እውቀትና የእውቀት ባለቤቶች ደረጃ
ክፍል - 14
እውቀት ካልተሰራበት ተጠያቂ ያደርጋል
ሰዎች የቂያማ ቀን በእውቀታቸው ምን እንደሰሩበት ይጠየቃሉ፡፡
አቡ በርዘተ አልአስለምይ የሚከተለውን የረሱል ﷺ ሐዲስ አስተላልፏል ፡
"لا تزول قدما عبد يوم القيامة حتى يسأل عن أربع – وذكر منها عليه الصلاة والسلام - : عن علمه ماذا عمل به" أخرجه الترمذي (2417)
“የቂያማ ቀን የባሪያው ሁለት እግሮች ከአራት ነገሮች እስከሚጠየቅ አይወገዱም - ከእነርሱ መካከል ረሱል የሚከተለውን አወሱ ፡ በእውቀቱ ምን እንደሰራበት (ይጠየቃል)”
ይህን አስመልክቶ አቡ ደርዳእ የሚከተለውን ተናግሯል ፡
"إنما أخشى يوم القيامة أن يناديني ربي على رؤوس الخلائق ، فيقول : يا عومر ماذا عملت فيما علمت؟"
“የቂያማ ቀን ፣ ጌታየ ከፍጡራን መካከል ጠርቶ 'ኡመይር ሆይ! ባወቅከው ምን ሰራህ?' ማለቱን ነው የምፈራው።”
ይህ ከባድ እና ታላቅ አደጋ ያለው አስፈሪ ጉዳይ ነው፡፡ ማንኛውም ባሪያ በፈጸመው ድርጊት ፣ ባወቀው እውቀት ምን እንደሰራበት የቂያማ ቀን መጠየቁ አይቀርም - ምክንያቱም የእውቀት አላማው ተግባር ነውና፡፡
በርካታ ሰለፎች የሚከተለውን ንግግር መናገራቸውም ተወርቷል ፡
"ليتني أنجو من علمي – يقصد من العلم الذي تعلمه – كفافا , لا لي ، ولا علي"
“ከእውቀቴ (ከመጠየቅ) ነጻ ብሆን እመኛለሁ - አላማው የተማረውን ትምህርት ማለቱ ነው - ለእኔም ሳይሆን ፣ በእኔም ላይ ሳይሆን ቢቀር (እመኛለሁ)”
ይህ ፣ ሰለፎች ምን ያክል አሏህን እንደሚፈሩ ያመላክታል፡፡
ሀሰን አልበስርይ ደግሞ የሚከተለውን ተናግረዋል :-
"إن المؤمن جمع بين إحسان ومخافة ، والمنافق جمع بين إساءة وأمل"
“ሙእሚን በጎ ስራ እና ፍርሃትን ሰብስቧል ፤ ሙናፊቅ ደግሞ ክፉ ስራ አና ከንቱ (ተፈጻሚ የማይሆን) ምኞትን ሰብበቧል፡፡”
አብደላህ ብን አቢ ሙለይካ የሚከተለውን ተናግሯል :-
"أدركت أكثر من ثلاثين صحابيا كلهم يخاف النفاق على نفسه" (علقه البخاري في "صحيحه" : باب خوف المؤمن أن يحبط عمله وهو لا يشعر (1\110 – "الفتح")
“ከሰላሳ በላይ ሶሃቦችን ፣ ሁሉም በነፍሳቸው ላይ ኒፋቅን የሚፈሩ ሆነው አግኝቻለሁ።"
ሶሀቦችና እነርሱን በመልካም የተከተሉት በሁለት ታላላቅ ደረጃዎች መካከል አላህ ሰብስቧቸዋል፡፡ መልካም በመስራትና ስራችን ከአላህ ዘንድ ተቀባይነት ላያገኝ ይችላል በሚል የፍርሀት ደረጃዎች፡፡
አላህ በቁርዓኑ የሚከተለውን ተናግሯል:-
وَالَّذِينَ يُؤْتُونَ مَا آتَوا وَّقُلُوبُهُمْ وَجِلَةٌ أَنَّهُمْ إِلَىٰ رَبِّهِمْ رَاجِعُونَ
"እነዚያም የሚሰጡትን ነገር እነርሱ ወደ ጌታቸው ተመላሾች መኾናቸውን ልቦቻቸው የሚፈሩ ኾነው የሚሰጡት፡፡"
(ሙእሚኑን ፡ 60)
አኢሻ የሚከተለውን ተናግራለች፤
ይህን አንቀጽ አስመልክቶ 'እነዚህ አስካሪ መጠጥ የሚጠጡ ፣ዝሙት የሚፈጽሙና የሚሰርቁ ሰዎች ናቸውን?' በማለት ረሱልን ጠየቅኋቸው።
ረሱልም ﷺ የሚከተለውን ምላሽ ሰጡኝ:-
"لا يا ابنة الصديق! ولكنهم الذين يصومون ويصلون ويتصدقون ويخافون أن لا يتقبل منهم ، أولئك الذين يسارعون في الخيرات" رواه الترمذي (3175)
“'የ (አቡበክር) ሲዲቅ ልጅ ሆይ! አይደለም' ፤ 'እነርሱ ይጾማሉ ፣ይሰግዳሉ ፣ይሶድቃሉ ፣ ይሁን እንጅ ስራችን ተቀባይነት ሊያጣ ይችላል ብለው ይፈራሉ' ፤ 'እነዚህ ሰዎች በመልካም የሚሽቀዳደሙ ናቸው' ”
አላህ የሚከተለውን ተናግሯል ፡
وَإِذْ يَرْفَعُ إِبْرَاهِيمُ الْقَوَاعِدَ مِنَ الْبَيْتِ وَإِسْمَاعِيلُ رَبَّنَا تَقَبَّلْ مِنَّا ۖ إِنَّكَ أَنتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ
"ኢብራሂምና ኢስማኢልም «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል፡፡ አንተ ሰሚውና ዐዋቂው አንተ ነህና»
(በቀራ ፡ 127)
ውሃይብ ብን አልወርድ ከላይ የጠቀስነውን የቁርአን አንቀጽ አነበበና አለቀሰ፡፡ ከዚያም የሚከተለውን ተናገረ:-
"يا خليل الرحمن! ترفع قوائم بيت الرحمن وأنت مشفق أن لا يقبل منك!"
“አንተ የረህማን ወዳጅ! የረህማንን ቤት ትገነባለህ ፣ (እንደገና) ስራህ ከአንተ ተቀባይነት ላያገኝ ይችላል ብለህ ትጨነቃለህ”
በተማረው ፣ በተገነዘበው እንዲሁም ሰዎችን በእርሱ በሚያዘው ነገር እራሱ ተፈጻሚ በማያደርግ ሰዉ ላይ በቁርዓን እና በሐዲስ ከባድ ዛቻዎች መጠዋል ፡፡
አላህ የሚከተለውን ተናግሯል ፡
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لِمَ تَقُولُونَ مَا لَا تَفْعَلُونَ
كَبُرَ مَقْتًا عِندَ اللَّهِ أَن تَقُولُوا مَا لَا تَفْعَلُونَ
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የማትሠሩትን ነገር ለምን ትናገራላችሁ? የማትሠሩን ነገር መናገራችሁ አላህ ዘንድ መጠላቱ ተለቀ፡፡"
(ሶፍ 2-3)
۞ أَتَأْمُرُونَ النَّاسَ بِالْبِرِّ وَتَنسَوْنَ أَنفُسَكُمْ وَأَنتُمْ تَتْلُونَ الْكِتَابَ ۚ أَفَلَا تَعْقِلُونَ
"እናንተ መጽሐፉን የምታነቡ ሆናችሁ ሰዎችን በበጎ ሥራ ታዛላችሁን? ነፍሶቻችሁንም ትረሳላችሁን? (የሥራችሁን መጥፎነት) አታውቁምን?"
(በቀራ ፡ 44)
ቡኻሪና ሙስሊም እንዲሁም ሌሎቸ በዘገቡት ኡሳማ የሚከተለውን የረሱል ሐዲስ አስተላልፈዋል :-
“የቂያማ ቀን ግለሰቡ ይመጣል ፤ እሳት ውስጥ ይጣላል ፤ አንጀቶቹ ይወጣሉ ፤ በእርሷ ልክ አህያ በወፍጮው እንደሚዞረው ይዞራል። የእሳት ሰዎች ይመጣሉ፡፡ 'እከሌ ሆይ! ሁኔታህ ምንድን ነው? በመልካም ታዘን ፣ ከመጥፎ ትከለክለን አልነበረምን?' ይሉታል። እርሱም :- 'አዎ፤ በመልካም አዛችሁ ነበር ፤ እኔ ግን አልተገብረውም ፤ ከመጥፎ እከለክላችሁ ነበር እኔ ግን እፈጽመው ነበር' ይላቸዋል።”
በመጨረሻም ፡ በአገራችን ከሚገኙ ቀደምት የፊቅህ አሊሞች መካከል አንዱ በሆኑት ሸይኽ ሙሐመድ ሙስጦፋ በተገጠመች ትምህርት አዘል ግጥም ጽሁፌን እቋጫለሁ።
እናንተ የእኛ ሰዎች ኪታብ የቀራችሁ
ሀቁን ተከተሉ ለአላህ ብላችሁ
ይህን ሙዳሀና ተውት እባካችሁ
ለቁርስም ለሻሂ ለልብስ እያላችሁ
ከአላህ ጠላቶች ጋር ገጠመ ሀላችሁ
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصيرة