድ እየሔደ ወንጌልን ይማር ነበር፡፡
#አምላካችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በነፍስ የታመሙትን በቃሉ፣ በሥጋ የታመሙትን በተአምራቱ ሲፈውስ ኒቆዲሞስ ሰምቶ፣ ተመልክቶ በመምህርነቱ ሳይኮራ አለቅነቱን መመኪያ ሳያደርግ በልቦናው የተሳለውን እውነትን የመፈለግ ስሜት አንግቦ ከ #ጌታው፣ ከመምህሩ ከ #ክርስቶስ ዘንድ በሌሊት ይገሰግስ ነበር (ዮሐ. ፫፥፩)፡፡ ምስክርነቱንም እንዲህ ሲል መስጠት ጀመረ፤ "መምህር ልታስተምር ከ #እግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን፡፡ #እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከኾነ በቀር አንተ የምታደርገውን ተአምራት ሊያደርግ የሚችል የለምና" (ዮሐ. ፱፥፳፬፤ ሐዋ. ፲፥፴፰)፡፡
ይህን ምስክርነቱን በሚሰጥበት ጊዜም ጎዶሎን የሚሞላ፤ አላዋቂነት በአዋቂነት የሚለውጥ፤ ከምድራዊ ዕውቀት ወደ ሰማያዊው ምሥጢር የሚያሸጋግር አምላክ "ዳግመኛ ያልተወለደ የ #እግዚአብሔርን መንግሥት ለማየት አይችልም"። በማለት የአይሁድ መምህር ለኾነው ኒቆዲሞስ ቢያስተምረው ምሥጢሩ አልተገለጠለትም ነበርና "ሰው ከሸመገለ በኋላ ዳግመኛ መወለድ እንደምን ይቻላል? ዳግመኛ ይወለድ ዘንድወደ እናቱ ማኅፀን ተመልሶ መግባት ይችላልን?" በማለት ጥያቄ አቅርቧል (ዮሐ. ፫፥፮፤ ፩ኛጴጥ. ፩፥፳፫)፡፡ "እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዳግመኛ ከውኃና ከ #መንፈስ_ቅዱስ ያልተወለደ ወደ #እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስነውና"። (ኤፌ. ፭፥፳፮) በማለት #አምላካችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ለኒቆዲሞስ ቢያስረዳውም ምሥጢሩ ከአቅሙ በላይ ስለ ኾነበት እንደምን ይቻላል? በማለት ጠይቋል፡፡
አበ ብዙኃን አብርሃም ከአምላኩ ሞገስን አግኝቶ የሰዶምና ገሞራ ጥፋት እንዳይደርስ ለመማለድ ከ #እግዚአብሔር ጋር ሲነጋገር እንደ ነበረ፤ ኒቆዲሞስም አላዋቂነቱን አምኖ ያልገባውን ምሥጢር ከአምላኩ በጠየቀ ጊዜ #ኢየሱስ_ክርስቶስም፡- "አንተ የእስራኤል መምህራቸው ኾነህ ሳለ ይህን ነገር አታውቅምን? በምድር ያለውን ስንነግራችሁ ካላመናችሁ በሰማይ ያለውን ብንነግራችሁ እንደምን ታምናላችሁ? ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይየወጣ የለም … ሙሴ በምድረ በዳ እባቡን እንደ ሰቀለ የሰውልጅ እንዲሁ ይሰቀላል፡፡ ያመነበት ዅሉ ለዘለዓለም ሕያው ኾኖ እንዲኖር እንጂ እንዲጠፋ አይደለም ..." እያለ ሰው በመብል ምክንያት የአምላኩን ትእዛዝ አፍርሶ ከ #እግዚአብሔር ቢለይም የሰው ልጅ ያጣውን ልጅነት ለመመለስ፣ ስመ ክርስትናን፣ ሀብተ ወልድን ለመስጠት #ጌታችን መምጣቱን አስረዳው (ዮሐ. ፫፥፲፬)፡፡ ይህን የ #ክርስቶስን የማዳን ሥራና በሥጋ መገለጥም "ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ አመከርከኒ ወኢተረክበ ዐመፃ በላዕሌየ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመሕያው፤ ልቤን ፈተንኸው፡፡ በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ፈተንከኝም፡፡ ምንም አላገኘህብኝም፡፡ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው" (መዝ. ፲፮፥፫) በማለት ቅዱስ ዳዊት ከኒቆዲሞስ ሕይወት ጋር በማዛመድ አመሥጥሮታል፡፡
በሌሊት ከአምላኩ ተምሮ ምሥጢሩ የተገለጸለት ኒቆዲሞስ ቀድሞ በአደባባይ ሔዶ መማርን ይፈራ እንዳልነበረ ምሥጢሩ ሲገለጽለት ግን አይሁድ #ጌታችንን በሰቀሉት ዕለት ፍርኃት ርቆለት ከአርማትያሱ ዮሴፍ ጋር ቅዱስ ሥጋውን ገንዞ ለመቅበር በቃ፡፡ "ወአልቦ ፍርኃት ውስተ ተፋቅሮትነ፤ ፍጹም ፍቅር ፍርኃትን አውጥቶ ይጥላል" ተብሎ እንደ ተጻፈ (ማቴ. ፳፯፥፶፰፤ ፩ኛዮሐ. ፬፥፲፰)፡፡ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
#ድምፀ_ተዋህዶ
✨✨✨✨✨✨
✝️#
ድምፀ_ተዋህዶ✝️
✨✨✨✨✨✨