ዕውቀት እና የዕውቀት ባለቤቶች ደረጃ
ክፍል -7
የእውቀት ባለቤቶች ሊዋቡባቸው የሚገቡ ስነ-ምግባራትና አዳቦች
ሸይኽ ዓብዱረህማን ብን ናሲር አስ'ሲዕድይ - (ረሂመሁሏህ) – “ፈዋኢድ ፊ አዳቢል ሙዓሊሚ ወልሙተዓሊሚን” በተባለው ኪታባቸው የሚከተለውን ተናግረዋል ፡-
((በሒዎት ስትኖር በኢኮኖሚም ይሁን በሌላ በትንሹ መብቃቃት አስፈላጊ መሆኑን እወቅ ፤ እውቀት የእድሜ ልክ ወይም የአብዛኛው እድሜያችን ስራ ነው ፤ በመሆኑም እውቀትን የዱንያ ስራ ከተጋፋው ጉድለት ይከሰታል ፤ ባለው ተብቃቅቶ መኖር የያዘውን ትምህርት ለመቀጠል ፤ በዱንያ ከመጠመድ ለመዳን ትልቁ ምክንያት ነው፡፡
“እውቀት ሙሉ ጊዜህን ከሰጠኸው ከፊሉን ይሰጥሃል፤ ከፊሉን ከሰጠኸው ደግሞ ምንም አይሰጥህም፡፡” ይላሉ ቀደምት ኡለሞቻችን፡፡
የእውቀት ባለቤት ፡ በቻለው ያህል ጠቃሚ እውቀትን ማሰራጨት አለበት፡፡ አንዲትን ኢልም ለሌሎች ያሰራጨ ይህ ከእውቀቱ በረካ ነው፤ ምክንያቱም የእውቀት ፍሬው ሰዎች በአንተ ኢልም መጠቀማቸው ነው፤ እውቀቱን የነፈገ እርሱ ሲሞት እውቀቱ አብሮት ይሞታል፤ አንዳንዴ እርሱ በሂዎት እያለ ሊረሳው ይችላል፤ እውቀቱን ያሰራጨ ሰው ግን ለእርሱ ሁለተኛ ሒዎቱ ነው ፤ ያወቀውንም መጠበቅ ነው፡፡
ረሱል - ዓለይሂሶላት ወሰላም - እውቀትን በሚደብቁ ሰዎች ዙሪያ የሚከተለውን ተናግረዋል ፡-
"من كتم علما ألجمه الله يوم القيامة بلجام من نار يوم القيامة"
“እውቀትን የደበቀ የቂያማ ቀን በእሳት ልጓም አላህ ይለጉመዋል፡፡”
አሊሞችም ይሁኑ እውቀት ፈላጊዎች ፡ ቃላቶቻቸውን አንድ ማድረግ፤ ልቦቻቸውን ማስተሳሰር ፤ የተንኮል፣ የምቀኝነት፣ የጠላትነት እና የጥላቻ በሮችን ጥርቅም አድርገው መዝጋት በእነርሱ ላይ ግዴታና አንገብጋቢ ነው፡፡ ይህን ስነ- ምግባር የአይኖቻቸው ማረፊያ ሊያደርጉት ይገባል፡፡ ይህን ስነምግባር ለመላበስ ጥረት ሊያደርጉ ይገባል፡፡ ስለዚህ በርካታ ልምድ ኖሯቸው በዚህ ጉዳይ ጊዜያቸውን ሰውተው ጥቅም እየሰጡ ያሉ የእውቀት ባለቤቶች ይህን ጉዳይ በመካከላቸው ተፈቃቅረው ሊያረጋግጡት ይገባል፡፡ ጎጅ የሆኑና ከዚህ ታላቅ አላማ የሚያግዱ ነገሮችን እንደቀላል ተመልክተው ቸል ሊሉት አይገባም ፤ ከፊሉ ከፊሉን ሊወድ ፤ ከፊሉ ከከፊሉ ላይ ሊከላከል ይገባል ፤ ስህተቶች ከተመለከቱ ለመምከር ጥረት ያድርጉ፤
ትክክለኛ አሊሞች በአቂዳቸውና አመለካከታቸው ሰላማዊነት፤ ቁርኣንና ሱናን በመከተላቸው ፤ ሰውን ወደመልካምና ወደቀጥተኛው ጎዳና በመጥራት ፤ ለሱና ተቃራኒ አካላትን በማስጠንቀቅ ይታወቃሉ፡፡
ባብዛኛው የጭቅጭቅና ጥላቻ ምንጩ ፡ ስሜትን መከተል፣ ዘረኝነት፣ ምቀኝነት፣ መታወቅንና የይስሙልኝን መፈለግ ናቸው፡፡
ከማህበረሰቡም ይሁን ፣ ከሌላው የኢልም ጠላት ከሆኑ አካላት በኡለሞች መካከል ገብተው ንግግራቸውን እንዳይከፋፍሉ ጉዳዩን ቸል ብለው ሊመለከቱት አይገባም፡፡ ይህን ታላቅ አላማ ማረጋገጥ በርካታና ተቆጥሮ የማይዘለቅ ጥቅሞችን ያስገኛል፡፡ ሌላ እንኳ ጥቅም ባይኖር ይህ ጉዳይ ባለቤቶቹ ሊቆሙበትና ሊይዙት ግድ የሆነ ፤ በማንኛውም መስመር ረሱል - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - የገፋፉበት የዲናችን አካል ነው፡፡
በአሁኑ ሰዓት እየገቡ ያሉ የጠማማ አመለካከት ባለቤቶች ኢልማንይ፣ ሹዒይና ደህርይ በእውቀት ባለቤቶች መካከል ጠላትነትን ለማስገባት ፤ የእውቀት ፈላጊዎችን በመከፋፈል ፤ እርስ በርስ እንዲተራረዱና የተለያዩ ጭፍሮች እንዲሆኑ እቅዱ አላቸው፡፡
የእውቀት ባለቤቶች መንገዳቸው አንድ ከሆነ ከፊሉ ከከፊሉ ለመማር አመች ይሆናል ፤ አንዱ አንዱን ያስተምራል ፤ ነገር ግን እያንዳንዱ ጭፍራ ከትክክለኛው መንገድ የተጣመመ ከሆነ በኢልም የሚገኘው ጥቅም ይቋረጣል ፤ በኢልም ቦታ ተቃራኒዋ ይሰፍራል፤ ጥላቻ ዘረኝነት ይከሰታል፤ አንዱ የአንዱን ነውር መፈተሽ ይጀምራል፤ አንዱ አንዱን ለማንቋሸሽ ስህተትን ይፈለፍላል፤ ለእኩይ አላማው መዳረሻም ያደርጋል ፤ ይህ ሁሉ ለዲን ለአቅል እንዲሁም ሰለፉነ ሷሊህ የነበሩበትንም የሚቃረን ነው፡፡ ጃሂል ይህን ተግባር ዲን ነው ብሎ ሊጠረጥር ይችላል ፤ ነገር ግን አላህ መልካሙን የገጠማቸው ሰዎች ግን የሚከተሉትን ነጥቦች ተፈጻሚ በማድረግ ላይ ይጠመዳሉ፡--
1-በተውሂድ ዙሪያ ለአላህ ብለው ይመካከራሉ፡ ከአላህ ዘንድ የሚገኘውን አጅር ታሳቢ በማድረግ ግልጽም ይሁን ስውር አምልኮታቸው ኢኽላስ እንዲኖረው የአላህን ባሮች ይመክራሉ፤
2-ስለ አላህ ኪታብ ይመካከራሉ፡ ሰዎች በቁርኣን ውስጥ ባለው ሁሉ እንዲያምኑ ፤ ቁርዓንን እንዲሁም ከእርሱ ጋር ተያያዥ የሆኑ ሸሪዓዊ እውቀቶችን ወደመማርና ወደማስተማር ፊቶቻቸውን እንዲያዞሩ ይመክራሉ፤
3-ስለረሱል - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - ይመካከራሉ፡ ረሱል በመጡበት መሰረታዊም ይሁን ቅርንጫፋዊ የዲን ጉዳዮች ሁሉ ሰዎች እንዲያምኑ ፤ ከአላህ ፍቅር በኋላ ፍቅራቸውን ለረሱል እንዲለግሱ ፤ ግልጽም ይሁን ስውር በሆኑ ሸሪዓዊ ጉዳዮች ሁሉ ረሱልን ብቻ መከተል እንዳለባቸው ይመክራሉ፤
4-ስለሙስሊም መሪዎችም ይመካከራሉ፡ ለመሪዎች መልካምን እንዲወዱ ፤ በንግግርም ይሁን በተግባር እነርሱን ለማገዝ እንዲንቀሳቀሱ ፤ ህዝቡ በእነርሱ ዙሪያ እንዲሰባሰብና አንድ እንዲሆን፤ እነርሱን ከመቃረን ርቆ በመታዘዝ ላይ መሰባሰብን እንዲወድ ይመክራሉ፤
5-ስለ አጠቃላይ ህዝቡም ይመካከራሉ፡ ለነፍሱ የሚወደውን ለእነርሱም እንዲወድ፤ ለነፍሱ የሚጠላውን ለእነርሱም እንዲጠላ፤ በሚችለው ያህል ጥቅም ወደእነርሱ እንዲደርስ ፤ ውጫዊ አካሉ የውስጥ ልቦናውን ፤ ንግግሩ ተግባሩን እንዲያረጋግጥ ፤ ወደዚህ ትልቅ መሰረትና ቀጥተኛ መንገድ ጥሪ ያደርጋሉ፤ ))
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصيرة