✅ዋሽንግተኒያን መፅሄት በባለፈው እትሙ ‹‹አንድ ሳምንት የዘለቀው ድንቅ ሠርግ›› በሚል አንድ ዘገባ አቅርቧል፡፡ እንደዘገባው ኤለን የጥርስ ሀኪም የሆነ ህንዳዊ ነው፡፡ አሜት ደግሞ በቨርጂኒያ ነዋሪ የሆነችና የአይቲ ኢንጂነር የሆነች ኤርትራዊት ናት፡፡
✅ የሁለቱም የጋራ ጓደኛ የሆነ ልደት በዋሽንግተን ዲሲ በሚከበርበት ወቅት ትውውቃቸው መጀመሩን አስረድቷል፡፡ ከዚያም በጆርጅ ታውን ራት ተቀጣጥረው ከተገናኙ በኋላ ግንኙነታቸውን ማጠናከራቸውን ገልጿል፡፡ ይህ ከሆነ ከአምስት አመት በኋላ በአሊንግተን ውስጥ ኤለን ተንበርክኮ ታገቢኛለሽ የሚል ጥያቄ ሊያቀርባለት ችሏል፡፡ ጥያቄው ተቀባይነት ካገኘ በኋላ ሁለቱ ጥንዶች ስለሰርጋቸው ማሰብና ማቀድ ይጀምራሉ፡፡ ውጥናቸው ተሳክቶም አንድ ሳምንት የፈጀ ልዩና ድንቅ ሠርግ ለማድረግ እንደቻሉ ዘገባው አስረድቷል፡፡
✅ ይህ ሠርግ አንድ ሳምንት ሊዘልቅ የቻለው የህንድና የኤርትራ ባህል በሙሉ መካተት ስለነበረበት ነው፡፡ በመሆኑም ከህንድና ከኤርትራ ድምፃዊያን ተጠርተውና ዘመድ ወዳጆቻቸው ተገኝተው የሠርግ ስነስርአቱ ሊከናወን እንደቻለ ዘገባው አስታውቋል፡፡ ጥንዶቹ ለሳምንት በዘለቀለው በዚህ ሠርግ ደስታቸውን ካጣጣሙ በኋላ ከድካማቸው ለማረፍና ለጫጉላ ሽርሽር ወደኢንዶኔዥያ ባሊ ሄደዋል ብሏል ዘገባው፡፡