ለጤናችን ጽዋ እናንሳ !
ዕድሜህ 30ን ሲሻገር ለጤናህ መጠንቀቅ መጀመር አለብህ። 40ን ስትሻገር ግን የዘወትር ልማዶችህን ማስተካከል አለብህ።
አለዚያ ስኳር፣ ደም ግፊት ሌላም ሌላም ሊያስቸግሩህ ይችላሉ።
ሰውነትህ ምልክት ሲሰጥህ አዳምጠውና ተገቢውን ማስተካከያ አድርግ
ከምልክቱ በፊትም ይሁን በኋላ ለጥንቃቄ ይህንን ልማድ አድርግ።
፩) ከእንቅልፍ እንደተነቃህ ሁለት ብርጭቆ ውሃ ጠጣ።
ውሃ የሰውነታችን ዋና ክፍል ነው። ውሃ ለጤናም ለውበትም ጠቃሚ ነው። ውሃ በበቂ መጠን ጠጣ። በቀን 8 ብርጭቆ ወይም 2 ሊትር ውሃ ጠጣ።
ቢቻል በቫይታሚን የበለጸገ ውሃ ጠጣ። ይህንን የቫይታሚን ውሃ ካላገኘህ ሎሚ፣ ኩኩምበር፣ ዝንጅብል፣ እርድና ቀረፋ በመጠኑ ጨምረህ ጠጣ።
፪) ቁርስህን ቀለል ያለና በፕሮቲንና ገለባ/ፋይበር የበለጸገ ምግብ ብላ።
ፕሮቲን ውድ ከመሰለህ እንቁላል፣ ለውዝ፣ አቮካዶ፣ ፉል አሉልህ። እናም ቁርስህን እንቁላል፣ ቆስጣ ወይም አቮካዶ ወይም ፉል ወይም ጩኮ ብላ።
የሰሃንህ ግማሽ በጎመና ገመን ይሞላ። ቀሪው በፕሮቲን እና 10% ያህሉ በካርቦሃይድሬት ይሞላ። ዳቦ ስትበላ ገለባው በበዛ እና በጠቆረ ዱቄት የተሠራ ዳቦ ይሁን።
፫) ምሳህን ሲርብህ ብላ። ሳይርብህ ሰዓት ስለደረሰ ብቻ አትብላ።
ምግብ ስትበላ ለጥጋብ ሩብ ጉዳይ ላይ አቁም። Hara hachi bu ይሉታል ጃፓኖች።
፬) ከምሽቱ 1:00 ሰዓት በኋላ ምግብ አትብላ። የግድ አምሽተህ ከበላህም ምግብ ከበላህ በኋላ 3:00 ያህል ቆይተህ ተኛ።
፭) ቡና አታብዛ። በቀን 1 ወይም ቢበዛ 2 ስኒ በቀን በቂ ነው።
ቢጫ ወይም ወርቃማ ቀለም ያለውን የዐረብ ዓይነት ቡና ጠጣ እንጂ ጥቁር ቡና አትጠጣ።
፮) በጎ በጎውን አስብ። ከሰው ተጫወት። ሳቅ፣ ተዝናና። ጨፍጋጋ ሃሳቦች ላይ አትቆይ። ቂም አትያዝ። አምላክህን አመስግን። ጸልይ። ጸሎት የመንፈሳዊውን ዓለም የማይታየውን መዋጊያ መሳሪያ ነው።
፯) መጾምን አዘውትር። ብትችል በሳምንት 3 ቀን እስከ 9:00 ሰዓት ጹም።
ብትችል ደግሞ ዘወትር በ4:00 ሰዓት እና 12:00 ሰዓት ብትበላ ጥሩ ነው። እኔ በ3:00 ሰዓት እና በ9:00 ሰዓት መብላት መርጣለሁ።
ጾም ለውስጣዊ አካልህም ለአእምሮህም ጽዳት ወሳኝ ነገር ነው።
፰) በቂ እንቅልፍ ተኛ።
ከምሽቱ 3:00 በኋላ ብትተኛ እና 11:00 ሰዓት መነሳትን ልማድ ብታደርግ ለጤናህ መልካም ነው።
የእንቅልፍ ሰዓትህን አታዘበራርቅ።
የእንቅልፍ እጥረት ያልታወቀበት የጤና ጸር ነው።
ሲመሽ ከሞባይል ወደ መጽሓፍ ንባብ ዙር። ከ40 ዓመት በኋላ እንቅልፍህ የተመጠነ እና የተለመደ ይሁን።
መስኮቱ አየር በማያስገባና በታፈነ ቤት ውስጥ አትተኛ። Sleep Apnea ስለሚባል ችግር አልሰማህም? Check!
፱) የጠዋት ፀሓይ ብትሞቅ ለጤናህ ይበጅሃል። የጠዋት ፀሓይ ለህጻን ልጅ ብቻ ነው ያለው ማን ነው?
፲) ተንቀሳቀስ።
በእግርህ ፈጠን ፈጠን እያልክ ተራመድ፣ ደረጃ ውጣ። ጎንበስ ቀና በል። ስገድ። ተንጠራራ። ከቻልክ ደግሞ ጂም ገብተህ ዋኝ፣ ዱብ ዱብ በል፣ ብረት አንሳ።
አይበቃም?
@Amazing_Fact_433