እውቀትና የእውቀት ባለቤቶች ደረጃ
ክፍል - 13
ለዲናዊ እውቀት ክብር መስጠት
ሶሀቦች ከነብዩ ﷺ መካከል ተቀምጠው እውቀትን ይቀስሙ ነበር፡፡ ሶሃቦች ለነብዩ ﷺ እውቀት ክብር ይሰጡ ነበር፡፡ ከነብዩ ﷺ ሐዲስ ሲያዳምጡ - ከነበራቸው አደብ የተነሳ - ልክ ከቅንጭላታቸው ላይ ወፍ የተቀመጠ ይመሰሉ ነበር።
አቡ ሰዒድ አልኹድርይ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል ፡
“የአላህ መልክተኛ ከመድረክ ላይ ቆሙ ፣ ከዚያም የሚከተለውን ተናገሩ ፡
(('እኔ ፣ በእናንተ ላይ የሚከፈተውን የምድር በረካዎች እፈራላችኋለሁ' በማለት ተናገሩ ፤ ከዚያም የዱንያን ውበቶች አወሱ ፤ ከሁለቱ በአንዱ ጀመሩ ፣ከዚያም በሌላው ቀጠሉ፡፡
አንድ ሰው ቆመ ፣ “የአላህ መልክተኛ ሆይ! መልካሙ በመጥፎው (ትክ) ይመጣል?” አላቸው፡፡
ነብዩም ዝም አሉ፡፡ “ወህይ እየወረደላቸው ይሆናል” አልን፡፡ ሁሉም ሰው ልክ ወፍ ከቅንጭላቱ እንዳረፈበት ዝም አለ፡፡))
(أخرجه البخاري 1\48-49 – فتح)
ሶሃቦች ለረሱል ﷺ የነበራቸው ክብር በአይናቸው ሞልተው አይመለከቷቸውም ነበር፡፡ አብረዋቸው ከሆኑም አንገታቸውን ሰበር አድርገው ይቀመጣሉ፡፡ አንዳንድ ሶሀቦች "የአላህ መልክተኛን ገጽታ ግለጹልን ብንባል መግለጽ አንችልም ነበር" ይላሉ፡፡
አብዱረህማን ብን ሹማሳ የሚከተለውን ተናገረ ፡
((አምር ብን አልዓስን ጣረ ሞት ላይ እያለ አገኘነው፡፡ ረዘም ላለ ጊዜ አለቀሰ፡፡ ፊቱን ወደግድግዳ አዞረው፡፡ ልጁም የሚከተለውን አለው :-
"በዚህ በዚህ .. የአላህ መልክተኛ አላበሰሩህምን? ፤ በዚህ በዚህ .. የአላህ መልክተኛ አላበሰሩህምን?"
ከፊቱ ቀና በማለት ፡ "ከምንቆጥረው ሁሉ በላጩ 'ላኢላሃ ኢልለላህ ፣ ሙሀመድ ረሱሉላህ' የሚለውን የምስክርነት ቃል ነው፡፡ እኔ በሶስት እርከኖች ላይ አልፊያለሁ፡፡
- ከእኔ የበለጠ ከፍተኛ ጥላቻ በረሱል ላይ እንዳልነበረ አይታችኋልያለው፡፡ ሁኔታው ቢመቻችልኝ ረሱልን ﷺ በመግደል እንደኔ የሚመኝ አልነበረም፡፡ በዚህ ባህሪ ለይ ብሞት ፤ ከእሳት ሰዎች እሆን ነበር፡፡
- አላህ እስልምናን በልቤ ውስጥ ያደረገልኝ ጊዜ ወደነብዩ ﷺ መጣሁ፡፡ 'ቀኝ እጅህን ዘርጋልኝ ቃል ልግባልህ' አልኳቸው። ቀኝ እጃቸውን ዘረጉ፡፡ እኔም እጀን ዘረጋሁ። 'አምር ሆይ ምን አለህ' አሉኝ 'መስፈርት ላደርግ ነው' አልኳቸው። 'በምን ላይ ነው መስፈርት የምታደርግ?' አሉኝ።
'(አሏህ) ምህረት እንዲያደርግልኝ' አልኳቸው።
'ኢስላም ከዚህ በፊት የነበረውን እንደሚሰርዝ አላወቅህምን? ፤ ሂጅራ ከዚህ በፊት ያለውን እንደሚሰርዝ አላወቅህምን? ፤ ሀጅ ከዚህ በፊት ያለውን እንደሚሰርዝ አላወቅክምን?' አሉኝ።
አሁን ደግሞ ከረሱል ﷺ የበለጠ የምወደው ፣ በአይኔ ትልቅ ልቅና የምሰጠው ከረሱል ﷺ የበለጠ አንድም የለም ፣ እርሱ ልቅና ለመስጠቴ በአይኔ ሞልቸ ማየት አልችልም፡፡ የረሱልን ﷺ ገጽታ ግለጽልን ቢሉኝ መግለጽ አልችልም፡፡ ምክንያቱም በአይኔ ሞልቸ ማየት ስለማልችል፡፡ በዚህ ባህሪ ላይ ብሞት ከጀነት ሰዎች እሆናለሁ ብየ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
- ከዚያም በአንዳንድ ነገሮች ላይ ሹመት አገኘን የእርሱንም ሁኔታ ምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ እኔ ከሞትሁ ሚሾ እና እሳት እንዳይከተለኝ፡፡ በቀበራችሁኝ ጊዜ አፈር በትኑብኝ፡፡ ከዚያም በእናንተ ደስተኛ እሆን ዘንድ ፣ ለጌታየ መልክተኞች የምመልስላቸውንም እስከምመለከት ግመል ታርዳ የምትከፋፈልበት ጊዜ ያክል ከቀብሬ ዘንድ ቆዩ።))
(ሙስሊም ዘግቦታል ፡ (121)
ታብእዮች ለኡለሞች እና ለኢልም ባላቸው ክብር
በዚሁ አይነት ተጉዘዋል
ሙጌራ የሚከተለውን ተናግሯል ፤
"كنا نهاب إبراهيم كما يهاب الأمير" (الجامع لأخلاق الراوي وآداب السامع) 1\184-185
“ኢብራሂም (አንነኸዒይን) ልክ አሚሩን እንደምንፈራው እንፈራው ነበር”
ኡለሞች ለዲናዊ እውቀት ክብር መስጠትን በተማሪዎቻቸው ልቦና ውስጥ የማስገባት ፣ ስህተት ላይ የወደቀን አካል ወደትክክለኛው አቅጣጫ የመምራት ግዴታ አለባቸው፡፡
ሰለፎች በታላቅ ስነምግባር ላይ ነበሩ ፡
አብደሏህ ኢብን ኡመር የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፏል፡
የአሏህ መልእክተኛ ﷺ የሚከተለውን ተናገሩ :-
"مثل المؤمن كمثل شجرة خضراء لا يسقط ورقها ولا يتحات"
“የአማኝ ምሳሌው ቅጠሉ የማይረግፍና የማይበሰበስ አረንጓዴ ዛፍ ማለት ነው፡፡”
ሶሀቦችም ፡ "እርሷ (ይህች ዛፍ) እንደዚህ እንደዚህ .. አይነት ዛፍ ነች፡፡" አሉ፡፡
ኢብን ኡመር የሚከተለውን ተናገረ ፡
“የተምር ዛፍ ናት ብየ ለመናገር ፈለግሁ ፣ እኔ ግን ገና ልጅ ስለነበርሁ (ለመመለስ) አፈርሁ፡፡”
የአላህ መልክተኛ ﷺ የሚከተለውን ተናገሩ ፡
"هي النخلة"
“እርሷ የተምር ዛፍ ነች”
(ሐዲሱን ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
በይሐቅይ በዚህ ሐዲስ ላይ ተንተርሶ የሚከተለውን ማብራሪያ ሰጧል ፡
“አብደላ እድሜው ገና ልጅ ስለነበረ በመሻይኾች መካከል ስለርሷ (ስለዛፏ) ለመናገር አፈረ፡፡ ይህ የሚመሰገን ባህሪው ነው፡። አባቱ ኡመር ግን እውቀቱ ይፋ እንዲሆን በመፈለግ መልስ ቢሰጥለት ተመኝቶ ነበር፡፡ ነብዩ ﷺ ዛፏን እነዲነግሯቸው ለሶሃቦች ጥያቄ አቅርበው እያለ እነርሱ መልስ ቢሰጡ አደብ ጥሰዋል አይባልም ...”
(الفوائد البهية في تراجم الحنفية : ص 109)
አንዳንድ የእውቀት ፈላጊዎች ሸህየው ተማሪዎቹን ጥያቄ ሲጠይቃቸው ከተማሪዎች መካከል አንዱ እግሩን በሌላው እግሩ ላይ አጣምሮ በኩራት ሲሳለቅ ስትመለከት ደግሞ በሰለፎች እና በእኛ መካከል ለእውቀት እና ለእውቀት ባለቤቶች የተሰጠው ክብር ምን ያክል የተራራቀ መሆኑን ትገነዘባለህ፡፡
የለይስ ብን ሰእድን ንግግር ምን ያማረ ድንቅ ንግግር አደረገው፡፡ ወደሐዲስ ባለቤቶች አንድ ቀን ቀረበ፡፡ የሆነ (ደስ ያላለው) ነገር ተመለከተ፡፡
የሚከተለውን ተናገረ ፡
"ما هذا أنتم إلى يسير من الأدب أحوج منكم إلى كثير من العلم" الجامع لأخلاق الراوي وآداب السامع (1\405)
“ከበርካታ እውቀት ይልቅ ለእናንተ በጣም የሚያስፈልጋችሁ ትንሿ አደብ ነች።”
ክፍል አስራ ሶስትን ከመቋጨቴ በፊት አንድ ወንድሜ ያጫወተኝን አንድ አስገራሚ ታሪክ ልንገራችሁ:
ለሸይኹ ከፍተኛ ክብር የሚሰጥ አንድ ደረሳ ነበር ይባላል። ከሸኽየው ጋር በፍጹም ተለያይቶ አያውቅም - ጉዞ ሲሄዱም ሲመለሱ። የአካባቢው ፈትዋ ሰጪ እርሳቸቸው ነበሩ ይባላል። እናም አንዳንዴ ጃሂል በሚጠይቃቸው ያልሆነ ጥያቄ የተበሳጨው ይህ ደረሳ
'እነሸይኽ ከዛሬ ጀምሮ ጃሂል ለሚጠይቅዎት ጥያቄ መልሱን እኔ እሰጣለሁ። እርስዎ አሊም ሲጠይቅዎት ብቻ መልስ ይስጡ' አላቸው።
በዚህም ተስማሙ። ከዚያም ባረፉበት አንድ አካባቢ ድንገት አንድ ጃሂል የሚከተለውን ጥያቄ አቀረበ:-
'የሸይጧን ጥርስ ስንት ነው እነ ሸይኽ' አላቸው። ሸኽየውም በቀረበው ጥያቄ ተጨናነቁ። ላበት ላበት አላቸው። ደረስየ 'አይጨናነቁ፣ ለጃሂል ጥያቄ እኔው መልስ እሰጣለሁ አላልኩዎትም?' አላቸው። 'ኧረ ልክ ነህ ፣ ብየሀለሁ' አሉት። ደረስየም